ቅዱሳት መጻህፍት
፪ ኔፊ ፳፰


ምዕራፍ ፳፰

በመጨረሻው ዘመን ብዙ ሀሰተኛ ቤተክርስቲያኖች ይሰራሉ—ውሸትን፣ ከንቱነትን፣ እና የማይረባ ትምህርትንም ያስተምራሉ—በሐሰተኛ አስተማሪዎችም የተነሳ ክህደት ይበዛል—ዲያብሎስ በሰዎች ልብ ቁጣን ያመጣል—የተለያዩ ሐሰተኛ ትምህርቶችን ሁሉ ያስተምራል። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

እናም አሁን እነሆ፣ ወንድሞቼ መንፈስ እንደገፋፋኝ ተናግሬአችኋለሁ፤ ስለሆነም፣ እነዚህ ነገሮች በእርግጥ እንደሚሆኑ አውቃለሁ።

እናም ከመጽሐፉ ላይ የተፃፉት ነገሮች ለሰው ልጆች፣ እና በተለይም የእስራኤል ቤት ቅሪት ለሆኑት ለእኛ ዘር፣ ታላቅ ዋጋ ይኖራቸዋል።

በዚያን ቀን እንዲህ ይሆናል፣ ለጌታም ያልሆነው የተሰሩት ቤተክርስቲያኖች፣ አንዱም ለሌላው ይለዋል—እነሆ፣ እኔ የጌታ ነኝ፤ እናም ሌሎቹም እኔ፣ እኔ የጌታ ነኝ ይላሉ፤ እናም ለጌታ ያልተሰሩት ቤተክርስቲያናት ሁሉ እንደዚህ ይላሉ—

እናም አንዳቸው ከሌላኛው ይከራከራሉ፤ ካህናቶቻቸውም አንዱ ከሌላ ይከራከራሉ፣ እናም ከራሳቸው የሆነውን ትምህርት ያስተምራሉ፣ የመናገርን ችሎታ የሚሰጠውንም መንፈስ ቅዱስ ይክዳሉ።

እናም የእግዚአብሔርን ኃይል፣ የእስራኤሉንም ቅዱስ ይክዳሉ፤ ለህዝቡም እንዲህ ይላሉ—አድምጡን፣ እናም የእኛን መመሪያ ስሙ፤ እነሆም እግዚአብሔር ዛሬ የለምና፣ ጌታና አዳኝ ስራውን ሰርቷል፣ እናም ኃይሉን ለሰዎች ሰጥቷልና።

እነሆ፣ የእኔን መመሪያ አድምጡ፤ በጌታ እጅ የተሰራ ተአምር አለ ካሉ አትመኑአቸው፤ በዛሬ ጊዜ እርሱ የተአምራት አምላክ አይደለምና፤ እሱ ስራውን ሰርቷል።

አዎን፣ እናም ብዙዎች እንዲህ የሚሉ አሉ፥ ብሉ፣ ጠጡ፣ እናም ተደሰቱ፣ ነገ እንሞታለንና፤ ይህም ለእኛ መልካም ይሆናል።

እናም ሌሎች ደግሞ እንዲህ የሚሉ ብዙ አሉ፥ ብሉ፣ ጠጡ፣ እናም ተደሰቱ፤ ይሁን እንጂ፣ እግዚአብሔርን ፍሩ—ትንሽ ኃጢያትን ብንሰራ ጥፋተኛ አያደርገንም፤ አዎን፣ ትንሽም ዋሹ፣ በቃሉ የተነሳ በሌላ ላይ ዕድል ተጠቀሙ፣ በጎረቤታችሁም ላይ ጉድጓድን ቆፍሩ፤ በዚህ ምንም ጉዳት የለም፤ እናም እነዚህን ነገሮች ሁሉ አድርጉ፣ ነገ እንሞታለንና፤ እናም ምንም እንኳን ጥፋተኛ ብንሆን፣ እግዚአብሔር በትንሹ ይቀጣናል፣ እናም በመጨረሻ በእግዚአብሔር መንግስት እንድናለን።

