ምዕራፍ ፳፮
ኢየሱስ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻው ያሉትን ነገሮች በሙሉ አብራራ—ህፃናት እንዲሁም ልጆች ሊፃፉ የማይችሉ አስደናቂ ነገሮችን ተናገሩ—በክርስቶስ ቤተክርስቲያን የነበሩት በመካከላቸው ሁሉም ነገሮች በጋራ ነበሩአቸው። ፴፬ ዓ.ም. ገደማ።
፩ እናም እንግዲህ እንዲህ ሆነ ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች በተናገራቸው ጊዜ እነዚህን ለህዝቡ አብራራ፤ እናም ትልቅ እንዲሁም ትንሽ የሆኑትን ሁሉንም ነገሮች አብራራላቸው።
፪ እናም እንዲህ አለ፥ እናንተ የሌላችሁን ሀእነዚህ ቅዱሳን መጽሐፍት አብ እንድሰጣችሁ አዟል፤ ለመጪው ትውልድ መስጠት እንደሚገባቸው የእርሱ ጥበብ ነው።
፫ እናም ከመጀመሪያው ጀምሮ ሀበክብሩ እስከሚመጣ ድረስ ያሉትን ሁሉንም ነገሮች—አዎን፣ በምድር ገፅ ላይ የሚመጡትን ነገሮች ሁሉ፣ የምድር ለማዕድናትም በታላቅ ሙቀት እስከሚቀልጡ ድረስና፣ ምድርም እንደ መጽሐፍ ጥቅልል ሐእስከምትጠቀለል፣ እናም ሰማይና ምድርም እስከሚያልፉ እንኳን አብራራላቸው፤
፬ እናም ሀገር ሁሉ፣ እናም ነገዶች ሁሉ፣ እናም ሁሉም ህዝቦችና ቋንቋ በሙሉ መልካም ይሁኑም መጥፎ፣ እንደስራቸው እንዲፈረድባቸው በእግዚአብሔር ፊት ሀስለሚቆሙበት ለታላቁና በመጨረሻው ቀንም እንኳን—
፭ መልካም ከሆኑም፣ ለዘለዓለማዊው ህይወት ሀትንሳኤ፤ ክፉ ከሆኑም፣ ወደኩነኔም ትንሳኤ፤ ለከአለም በፊት በነበረው ክርስቶስ ምህረትና፣ ሐፍትህ፣ እና ቅድስና መሰረት፣ አንደኛው በአንድ እጅ እናም ሌላኛው በሌላ እጅ በመሆን እነዚህ የተገናኙ ናቸው።
፮ እናም እንግዲህ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ኢየሱስ በእውነት ለህዝቡ ካስተማራቸው ነገሮች ሀአንድ መቶኛው እንኳን ሊፃፍ አልተቻለም፤
፯ ነገር ግን እነሆ ሀየኔፊ ሠሌዳዎች ህዝቡን ስላስተማራቸው ነገሮች በይበልጥ ይዘዋል።
፰ እናም እኔ የጻፍኳቸው እነዚህ ነገሮች፣ እርሱ ካስተማራቸው ነገሮች ጥቂቶች ናቸው፤ እናም እነርሱም ኢየሱስ በተናገራቸው ቃላት መሰረት እነዚህ ለዚህ ህዝብ በድጋሚ ሀከአህዛብ ይመጡ ዘንድ ፅፌአቸዋለሁ።
፱ እናም እምነታቸውን በመጀመሪያ እንዲፈትኑበት ይህን መቀበላቸው አስፈላጊ ስለሆነ፣ ይህን በተቀበሉበት ጊዜ፣ እናም እነዚህን ነገሮች የሚያምኗቸው ከሆነ ከዚያም ሀታላላቅ የሆኑት ነገሮች ይገለፁላቸዋል።
፲ እናም እነዚህን ነገሮች የማያምኑ ከሆኑ፣ ታላላቆቹ ነገሮችም እነርሱን ይኮንኑ ዘንድ ሀአይገለፁላቸውም።
