ምዕራፍ ፳፱
የመፅሐፈ ሞርሞን መምጣት ጌታ እስራኤልን የሚሰበስብበት እንዲሁም ቃል ኪዳኑን ለመፈጸም የሚጀምርበት ምልክት ነው—የኋለኛው ቀን ራዕዮችን እንዲሁም ስጦታዎችን የማይቀበሉ የተረገሙ ይሆናሉ። ከ፴፬–፴፭ ዓ.ም. ገደማ።
፩ እናም እንግዲህ እነሆ፣ እንዲህ እላችኋለሁ፤ እነዚህ ነገሮች በቃሉ መሰረት ወደ አህዛብ ሀመምጣታቸው በጥበቡ ጌታ ተገቢ መሆናቸውን በሚመለከትበት ጊዜ፣ አብም ከእስራኤል ልጆች ጋር በድጋሚ ወደ ትውልድ ምድራቸው ለመመለስ ለቃል ኪዳን የገባውን መፈፀም እንደጀመረ ታውቃላችሁ።
፪ እናም በቅዱሳን ነቢያት የተነገሩት የጌታ ቃልም በሙሉ እንደሚፈፀሙ ታውቃላችሁ፤ እናም ጌታ ወደ እስራኤል ልጆች የሚመጣበት ጊዜውን ሀአዘገየ ማለት አያስፈልጋችሁም።
፫ እናም የተነገሩት ቃላትም ከንቱ ናቸው ብላችሁ በልባችሁ አትገምቱ፣ ምክንያቱም እነሆ ጌታ ለእስራኤል ቤት ለህዝቡ የገባውን ቃል ኪዳን ያስታውሳልና።
፬ እናም እነዚህ የተባሉት በመካከላችሁ ሲመጡ በምትመለከቱበት ጊዜ፣ ከዚያም የጌታን ስራ ልትወቅሱ አይገባችሁም፣ ምክንያቱም ሀየፍትህ ለጎራዴ በቀኝ እጁ ናትና፤ እናም እነሆ፣ በዚያን ቀን ስራውን የምትወቅሱ ከሆነ በቅርቡይህችም እንድታሸንፋችሁ ያደርጋል።
፭ የጌታን ስራ ሀየሚወቅስ ለወዮለት፣ አዎን፣ ክርስቶስን እና ስራዎቹን ሐለሚክድ ወዮለት!
፮ አዎን፣ የጌታን ራዕይ ለሚክድ፣ እናም ጌታ ከእንግዲህ በራዕይ፣ ወይንም በትንቢት፣ ወይም ሀበስጦታ፣ ወይም በልሳን ወይም በፈውስ፣ ወይንም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አይሰራም ለሚል ለወዮለት!
፯ አዎን፣ እናም በዚያን ቀን ሀጥቅምን ለማግኘት፣ በኢየሱስ ክርስቶስም ከእንግዲህ ለድንቅ ነገር አይሰራም ለሚል ወዮለት፤ ይህንን የሚያደርግ ሐእንደጥፋት ልጅ ይሆናልና፣ ለእርሱም በክርቶስ ቃል መሰረት ምህረት አይኖረውምና!
፰ አዎን፣ እናም ከእንግዲህ ሀልታጉረመርሙ፣ እንዲሁም ለልትወቅሱ፣ ሐአይሁዶችንም ሆነ፣ የእስራኤል ቤት ቅሪት በሆኑት ላይ ትቀልዱም ዘንድ አይገባችሁም፤ እነሆም ጌታ ለእነርሱ የገባውን ቃል ኪዳን ያስታውሳል፣ እናም በመሃላ እንደገባውም ይፈጽምላቸዋል።
፱ ስለዚህ ጌታም ለእስራኤል ቤት የገባውን ቃል ኪዳን ለማሟላት ፍትሁን ለመፈጸም እንዳይችል ቀኝ እጁን ወደግራው ለመመለስ ይቻለናል በማለት መገመት የለባችሁም።