አዎን፣ እናም እንደዚህ ውሸትና ከንቱና የማይረባ ትምህርትን የሚያስተምሩ፣ እናም በልባቸውም የታበዩና፣ ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከጌታ ለመሰወር የሚፈልጉ ብዙዎች ይኖራሉ፤ እናም ስራቸውም በጨለማ ውስጥ ይሆናል።

እናም የቅዱሳን ደም ከምድር በእነርሱ ላይ ይጮሃል።

፲፩ አዎን፣ ሁላቸውም መንገዳቸውን ስተዋል፤ ተበላሽተዋልም

፲፪ በኩራትና፣ በሐሰተኛ አስተማሪዎች፣ እንዲሁም በሀሰት ትምህርት የተነሳ፣ ቤተክርስቲያናቸው ተበላሽቷል፣ እናም ቤተክርስቲያኖቻቸው ከፍ ብለዋል፤ በኩራትም የተነሳ ተወጥረዋል።

፲፫ በመልካሙ ቅዱስ ስፍራ የተነሳ ድሆችን ይበዘብዛሉ፤ በመልካም ልብሳቸውም የተነሳ ድሆችን ይበዘብዛሉ፤ እናም ትሁታንንና በልባቸው ድሆች የሆኑትን ያሳድዳሉ፣ በኩራታቸው የተነሳ ተወጥረዋልና።

፲፬ አንገተ ደንዳና እና ትምክህተኞች ናቸው፤ እናም አዎን፣ ከጥቂት ትሁት የክርስቶስ ተከታዮች በስተቀር በኩራታቸው፣ በክፋታቸው፣ በእርኩሰታቸውና በዝሙት የተነሳ ሁሉም ባክነዋል፤ ይሁን እንጂ፣ ተመርተዋል፣ በብዙ መንገድ የተሳሳቱበት ምክንያትም በሰዎች አስተያየቶች ስለተማሩ ነው።

፲፭ አቤቱ በልባችሁ ኩራት የተወጠሩ ጥበበኞች፣ የተማሩና፣ ሀብታሞች፣ እናም ሀሰተኛ ትምህርትን የሚያስተምሩ ሁሉና፣ ዝሙትን የሚፈጽሙ ሁሉ፣ እናም ትክክለኛውን የጌታን መንገድ የሚያጣምሙ፣ ወዮ፣ ወዮ፣ ለእነርሱ ወዮላቸው ወደ ሲዖልም ይጣላሉና ይላል ሁሉን የሚገዛ ጌታ እግዚአብሔር።

፲፮ ፃድቁንም በከንቱ ነገር ዞር የሚይደርጉና ጥሩ የሆነውን የሚሰድቡ፣ እናም ዋጋ የለውም ለሚሉ ወዮላቸው! ጌታ እግዚአብሔር የምድር ነዋሪዎቹን የሚጎበኝበት ቀን በፍጥነት ይመጣልና፤ እናም በዚያን ቀን በጥፋት ፈጽመው የበሰሉትም ይጠፋሉ።

፲፯ ነገር ግን እነሆ፣ የምድር ነዋሪዎች ለክፋታቸውና ለእርኩሰታቸው ንሰሀ ከገቡ አይጠፉም ይላል የሠራዊት ጌታ።

፲፰ ነገር ግን እነሆ፣ ያቺ ታላቋና የርኩሰት ቤተክርስቲያን የምድር ሁሉ ጋለሞታም ወደ አፈር ትወድቃለች፣ እናም አወዳደቋም ታላቅ ይሆናል።

፲፱ የዲያብሎስ መንግስት መናወጥ አለበት፣ እናም የእርሱ የሆኑትም ለንስሀ መነቃቃት ይገባቸዋልና፣ አለበለዚያ ዲያብሎስ በዘለዓለማዊ ሰንሰለቱ ይይዛቸዋል፣ እናም እነርሱ ለቁጣ ይነሳሳሉም፣ ይጠፋሉም፤

