ምዕራፍ ፰
ህጻናትን ማጥመቅ የከፋ ርኩሰት ነው—ህፃናት በክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካይነት ህያው ናቸው—እምነት፤ ንሰሃ፤ የዋህነት እናም የልብ ርህራሄ፤ መንፈስ ቅዱስን መቀበል፣ እና እስከ መጨረሻው ፅኑ መሆን ወደ ደህንነት ይመራል። ፬፻፩–፬፻፳፩ ዓ.ም. ገደማ።
፩ ሀአባቴ ሞርሞን ለእኔ ለሞሮኒ የፃፈልኝ ደብዳቤ፤ እናም የተፃፈልኝ ወዲያው ለአገልግሎት ከተጠራሁ በኋላ ነበር። እናም በዚህም ሁኔታ እንዲህ ሲል ነበር የፃፈልኝ፥
፪ የተወደድክ ልጄ ሞሮኒ፣ ጌታህ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለአንተ ስለሚያስብልህ እናም ለአገልግሎት እናም ለቅዱሱ ስራው ስለጠራህ እጅግ ተደስቻለሁ።
፫ እናም በቅዱሱ ልጁ በኢየሱስ ስም ወደ እግዚአብሔር አብ ያለማቋረጥ በመፀለይ፣ እርሱም ወደር በሌለው ሀቸርነቱ እንዲሁም ለፀጋው እስከመጨረሻው በእምነት የፀናህ እንድትሆን ይጠብቅህ ዘንድ፣ ሁል ጊዜ በፀሎቴ ስለአንተ አስባለሁ።
፬ እናም እንግዲህ፣ ልጄ እጅግ ያሳዘነኝን ነገር በተመለከተ እነግርሃለሁ፤ በመካከላችሁ ሀክርክር በመነሳቱ እኔን አሳዝኖኛል።
፭ እውነቱን እንደተረዳሁት ከሆነ፣ የህጻናትን ጥምቀት በሚመለከት በመካከላችሁ ክርክር ነበር።
፮ እናም እንግዲህ፣ ልጄ ይህ ታላቅ ስህተትም ከመካከላችሁ እንዲወገድ ተግተህ እንድትሰራ እፈልጋለሁ፤ ለዚህ ስልም ይህንን ደብዳቤ ፃፍኩልህ።
፯ ስለእነዚህን ነገሮች ካንተ ካወቅሁኝ በኋላ ሁኔታውን በሚመለከት ጌታን ወዲያው ጠየቅኩኝ። እናም የጌታ ሀቃልም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንዲህ ሲል መጣልኝ፥
፰ የአዳኝህን፣ የጌታህን እናም የአምላክህን የክርስቶስን ቃል አድምጥ። እነሆ፣ ወደ ዓለም የመጣሁት ፃድቃንን ሳይሆን ኃጢአተኞችን ንሰሃ እንዲገቡ ልጠራ ነው፤ ሕመምተኞች እንጂ ሀብርቱዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤ ስለሆነም፣ ለህፃናት ሐፍፁማን ናቸው፤ መኃጢያትንም ለመፈፀም አይችሉምና፤ ስለሆነም፣ ሠየአዳም እርግማን ከእነርሱ በእኔ ተወስዷል፤ በእነርሱ ላይ ምንም ኃይል የለውም፤ ረየግርዘት ህግም በእኔ ተሽሯል።
፱ እናም በዚህ ሁኔታ ነው መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ቃል የገለጠልኝ፤ ስለሆነም፣ የተወደድክ ልጄ፣ ህፃናትን ማጥመቅህ በእግዚአብሔር ፊት ከባድ ፌዝ መሆኑን አውቃለሁ።
፲ እነሆ ይህንን ነገር እንድታስተምር እልሃለሁ—ንስሀ መግባትን እና ጥምቀትን ሀተጠያቂ ለሆኑት እና ኃጢያትን ለሚፈጽሙት፤ አዎን፣ ወላጆች ንሰሃ መግባት እናም መጠመቅ እንዳለባቸው፣ እናም እንደ ለህፃናቱ ልጆቻቸው እራሳቸውን የዋህ እንዲያደርጉ አስተምራቸው፣ እናም ሁሉም ከህፃናት ከልጆቻቸው ጋር ይድናሉ።
፲፩ እናም ሀህፃናት ልጆቻቸው ጥምቀትም ሆነ ንሰሃ አያስፈልጋቸውም። እነሆ ለንሰሃ መጠመቅ ትዕዛዙን ለመፈፀም እናም ለኃጢያት ለስርየት ነው።
፲፪ ነገር ግን ሀህፃናት ልጆች በክርስቶስ ከዓለም መፈጠር ጀምሮም ህያው ናቸው፤ ይህ ባይሆን ኖሮ፣ እግዚአብሔር ፍትህ የሌለው እናም ደግሞ የሚለወጥ አምላክ እናም ለሰዎች ለየሚያደላ ነው፤ ምን ያህል ህፃናትስ ጥምቀትን ሳያገኙ ሞተዋልና!
