ምዕራፍ ፬
ሽማግሌዎች እና ካህናት የቅዱስ ቁርባንን ዳቦ እንዴት እንደሚባርኩት ተገልጿል። ፬፻–፬፻፳፩ ዓ.ም. ገደማ።
፩ ሀሽማግሌዎቻቸው እናም ካህናቶቻቸው የክርስቶስን ስጋና ደም ለቤተክርስቲያን በመባረክ የሚያስተላልፉት ለስርዓት፤ እናም በረከቱንም ሐየሚያደርጉት እንደ ክርስቶስ ትዕዛዝ ነው፣ ስለዚህ ስርዓቱም ትክክል እንደሆነም እናውቃለን፤ እናም ሽማግሌው ወይም ካህኑ ይባርኩታል—
፪ እናም ከቤተክርስቲያኗ አባላትም ጋር ይንበረከካሉ፣ እናም በክርስቶስ ስምም እንዲህ ሲሉ ወደ አብ ይፀልያሉ፥
፫ አቤቱ ዘለዓለማዊ አባት እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህንን ሀዳቦ ለሚቋደሱት ነፍሳት ሁሉ የልጅህን አካል ለበማስታወስ እንዲበሉት እና፣ አቤቱ ዘለዓለማዊ አባት እግዚአብሔር ሆይ፣ እነርሱ ሐየልጅህን ስም በላያቸው ላይ ለመውሰድ ፈቃደኞች መሆናቸውን፣ እና ሁልጊዜ እርሱን እንደሚያስታውሱና እርሱ የሰጣቸውን ትእዛዛት እንደሚጠብቁ ለአንተም ይመሰክሩ ዘንድ፣ በዚህም የእርሱ መመንፈስ ሁልጊዜ እንዲኖራቸው ትባርከውና ትቀድሰው ዘንድ በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጠይቅሃለን። አሜን።