እነሆም፣ በዚያን ቀን በሰው ልጆች ልብ ውስጥ ይቆጣል፣ እናም ጥሩ በሆነውም ላይ ለቁጣ ያነሳሳቸዋል።

፳፩ እናም እርሱ ሌሎችን ያረጋጋልና፣ ቀስ ብሎም ወደ ስጋዊ ደህንነት አባብሏቸው እንዲህ ይላሉ፥ በፅዮን ሁሉም መልካም ነው፤ አዎን፣ ፅዮን ትለመልማለች፤ ሁሉም መልካም ነው—ዲያብሎስም ነፍሳቸውን እንዲህ ያታልላል፣ እናም በጥንቃቄ ወደ ሲኦል ይመራቸዋል።

፳፪ እናም እነሆ፣ ሌሎችን እያሞገሰ ያስታቸዋል፣ እናም ሲኦል የለም ብሎ ይነግራቸዋል፤ እናም ይላቸዋል፥ እኔ ዲያብሎስ አይደለሁም፣ እርሱ የለምና—እናም ማላቀቅ በማይቻለው በመጥፎው ሰንሰለቱ እስከሚያስራቸው ድረስ በጆሮአቸው እንዲህ ያንሾካሹካል።

፳፫ አዎን፣ በሞትና በሲኦል ተይዘዋል፤ እናም ሞትና ሲኦል እንዲሁም ዲያብሎስና በእነርሱም የተያዙት ሁሉ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት መቆም አለባቸው፣ እናም እንደስራቸው ይፈረድባቸዋል፣ ከዚያም ለእነርሱ በተዘጋጀው ቦታ ወደማያቋርጥ ስቃይ ወደሆነው፣ እንዲሁም ወደ እሳትና ወደ ዲኑ ባህር መሄድ አለባቸው።

፳፬ ስለዚህ፣ በፅዮን ለሚዝናናው ወዮለት!

፳፭ ሁሉ መልካም ነው! ብሎ ለሚጮህ ወዮለት!

፳፮ አዎን፣ የሰዎችን አስተያየት ለሚያዳምጥና፣ የእግዚአብሔርን ኃይልና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ለሚክድ ወዮለት!

፳፯ አዎን፣ እኛ ተቀብለናል፣ እናም ሌላ አንፈልግም ለሚልም ወዮለት።

፳፰ እናም በአጠቃላይ ለሚንቀጠቀጡ ሁሉና፣ በእግዚአብሔር እውነት ምክንያት ለሚቆጡ ወዮላቸው! እነሆም በአለት ላይ የሰራ ይህን በደስታ ይቀበላል፤ እናም በአሸዋ መሰረት ላይ የሰራው ግን በፍርሃት እወድቃለሁ ብሎ ይንቀጠቀጣል።

፳፱ የእግዚአብሔርንም ቃል ተቀብለናል፣ እናም የእግዚአብሔርንም ቃል ከዚህ በተጨማሪ ምንም አንፈልግም፣ ምክንያቱም በቂ አለንና ለሚሉት ወዮላቸው!

እነሆም፣ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል—ለሰው ልጆች በትዕዛዝ ላይ ትዕዛዝ፣ በስርዐት ላይ ስርዐት፣ ጥቂት በዚህ፣ ጥቂት በዚያ እሰጣለሁ፤ ትምህርቴን የሚሰሙ፣ እናም ምክሬን የሚያደምጡ የተባረኩ ናቸው፣ ጥበብን ይማራሉና፤ ለሚቀበልም ተጨማሪ እሰጣለሁና፤ እና ይበቃናል ለሚሉም፣ ያላቸውም እንኳን ቢሆን ይወሰድባቸዋል።

፴፩ እምነቱን በሰው የሚያደርግ፣ ወይም ስጋን ክንዱ የሚያደርግ፣ ወይም አስተያየታቸው በመንፈስ ቅዱስ ሀይል አማካኝነት ካልተሰጠ በስተቀር የሰውን ትምህርት የሚሰማ የተረገመ ነው።

፴፪ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለአህዛብ ወዮላቸው ይላል! ክንዴን ከቀን ወደቀን ብዘረጋትም እንኳን ይክዱኛልና፣ ይሁን እንጂ፣ ንስሀ የሚገቡና ወደ እኔ የሚመጡ ከሆነ እምራቸዋለሁ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ክንዴ ቀኑን ሁሉ ትዘረጋለችና ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።