፲፩ እነሆ፣ በኔፊ ሠሌዳዎች ላይ የተፃፉትን ሁሉ ለመፃፍ ተዘጋጅቼ ነበር፣ ነገር ግን ጌታ እንዲህ በማለት ከልክሎኛል፥ የህዝቤን እምነት ሀእፈትናለሁ።
፲፪ ስለዚህ እኔ ሞርሞን፣ በጌታ የታዘዝኩባቸውን ነገሮች እፅፋለሁ። እናም እንግዲህ እኔ ሞርሞን ንግግሬን አበቃለሁ፤ እናም የታዘዝኳቸውን ነገሮች መፃፌን እቀጥላለሁ።
፲፫ ስለዚህ፣ ጌታም ለሶስት ቀናት በእውነት ህዝቡን እንዳስተማረ እንድትመለከቱ እፈልጋለሁ፤ እናም ከዚያ በኋላ በተደጋጋሚ ራሱን ሀአሳይቷቸዋል፣ እናም በተደጋጋሚም ለዳቦ በመቁረስ ባርኮ ሰጥቷቸዋል።
፲፬ እናም እንዲህ ሆነ የተነገረላቸውን ሰዎች ሀልጆችም ኢየሱስ አስተማራቸውና አገለገላቸው፣ እናም አንደበታቸውን ፈታላቸውና፣ ለህዝቡ እርሱ ከገለፀላቸው የበለጡትን ለአባቶቻቸው ታላቅና አስገራሚ የሆኑ ነገሮችን ተናገሩ፤ እናም ለመናገር እንዲችሉም አንደበታቸውን ለፈታላቸው።
፲፭ እናም እንዲህ ሆነ ወደ ሰማይም ካረገ በኋላ—ለሁለተኛ ጊዜ እራሱን ገለፀላቸው፣ እናም በሽተኞቻቸውንና ሽባዎችን በሙሉ ሀከፈወሰና፣ የዕውሮችን ዐይን ካበራ፣ እናም የደንቆሮን ጆሮዎች ከከፈተና፣ ሁሉንም ዐይነት ፈውሶች በመካከላቸው ካደረገ በኋላ፣ እናም አንድን ሰው ከሞት ካስነሳና ኃይሉንም ካሳያቸው በኋላ ወደአብ ሄደ—
፲፮ እነሆ፣ እንዲህ ሆነ በሚቀጥለው ቀን ህዝቡ በአንድ ላይ ተሰበሰበ፣ እናም እነዚህን ልጆች ተመለከቱአቸውና፣ አዳመጡአቸው፤ አዎን፣ ሀህፃናቱም አፋቸውን ከፈቱና፣ አስደናቂ ነገሮችን ተናገሩ፤ እናም የተናገሩአቸውን ነገሮች ማንም እንዳይፅፍ ተከልክሏል።
፲፯ እናም እንዲህ ሆነ ኢየሱስ የመረጣቸው ሀደቀመዛሙርት ከዚያን ጊዜ በኋላ ወደ እነርሱ የመጡትን ሰዎች ሁሉ ማጥመቅና ማስተማር ጀመሩ፤ እናም በኢየሱስ ስም ለየተጠመቁት ሰዎች በሙሉ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ነበር።
፲፰ እናም ብዙዎች ሊፃፉ ሀበህግ ያልተፈቀዱትን፣ ሊነገሩ የማይችሉ ነገሮችን ተመልክተዋልም፣ ሰምተዋልም።
፲፱ እናም አንዳቸው ሌላኛውን አገለገሉና፣ አስተማሩ፤ እንዲሁም እያንዳንዱ ሰውም እርስ በርሱ በፍትህ በማገልገል፣ በመካከላቸው ሀሁሉም ነገሮች ለበጋራ ነበሩአቸው።
፳ እናም እንዲህ ሆነ ኢየሱስ እንዳዘዛቸው ሁሉንም ነገሮች አደረጉ።
፳፩ እናም በኢየሱስ ስም የተጠመቁት ሀየክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተብለው ይጠሩ ነበር።