ቅዱሳት መጻህፍት
፪ ኔፊ ፲፫


ምዕራፍ ፲፫

ይሁዳና ኢየሩሳሌም ባለመታዘዛቸው ይቀጣሉ—ጌታም ለህዝቡ ይማፀናል፣ እናም ሕዝቡን ይፈርዳል—የፅዮን ሴት ልጆች በዓለማዊነታቸው የተነሳ የተረገሙና የተሰቃዩ ናቸው—ኢሳይያስ ፫ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

፩ እነሆም፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ፣ ምርኩዝን፣ እና ድጋፍን፣ የዳቦን ድጋፍ ሁሉ እናም የውሃንም ድጋፍ ሁሉ ይወስዳል—

፪ ሀያሉን ሰውና፣ ተዋጊውንም፣ ፈራጁንም፣ ነቢዩንም፣ ብልሁንና፣ ሽማግሌውን ሰው ይወስዳል፤

፫ የሀምሳ አለቃውንና፣ የተከበረውን ሰው፣ አማካሪውንም፣ እና ብልሁን ሠራተኛና፣ ጥሩ ተናጋሪውን ይወስዳል።

፬ እናም ልዑሎቻቸው ይሆኑ ዘንድ ሕፃናትን እሰጣቸዋለሁ፣ ሕፃናቶችም እነርሱን ይገዛሉ።

፭ እናም ሕዝቡ ይጨቆናል፣ አንዱ በሌለኛው፣ እንዲሁም አንዱ በጎረቤቱ፤ ሕፃናቱ በሽማግሌው ላይ እንዲሁም ፀያፍ አድራጊዎች በተከበረው ላይ ይኮራሉ።

፮ አንድ ሰው በአባቱ ቤት ውስጥ ወንድሙን በያዘ ጊዜ፣ እናም እንዲህ ሲለው፥ አንተ ልብስ አለህ፣ አለቃም ሁንልን፣ እናም ይህም ጥፋት ከእጅህ በታች እንዲሆን አትፍቀድ—

፯ በዚያ ቀን እንዲህ በማለት ይምላል—ባለመድሀኒት አልሆንም፤ ምክንያቱም በቤቴ ዳቦም ሆነ ልብስ የለምና፤ የሕዝቡም አለቃ አታድርጉኝ።

፰ የክብሩን ዐይን ለማስቆጣት፣ ምላሳቸውና ስራቸው ጌታን ስለሚፃረሩ ኢየሩሳሌም ፈረሰች፣ እናም ይሁዳ ወደቀች።

፱ በፊታቸው የሚታየው በእነርሱ ላይ ይመሰክራል፣ እናም ኃጢአታቸው እንደሰዶም አይነት እንደሆነ ያውጃል፣ እናም ሊደብቁት አይችሉም። በራሳቸው ላይ ኃጢያትን በማምጣታቸው ለነፍሳቸው ወዮላቸው!

፲ የስራቸውን ፍሬ ይበላሉና፤ ፃድቃንን መልካም ይሆንላችኋል በላቸው።

፲፩ ወዮላቸው ለክፉዎች፤ ይጠፋሉና፤ የስራቸውም ዋጋ በእነርሱ ላይ ይሆናል!

፲፪ እናም ሕዝቤ፣ ሕፃናት ጨቋኛቸው ናቸው፣ እንዲሁም ሴቶች ገዢዎቻቸው ናቸው። ሕዝቤ ሆይ፣ የመሩአችሁ ያስቱአችኋል፣ እንዲሁም የምትሄዱበትንም መንገዳችሁን ያጠፋሉ።

፲፫ ጌታ ለሙግት ተነስቷል፣ እናም በሕዝቡም ላይ ሊፈርድ ቆሟል።

፲፬ ጌታ ከሕዝቡ ሽማግሌዎችና ከልዑሎች ጋር ለፍርድ ይገባል፤ ምክንያቱም የወይኑን ቦታ እና በቤታችሁ የሚገኙት ድሆችን ብዝበዛ የጨረሳችሁ እናንተ ናችሁ።

፲፭ እናንት ምን ማለታችሁ ነው? ሕዝቤን ታደቁአቸዋላችሁ፣ እና የድሆችንም ፊት ትፈጫላችሁ፣ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

