ቅዱሳት መጻህፍት
፫ ኔፊ ፲


ምዕራፍ ፲

በምድሪቱም ላይ ለብዙ ሰዓታት ዝምታ ሆነ—ዶሮ ጫጩቶችዋን እንደምትሰበስብ የክርስቶስ ድምፅም ህዝቡን ለመሰብሰብ ቃል ኪዳን ገባ—ፃድቃኖች የነበሩትም አብዛኞቹም ተጠብቀዋል። ፴፬–፴፭ ዓ.ም. ገደማ።

እናም አሁን እነሆ፣ እንዲህ ሆነ በምድሪቱ የነበሩት ሰዎች ሁሉ ይህንን ንግግር አድምጠዋል፣ እናም ስለዚያም መስክረዋል። እናም ከዚህ ንግግር በኋላ በምድሪቱ ላይ ለብዙ ሰዓታት ፀጥታ ነበር፤

የህዝቡም መገረም ታላቅ በመሆኑ ስለተገደሉት ወገኖቻቸው ማልቀስ እናም መጮሃቸውን አቆሙ፣ ስለዚህ ለብዙ ሰዓታት በምድሪቱ ሁሉ ላይም ፀጥታ ነበር።

እናም እንዲህ ሆነ ወደ ህዝቡም በድጋሚ ድምፅ እንዲህ ሲል መጣ፣ እናም ህዝቡ ሁሉ ሰምተውትና፣ መስክረውበት ነበር፥

አቤቱ የእነዚህ የጠፉት ታላላቅ ከተሞች ሰዎች፣ የያዕቆብ ዝርያዎች፣ አዎን፣ የእስራኤል ቤት የሆናችሁ፣ ዶሮ ጫጩትዎችዋን በክንፎችዋ እንደምትሰበስብ ስንት ጊዜ ሰበሰብኳችሁ እናም መገብኳችሁ

እናም በድጋሚ፣ ዶሮ ጫጩትዎችዋን በክንፎችዋ እንደምትሰበስብ ስንት ጊዜ ሰበሰብኳችሁ፣ አዎን፣ አቤቱ የእስራኤል ቤት የሆናችሁ የጠፋችሁት፤ አዎን፣ አቤቱ የእስራኤል ቤት የሆናችሁ እናንተ በኢየሩሳሌም የምትኖሩ፤ እናንት እንደ ጠፋችሁትም አይነት፤ አዎን፣ ዶሮ ጫጩትዎችዋን እንደምትሰበስብ ሁሉ እሰበስባችሁ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ፣ እናም እናንተ ግን አልወደዳችሁም።

እናንተ ያዳንኳችሁ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ አቤቱ ንሰሃ ከገባችሁ እናም በልባችሁ ሙሉ አላማ ወደ እኔ ከተመለሳችሁ ዶሮ ጫጩትዎችዋን በክንፎችዋ ስር እንደምትሰበስብ ስንት ጊዜ እሰበስባችኋለሁ።

ካልሆነ ግን፣ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ የአባቶቻችሁ ቃል ኪዳን እስከሚፈፀምበት ጊዜ ድረስ የመኖሪያችሁ ስፍራ ባዶ ይሆናል።

እናም አሁን እንዲህ ሆነ ህዝቡ እነዚህን ቃላት ከሰሙ በኋላ፣ እነሆ፣ ወገኖቻቸውንና ጓደኞቻቸውን በማጣታቸው በድጋሚ ማልቀስና መጮህ ጀመሩ።

እናም እንዲህ ሆነ በዚህ ሁኔታ ሦስቱ ቀናት አለፉ። እናም በጠዋት ነበር፣ እናም ጨለማው ከምድር ገጽ ላይም ተበተነ፣ ምድርም መንቀጥቀጥዋን አቆመች፣ አለቶችም መፈረካከሳቸውን አቆሙና፣ የሚያስፈራውም ማቃሰት ቆመ፤ እናም ሀይለኛ የነበረው ሁከትም ቆመ።