፲፫ ስለዚህ፣ ህፃናት ያለጥምቀት መዳን ባይቻላቸው ኖሮ እነዚህም መጨረሻ ወደሌለው ገሃነም ይሄዱ ነበር።
፲፬ እነሆ እንዲህ እልሀለሁ፤ ህፃናት መጠመቅ እንዳለባቸው የሚገምት እርሱ በመራራው መርዝ እናም በክፋት ሰንሰለት ውስጥ ነው፤ ምክንያቱም እርሱ ሀእምነት፣ ተስፋም ሆነ ልግስና የለውምና፣ ስለዚህ፣ ይህንን እያሰበ ከሞተም፣ እርሱ ወደ ሲኦል መውረድ አለበት።
፲፭ እግዚአብሔር በጥምቀት አንድን ልጅ ያድናል፤ እናም ያልተጠመቁት ሌሎቹ ግን ይጠፋሉ ብሎ ማሰብ የከፋ ኃጢያት ነው።
፲፮ በዚህ ሁኔታ የጌታን መንገድ ለሚበክሉት ወዮላቸው፤ ምክንያቱም እነርሱ ንሰሃ ካልገቡ ይጠፋሉና። እነሆ፣ ከእግዚአብሔር ሀስልጣን ስለተሰጠኝ በድፍረት እናገራለሁ፤ እናም ሰው ለማድረግ የሚችለውን አልፈራም፤ ምክንያቱም ፍፁም የሆነ ለፍቅር ፍርሃትን ሁሉ ሐአውጥቶ ይጥላልና።
፲፯ እናም እኔ ዘለዓለማዊ ፍቅር በሆነው ሀልግስና ተሞልቻለሁ፤ ስለሆነም፣ ህፃናት ሁሉ ለእኔ የሚመሳሰሉ ናቸው፤ ስለሆነም፣ ለህፃናትን ፍፁም በሆነ ፍቅር እወዳቸዋለሁ፤ እናም ሁሉም ተመሳሳይ ናቸው እናም ከደህንነቱም ተካፋዮች ናቸው።
፲፰ እግዚአብሔር የማያዳላ እናም ሀየማይለወጥ አምላክ እንደሆነ አውቃለሁ፤ ነገር ግን እርሱ ከዘለዓለም እስከዘለዓለም ለበሙሉ አይለወጥም።
፲፱ ሀህፃናት ንሰሃ ለመግባት አይችሉም፤ ስለሆነም፣ ለእነርሱ ንፁህ የሆነውን የእግዚአብሔርን ምህረት መካድ የከፋ ኃጢያት ነው፤ ምክንያቱም ለበምህረቱ ሁሉም ህያው ሆነዋልና።
፳ እናም ህፃናት መጠመቅ አለባቸው የሚል የክርስቶስን ሀየኃጢያት ክፍያ የካደ ነው፣ እናም የእርሱን የኃጢያት ክፍያ እናም የቤዛነቱን ኃይል እንደምንም ንቀውታል።
፳፩ እነርሱም በሞት፣ ሀበሲኦል፣ እናም ለመጨረሻ በሌለው ቅጣት አደጋ ላይ በመሆናቸው ወዮላቸው። በድፍረት እናገራለሁ፤ እግዚአብሔርም አዞኛል። እነርሱን ስሙ እናም አድምጡ፣ አለበለዚያ በክርስቶስ ሐየፍርድ ወንበር ፊት በእናንተ ላይ ለምስክር ይቆማሉና።