፲፮ ከሁሉም በላይ፣ ጌታ እንዲህ አለ፥ የፅዮን ሴት ልጆች ትዕቢተኛ ስለሆኑና አንገታቸውን በማስገግ ስለሚራመዱና በሚሄዱበት ጊዜ ዐይናቸውን በማጣቀስ፣ ፈጠን ብለው በመራመድ እናም በእግራቸው እያቃጨሉ በመሄዳቸው ምክንያት—

፲፯ ስለዚህ ጌታ የፅዮንን ሴት ልጆች ራስ በቡሃነት ይመታል፣ እናም ጌታ ሀፍረተ-ስጋቸውን ይገልጣል።

፲፰ በዚያ ቀን ጌታ የሚያንቃጭለውን ጌጣቸውን፣ መርበብን፣ እና ጨረቃ የሚመስለውን የአንገት ጌጣቸውን ውበት ያስወግዳል።

፲፱ ሰንሰለቱንና አምባሩን፣ እና መሸፈኛውን፤

፳ ቆብና የእግር አልቦውን፣ እና የራስ ማሰሪያውንና፣ የሽቶውን ዕቃ፣ እና የጆሮ ቀለበቶቹን፤

፳፩ ቀለበት እና የአፍንጫ ጌጥ፤

፳፪ ውድ ሱፍ ልብስንም፣ ካባውንንም፣ መጎናፀፊያውንም፣ እና ፀጉር መጠቅለያውን፤

፳፫ መስታወቱንም፣ ከጥሩ በፍታ የተሰራውንም ልብስ፥ ራስ ማሰሪያውንም፥ ዓይነ ርግቡንም ያስወግዳል።

፳፬ እናም እንዲህ ይሆናል፣ በጥሩ ሽታ ፈንታ ግማት፣ እና በመታጠቅያው ፈንታ ቀዳዳ፤ ጠጉርንም በመነቀስ ፈንታ መላጣነት፤ በተብለጨለጨው ልብስ ፈንታ ማቅ፤ በውበትም ፈንታ ጠባሳ ይሆናል።

፳፭ ወንዶችሽ በሰይፍ ጀግኖችሽም በውጊያ ይወድቃሉ።

፳፮ እናም በሮችዋ ያዝናሉ ያለቅሱማል፤ እናም ተስፋ በመቁረጥ በመሬት ላይ ብቻዋን ትቀመጣለች።

      • ኢሳ. ፫፥፮።

      • ዕብ. የሚያስር (ቁስልን)፤ ይህም ለችግርህ መፍትሄ ልሰጥህ አልችልም ማለት ነው።

      • ኤር. ፱፥፲፩።

      • ሰቆ. ፩፥፫።

      • ዘዳግ. ፲፪፥፳፰።

      • ኢሳ. ፱፥፲፮።

      • ዕብ. ገዢዎች ወይም መሪዎች።

      • ኢሳ. ፭፥፯።

      • ፪ ኔፊ ፳፰፥፲፪–፲፫።

      • ይህም አጭበርብሮ ማግኘት ማለት ነው።

      • ዕብ. መጨረስ፣ ወይም መቃጠል።

      • ይህም በሽንገላ ጸባይ በአጭር፣ ፈጣን እርምጃ መሄድማለት ነው።

      • ዕብ. ማጋለጥ፤ “አሳፍራቸው” የሚል ትርጉም ያለው የአነጋገር ዘይቤ።

      • ምናልባት የጸጉር ማሰሪያ። ባለስልጣኖች በቁጥሮች ፲፰–፳፫ ውስጥ ስለተዘረዘሩት የሴት ጌጦች ምን እንደሆኑ አይስማሙም።

      • ይህም እንደ ሩብ ጨረቃ ቅርጽ ያላቸው ጌጦች ማለት ነው።

      • ዕብ. መጋረጃዎች።

      • ዕብ. የሚያንጸባርቅ ልብስ።

      • ወይም ስስ ልብስ።

      • ዕብ. ቁራጭ ጨረቅ።

      • ወይም ካባ።

      • ወይም መጥበስ (በባሪያ ቆዳ ላይ የሚደረግ ምልክት)።