እናም ምድሪቱ በአንድነት ተጣበቀችም፣ ጸናችም፤ እናም በህይወት የተረፉት ሰዎች ሀዘንና፣ ለቅሶ፣ እንዲሁም ዋይታም ቆመ፤ እናም ሀዘናቸው በደስታ፤ እንዲሁም ልቅሶአቸው ወደ ውዳሴና ወደ አዳኛቸው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ምስጋና ተለወጠ፤

፲፩ እናም በነቢያቱ የተነገሩትም ቅዱሳን መፃህፍት እስከዚህ ድረስ ተፈፅመዋል

፲፪ እናም የዳኑትም ይበልጥ ፃድቃን የነበሩት ሰዎች ናቸውና፣ ነቢያትን የተቀበሉትና በድንጋይ ያልወገሩአቸውም እነርሱ ነበሩ፤ እናም የተረፉትም የቅዱሳንን ደም ያላፈሰሱት ነበሩ—

፲፫ እናም እነርሱም ድነዋልና፣ አልሰመጡም፣ እንዲሁም በምድር ውስጥም አልተቀበሩም፤ በጥልቅ ባህሩ ውስጥም ሰጥመው አልቀሩም ነበር፤ እናም በእሳት አልተቃጠሉም፣ አልወደቁባቸውምና፣ በመደፋፈጥ አልሞቱም፤ እናም በአውሎ ነፋሱም አልተወሰዱም ነበር፤ በጭስና በጨለማውም ጭጋግ አልተሸነፉም ነበር።

፲፬ እናም አሁን ማንም የሚያነብ ይረዳ፤ ቅዱስ መጽሐፍ ያለው፣ ይመርምራቸው፣ እናም እነዚህ በእሳትና፣ በጭስ፣ እንዲሁም በኃይለኛው ነፋስ፣ እናም እነርሱን ለመዋጥ በመሬት መከፈት የሆኑት ሞቶችና፣ ጥፋቶች ሁሉ፣ እናም እነዚህ ነገሮች ሁሉ የሆኑት የብዙዎቹ ቅዱሳን ነቢያት ትንቢቶች እንዲፈፀሙ እንደሆነም ይይና ይመልከት።

፲፭ እነሆ፣ እንዲህ እላችኋለሁ፣ አዎን፣ ብዙዎች በክርስቶስ መምጣት ስለእነዚህ ነገሮች መስክረዋል፣ እናም ስለእነዚህ ነገሮች በመመስከራቸው ተገድለዋል

፲፮ አዎን፣ ነቢዩ ዜኖስ ስለነዚህ ነገሮች መሰከረ፣ እናም ደግሞ ዜኖቅ እነዚህን ነገሮች በተመለከተ ተናግሯል፣ ምክንያቱም እነርሱ በተለይ የዘሮቻቸው ቅሪት ስለሆነው ስለእኛ ተናግረዋል።

፲፯ እነሆ፣ አባታችን ያዕቆብ ደግሞ ስለዮሴፍ ዘር ቅሪቶች መስክሯል። እናም እነሆ፣ እኛ የዮሴፍ ዘር ቅሪቶች አይደለንምን? እናም ስለእኛ የሚመሰክሩት እነዚህ ነገሮች አባታችን ሌሂ ከኢየሩሳሌም ባመጣቸው የነሃስ ሰሌዳዎች ላይ አልተጻፉምን?

፲፰ እናም እንዲህ ሆነ በሠላሳ አራተኛው ዓመት መጨረሻ፤ እነሆ፣ የተረፉት የኔፊ ሰዎችና ደግሞ ላማናውያን ተብለው የሚጠሩት የተረፉት፣ ታላቅ ደግ ነገርን እንደተመለከቱ፣ እናም በራሳቸውም ላይ ታላቅ በረከት እንደፈሰሰባቸው አሳያችኋለሁ፤ በዚህም የተነሳ ክርስቶስ ወደ ሰማይ እንዳረገ ወዲያውም በእውነት ለእነርሱ እራሱን ገለፀላቸው—

፲፱ ሰውነቱን ለእነርሱ አሳያቸውና፣ አገለገላቸው፤ እናም የአገልግሎቱም ታሪክ ከዚህ በኋላ የሚሰጥ ይሆናል። ስለዚህ በዚህ ጊዜ ንግግሬን አቆማለሁ።