ቅዱሳት መጻህፍት
፫ ኔፊ ፳፬


ምዕራፍ ፳፬

የጌታ መልዕክተኛ የክርስቶን ዳግም ምፅዓት መንገድ ያዘጋጃል—ክርስቶስ በፍርድ ወንበር ይቀመጣል—እስራኤል አስራትን እናም በኩራትን እንዲከፍል ታዛለች—የመታሰቢያ መጽሐፍ ተጠብቋል—ሚልክያስ ፫ን አነጻፅሩ። ፴፬ ዓ.ም. ገደማ።

እናም እንዲህ ሆነ የሚነግራቸውን፣ አብም ለሚልኪያስ የሰጠውን ቃላት እንዲጽፉት አዘዛቸው። እናም እንዲህ ሆነ ከጻፉትም በኋላ አስረዳቸው። እናም እንዲህ በማለት ለእነርሱም የነገራቸው ቃላት እነዚህ ናቸው፥ አብም ለሚልኪያስ እንዲህ ሲል ተናገረው—እነሆ፣ መልዕክተኛዬን እልከዋለሁ፣ እርሱም መንገዱን ከፊቴ ያዘጋጃል፣ እናም የምትፈልጉት ጌታም በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፤ ያውም የምትወዱት የቃል ኪዳን መልዕክተኛ፣ እነሆ፣ ይመጣል፣ ይላል የሠራዊት ጌታ።

ነገር ግን የሚመጣበትን ቀን መታገስ የሚችልና በተገለጠ ጊዜም የሚቆም ማን ነው? እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳት እናም እንደ አጣቢ የሚያጠራ ሳሙና ነውና።

እናም እርሱም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፤ የሌዊንም ልጆች ያጠራል፣ እንደ ወርቅና ብርም ያነጥራቸዋል፣ እነርሱም ለጌታ በፅድቅ መስዋዕት የሚያቀርቡ ይሆናሉ።

ጌታም እንደ ድሮው ዘመንና እንደቀደሙት ዓመታት በይሁዳና በኢየሩሳሌም መስዋዕት ደስ ይለዋል።

እናም ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ እናም በመተተኞችና፣ በአመንዝሮች፣ በሀሰትም በሚምሉና፣ የምንደኛውን ደሞዝ በሚከለክሉ፣ እናም መበለቲቱንና ድሃ አደጉን በሚያስጨንቁ፣ እንዲሁም በመጻተኛውም ፍርድን በሚያጣምሙ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ ይላል የሰራዊት ጌታ።

እኔ ጌታ ነኝና አልለወጥም፤ ስለዚህ እናንተ የያዕቆብ ልጆች የጠፋችሁ አይደላችሁም።

ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከስርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል፣ እናም አልጠበቃችኋቸውም። ወደ እኔ ተመለሱና እኔ ወደ እናንተ እመለሳለሁ ይላል የሰራዊት ጌታ። እናንተ ግን የምንመለሰው ወዴት ነው? ብላችኋል።

ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። ነገር ግን እንዴት ነው አንተን የሰርቅነው? ብላችኋል። በአስራትና በበኩራት ነው።

እናንተ፥ ይህ ሀገር ሁሉ እኔን ሰርቋልና በእርግማን ርጉሞች ናችሁ።

በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አስራቱን ሁሉ ወደ ጎተራው አግቡ፤ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ በረከቴንም አትረፍርፌ ባላፈስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ ይላል የሠራዊት ጌታ።

፲፩ እናም ስለእናንተ ነቀዙን እገስፃለሁ፣ እናም የምድራችሁን ፍሬ አያጠፋም፣ በእርሻችሁም ያለው ወይን ፍሬውን አያረግፍም ይላል የሠራዊት ጌታ።

፲፪ እናም የተድላ ምድር ትሆናላችሁና፣ ሀገር ሁሉ ብፁዓን ብለው ይጠሩአችኋል ይላል የሠራዊት ጌታ።

፲፫ ቃላችሁ በእኔ ላይ ድፍረት ሆኖአል ይላል ጌታ። እናንተ ግን፣ በአንተ ላይ የተናገርነው ምንድነው? ብላችኋል።

፲፬ እናንተ እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፣ ስርአቶቹን በመጠበቅ በሠራዊት ጌታ ፊት ሃዘንተኞች ሆነን በመራመድ ምን ይረባናል? ብላችኋል።

፲፭ እናም አሁን የሚታበዩትን ሰዎች ብፁዐን ብለው ይጠሩአቸዋል፤ አዎን ክፉንም የሚሰሩ ጸንተዋል፤ አዎን እግዚአብሔርን የሚፈታተኑ ይለቀቃሉ።

፲፮ ጌታን የሚፈሩ እርስ በርሳቸው ሁል ጊዜ ይነጋገራሉ፤ እናም ጌታ አደመጠ፤ እናም ሰማም፤ ጌታን ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ መጽሐፍ በፊቱ ተፃፈ።

፲፯ እናም ጌጤን ስሰራ በዚያን ቀን የእኔ ይሆናሉ ይላል የሠራዊት ጌታ፤ እናም ሰው የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር እንዲሁ እምራቸዋለሁ።

፲፰ ተመልሳችሁም በፃድቁና በኃጢአተኛው መካከል፣ ለእግዚአብሔር በሚገዛውና በማይገዛው መካከል ትለያላችሁ