ቅዱሳት መጻህፍት
ሞሮኒ ፩


መፅሐፈ ሞሮኒ

ምዕራፍ ፩

ሞሮኒ ለላማናውያን ጥቅም ፃፈ—ክርስቶስን ያልካዱ ኔፋውያን ተገደሉ። ፬፻፩–፬፻፳፩ ዓ.ም. ገደማ።

እንግዲህ እኔ ሞሮኒ፣ የያሬዳውያንን ሰዎች ታሪክ አሳጥሮ መጻፉን ከጨረስኩ በኋላ፣ ከዚህ የበለጠ እፅፋለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር፤ ነገር ግን እስካሁንም አልጠፋሁም፤ እናም ላማናውያን ያጠፉኛል ብዬ በመፍራቴ ራሴን አላሳወቅሁም።

እነሆም፣ በመካከላቸው ያሉት ጦርነቶችም እጅግ ኃይለኛ ናቸው፤ እናም በጥላቻቸው ምክንያትም ክርስቶስን የማይክዱትን ኔፋውያን እያንዳንዳቸውን ይገድላሉ

እናም እኔ፣ ሞሮኒ፣ ክርስቶስን አልክደውም፤ ስለዚህ ለህይወቴ ደህንነትም ስል በምችለው ቦታ ሁሉ እዘዋወራለሁ።

ስለዚህ ከገመትኩት ተቃራኒ የሆኑ ጥቂት ነገሮችን እፅፋለሁ፤ ከዚህ የበለጠ እንድፅፍ አልጠብቅም ነበርና፤ ነገር ግን በጌታ ፈቃድ ወደፊት አንድ ቀን ለወንድሞቼ ለላማናውያን ምናልባት ይጠቅማቸው ዘንድ ከዚህ የበለጠ ጥቂት ነገሮችን እጽፋለሁ።