ቅዱሳት መጻህፍት
ሞሮኒ ፪


ምዕራፍ ፪

ኢየሱስም ኔፋውያን ደቀመዛሙርት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን እንዲሰጡ ስልጣንን ሰጣቸው። ፬፻፩–፬፻፳፩ ዓ.ም. ገደማ።

ክርስቶስ ለመረጣቸው አስራ ሁለቱ ደቀመዛሙርት እጁን በመጫን የተናገራቸው ቃላት—

እናም በስማቸውም በመጥራት እንዲህ አላቸው፥ በብርቱ ፀሎት አብን በስሜ ጥሩት፤ እናም ይህንንም ካደረጋችሁ በኋላ እጃችሁን በምትጭኑበት ላይ መንፈስ ቅዱስን ለመስጠት ስልጣን ይኖራችኋል፤ እናም በስሜም ትሰጡታላችሁ፤ ይህንንም ሐዋሪያቶቼ ያደርጉታልና።

እንግዲህ ክርስቶስ በመጀመሪያም እራሱን ለእነርሱ ሲገልፅ እነዚህን ቃላት ተናግሯል፤ እናም ህዝቡም አላዳመጡም፤ ነገር ግን ደቀመዛሙርቱ አዳምጠውታል፤ እናም እጃቸውን በጫኑባቸው በሙሉ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው።