ቅዱሳት መጻህፍት
ሞሮኒ ፱


ሞርሞን ለልጁ ሞሮኒ የፃፈው ሁለተኛው ደብዳቤ።

ምዕራፍ ፱ አጠቃሎ የያዘ።

ምዕራፍ ፱

ኔፋውያን እናም ላማናውያን ነውረኛ እና የረከሱ ናቸው—እነርሱም እርስ በርሳቸው ስቃይን እናም ግድያን ይፈፅማሉ—ሞርሞንም ፀጋ እና ቸርነት ለዘለዓለም በሞሮኒ ላይ እንዲሆን ፀለየ። ፬፻፩ ዓ.ም. ገደማ።

የተወደድክ ልጄ እስካሁን በህይወት ያለሁ መሆኔን ታውቅ ዘንድ በድጋሚ ይህንን ፃፍኩልህ፤ ነገር ግን አሳዛኝ ስለሆነው ነገር በመጠኑ እፅፋለሁ።

እነሆም፣ ከላማናውያን ጋር ድልን ያላገኘንበት አሰቃቂ የሆነ ውጊያ አድርጌ ነበር፤ እናም አርኬአንቱስ፣ ደግሞም ሉራም፣ እና ኤምሮን በጎራዴው ወደቁ፤ አዎን፣ እናም በርካታ የተመረጡ ጀግኖቻችንን አጥተናል።

እናም እንግዲህ እነሆ ልጄ፣ ላማናውያን እነዚህን ሰዎች ያጠፉአቸዋል ብዬ እፈራለሁ፤ ምክንያቱም እነርሱ ንሰሀ አልገቡም እናም ሰይጣንም ዘወትር እርስ በእርሳቸው እንዲበጣበጡ እያደረጋቸው ነውና።

እነሆ፣ እኔም ያለማቋረጥ ከእነርሱ ጋር እየሰራሁ ነኝ፣ የእግዚአብሔርንም ቃል በኃይለ ቃል ስናገር እነርሱ ይንቀጠቀጣሉ እናም ይቆጡኛል፤ እናም በኃይለ ቃል ባልተናገርኳቸውም ጊዜ በቃሉ ላይ ልባቸውን ያጠጥራሉ፤ ስለሆነም የጌታ መንፈስ ከእነርሱ ጋር መሆኑን ያቆማል ብዬ እፈራለሁ።

እነርሱም እጅግ በኃይል ተቆጥተው ስለነበር ሞትንም ቢሆን የማይፈሩ መስለውኛል፤ እርስ በርሳቸውም የነበራቸውን ፍቅር አጥተዋል፤ እናም ለፀብና ያለማቋረጥ ለመበቀል ጥማት አላቸው።

እናም እንግዲህ፣ የተወደድክ ልጄ፣ እነርሱ ልባቸውን ቢያጠጥሩም እኛ ተግተን እንስራ፤ መስራት ካቆምን እንኮነናለንና፤ የፅድቅ ጠላት የሆነውን ሁሉ እናሸንፍ ዘንድ፣ እናም ነፍሳችንን በእግዚአብሔር መንግስት እናሳርፍ ዘንድ፣ በዚህ በጭቃ ሰውነታችን የምናከናውነው ስራ አለንና።

እናም አሁን ስለዚህ ህዝብ ስቃይ በመጠኑ እፅፋለሁ። ከአሞሮን ባገኘሁት እውቀት መሠረት እነሆ፣ ላማናውያን ከሼሪዛ ግንብ የወሰዱአቸው ብዙ እስረኞች አሉአቸው፤ ወንዶችም፣ እናም ሴቶችም፣ እናም ልጆችም ነበሩ።

እናም የእነዚህ ሴቶችና የልጆቹ ባሎችንና አባቶች ተገድለዋል፤ እናም ሴቶችን የባሎቻቸውን ስጋ እንዲበሉ እናም ልጆችም የአባቶቻቸውን ስጋ እንዲበሉ አደረጉአቸው፤ እናም ከጥቂት በስተቀር ምንም ውኃ አይሰጡአቸውም ነበር።

እናም ላማናውያን ይህ ታላቅ እርኩሰት ቢኖርባቸውም በሞሪያንቱም ካሉት ከኛ ህዝብ ጥፋት አይበልጥም። እነሆ ብዙ የላማናውያን ሴት ልጆችም በምርኮ ወስደው ነበርና፤ እናም ከሁሉም ነገሮች በላይ የተወደሰ እና የተከበረ፣ እንዲሁም ድንግልነታቸውን እና ምግባረ ጥሩነታቸው ከወሰዱባቸው በኋላ—

እናም ይህን ካደረጉ በኋላ፣ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ገደሉአቸው፤ ሰውነታቸውንም እስከሚሞቱ አሰቃዩአቸው፤ እናም ይህንን ካደረጉ በኋላ፣ ልባቸው ጠጣር በመሆኑ እንደዱር አውሬ ስጋቸውን በጨቁአቸው፤ እናም ይህንንም ያደረጉት ጀግንነታቸውን ለማሳየት ነበር።

፲፩ አቤቱ የተወደድክ ልጄ፣ እንደዚህ አይነቶቹ ሰዎች እንዴት ያልሰለጠኑ ሊሆኑ ተቻላቸው—

፲፪ (እናም ደግሞ ጥቂት ዓመታት አለፉ፣ እናም ሰዎቹም የሰለጠኑ እናም መልካም ሰዎች ነበሩ)

፲፫ ነገር ግን አቤቱ ልጄ ከእንደዚህ ዓይነት ህዝብ ደስታ እንዴት በእርኩስነት ሊገኝ ይችላል—

፲፬ እግዚአብሔርስ እጆቹን በፍርድ ከእኛ ላይ አያነሳም ብለን እንዴት እንጠብቃለን?

፲፭ እነሆ፣ ልቤ፥ ለዚህ ህዝብ ወዮለት ብላ ታለቅሳለች። አቤቱ እግዚአብሔር ቅጣትህን ፈፅም እናም ኃጢአታቸውን እናም እርኩሰቶቻቸውን ከፊትህ ደብቅላቸው!

፲፮ እናም በድጋሚ ልጄ፣ በሼሪዛ የቀሩ ብዙ ባልቴቶች እና ሴት ልጆቻቸው አሉ፤ እናም እነዚያን ላማናውያን ያልወሰዷቸውን ስንቆች፤ እነሆ፣ የዜኔፊ ወታደሮችም ወሰዱአቸው እናም በየደረሱበት ስፍራም ምግብ ፈልገው እንዳያገኙ ተዉአቸው፤ እናም በጉዞአቸውም ብዙ አረጋውያን ሴቶች እራሳቸውን ሳቱ እናም ሞቱ።

፲፯ እናም ከእኔም ጋር የነበሩት ወታደሮች ደካሞች ናቸው፤ እናም የላማናውያን ወታደሮች በሼሪዝ እና በእኔ መካከል ናቸው፤ ወደ አሮን ወታደር የሸሹት በሙሉ በእነርሱ ጨካኝነት ወድቀዋል።

፲፰ አቤቱ የህዝቤ ጥፋት እንዴት ይገርማል! እነርሱም ምህረትም ሆነ ስርዓት የላቸውም። እነሆ፣ ነገር ግን እኔ ወንድ ነኝ፣ እናም የወንድ ጥንካሬም ብቻ ነው ያለኝ፣ እናም ከዚህ በኋላም ትዕዛዜን እንዲቀበሉ ላስገድዳቸው አልችልም።

፲፱ እናም በብልግናቸው ጠንካሮች ሆኑ፤ እናም በሁሉም ነገር ጨካኝ በመሆናቸው ህፃናትንም ሆነ ሽማግሌዎችን አላስተረፉም፤ መልካም ከሆነው በስተቀር በሁሉም ነገር ይደሰታሉ፤ እናም የሴቶቻችን እናም የልጆቻችን ስቃይ በምድር ገፅታ ላይ ከነበረው ከማንኛውም የበለጠ ነው፤ አዎን፣ በአንደበት ለመናገርም ሆነ ለመፃፍ የሚቻል አይደለም።

እናም እንግዲህ ልጄ፣ በዚህ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ከዚህ በላይ አልቆይም። እነሆ፣ አንተ የህዝብህን ኃጢያት ታውቃለህ፤ እነርሱም መሰረታዊ መርሆች እንደሌላቸው እናም ስሜት እንደሌላቸው ታውቃለህ፤ እናም ክፋቶቻቸውም ከላማናውያን በላይ ናቸው።

፳፩ እነሆ ልጄ፣ እግዚአብሔርም ይመታኛል ብዬ በመፍራቴ እነርሱን ብቁ ናቸው ብዬ ለመመስከር አልችልም።

፳፪ ነገር ግን እነሆ፣ ልጄ፣ ለእግዚአብሔር ስለአንተ እመሰክራለሁ፣ እናም አንተም እንደምትድን በክርስቶስ እምነት አለኝ፤ እናም ህዝቡም ወደ እርሱ ሲመለሱ ወይንም ፈፅመው ሲጠፉ እንድትመሰክር እግዚአብሔርም ህይወትህን እንዲያተርፍ እፀልያለሁ፣ ንስሀ ካልገቡ እና ወደ እርሱ ካልተመለሱ መጥፋት እንዳለባቸው አውቃለሁና።

፳፫ እናም በልቦቻቸው ሙሉ ፈቃድ፣ ደም እና በቀል በመሻታቸው፣ ከጠፉ ጥፋታቸው እንደ ያሬዳውያን ይሆናል።

፳፬ እናም የሚጠፉም ከሆነ፣ ብዙ ወንድሞቻችን ከላማናውያን ጋር ለመቀላቀል እንደሔዱ እናም ከዚህም ደግሞ የበለጡ ብዙዎች እንደሚሄዱ እናውቃለን፤ ስለሆነም፣ አንተ ከተረፍክ እናም እኔ ከጠፋሁ እናም አንተን ካላየሁ ነገሮችን በመጠኑ ጻፍ፤ ነገር ግን ለአንተ የምሰጥህ ቅዱስ መዛግብት ስላሉኝ በቅርቡ እንደማይህ ተስፋ አለኝ።

፳፭ ልጄ በክርስቶስ የታመንክ ሁን፤ እናም የፃፍኳቸውም ነገሮች አንተን ለሞት እስከሚያደርሱ አያሳዝኑህ፤ ነገር ግን ክርስቶስ ከፍ ያድርግህ፣ እናም ስቃዩ፣ እናም ሞቱ፣ እናም ሰውነቱን ለአባታችን ማሳየቱ፣ እናም ምህረቱ እናም ፅናቱ፣ እናም ለክብሩ እናም ለዘለዓለማዊ ህይወት ያለው ተስፋ ለዘለዓለም በአዕምሮህ ይኑር።

፳፮ እናም በሰማያት ዙፋኑ ከፍ ያለው የእግዚአብሔር አብ፣ እናም ሁሉም ነገር በእርሱ የሚገዙ እስከሚሆን ድረስ በኃይሉ በቀኝ እጅ በኩል የተቀመጠው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ ለዘለዓለም ከአንተ ጋር ይሁን እናም ይኑር። አሜን።