፳፪ እነሆ ህፃናት በሙሉ፣ እናም ደግሞ ህጉ የሌላቸው ሁሉ በክርስቶስ ሀህያው ናቸውና። ምክንያቱም ለየቤዛነት ኃይል ሐህጉ ለሌላቸው ሁሉ ይመጣልና፤ ስለሆነም ያልተኮነነ ወይንም ኩነኔ የሌለበት ንሰሃ ለመግባት አይችልም፤ እናም ለእንደዚህ አይነቱ ሰው ጥምቀት ምንም ጥቅም የለውም—
፳፫ ነገር ግን ይህ በእግዚአብሔር ፊት መሳለቅ፣ የክርስቶስን ምህረት እናም የመንፈስ ቅዱሱን ኃይል መካድ፣ እናም ሀበሞተ ስራ ላይ ተስፋ ማድረግ ነው።
፳፬ እነሆ ልጄ ይህ ነገር መሆን የለበትም፤ ምክንያቱም ሀንሰሃ የሚያስፈልገው በኩነኔ እናም በተጣሰው ህግ እርግማን ሥር ላሉት ነውና።
፳፭ እናም ሀየንሰሃ የመጀመሪያው ፍሬ ለጥምቀት ነው፤ እናም ጥምቀት የሚመጣው በእምነት ትዕዛዙን በመፈፀም ነው፤ እናም ትዕዛዙን መፈፀም የኃጢያት ሐስርየትን ያመጣል፤
፳፮ እናም የኃጢያት ስርየት ሀየዋህነትን፣ እና የልብ ርህራሄን ያመጣል፤ እናም የዋህነት እናም የልብ ርህራሄ ለበመንፈስ ቅዱስ መጎብኘትን ያመጣል፤ ይህም ሐአፅናኝ መበተስፋ እናም ሠበፍፁም ፍቅር ይሞላል፣ ይህም ፍቅር ረቅዱሳን በሙሉ ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖሩበት መጨረሻው እስከሚመጣ ሰበትጋት ሸበመፀለይ ይጸናል።
፳፯ እነሆ፣ ልጄ፣ ከላማናውያን ጋር ለመዋጋት ወዲያው ካልሄድኩ በድጋሚ እፅፍልሃለሁ። እነሆ፣ የዚህ ሀገር ወይም የኔፋውያን ሀኩራት፣ ንሰሃ ካልገቡ በቀር እንደሚጠፉ አረጋግጦአል።
፳፰ ልጄ ንሰሃ ይመጣላቸው ዘንድ ለእነርሱ ፀልይላቸው። ነገር ግን እነሆ፣ መንፈስ ከእነርሱ ጋር መስራቱን ሀእንዳያቆም እፈራለሁ፤ እናም በዚህች ምድርም ደግሞ ሁሉንም ከእግዚአብሔር የመጣውን ኃይልና ስልጣን ለማናናቅ ይፈልጋሉ፤ እናም እነርሱም መንፈስ ቅዱስን ለክደዋል።
፳፱ እናም ልጄ፣ ታላቁን እውቀት አንቀበልም ካሉ በኋላ፣ እነርሱ በነቢያት የተነገሩትን ትንቢቶች፣ እናም ደግሞ በአዳኛችን በራሱ የተነገሩትን ቃላት ይፈፅሙ ዘንድ በፍጥነት መጥፋት አለባቸው።
፴ ልጄ እስከምፅፍልህ ወይንም በድጋሚ እስከማገኝህ ድረስ ደህና ሁን። አሜን።