መታመን ደግሞም ልበ ሙሉነት; እምነት፣ ማመን ተመልከቱ በአንድ ሰው ወይም በአንድ ነገር ላይ መመካት ወይም እምነትን መጣል። በመንፈሳዊ ነገሮች፣ ማመን በእግዚአብሔር እና በመንፈሱ መመካት ነው። ቢገድለኝ ስንኳ እርሱን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ, ኢዮብ ፲፫፥፲፭. በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን, ምሳ. ፫፥፭. እግዚአብሔር በእርሱ የሚያምኑትን አገልጋዮች አዳነ, ዳን. ፫፥፲፱–፳፰. ለዘለዓለም በአንተ እታመናለሁ, ፪ ኔፊ ፬፥፴፬. ተደሰቱ፣ እናም በእግዚአብሔር እምነታችሁን አድርጉ, ሞዛያ ፯፥፲፱. እምነቱን በእርሱ ያደረገ በመጨረሻው ቀን ከፍ ይላል, ሞዛያ ፳፫፥፳፪. እምነታቸውን በእግዚአብሔር ላይ ያደረጉ ሁሉ፣ በፈተናቸውይደገፋሉ, አልማ ፴፮፥፫፣ ፳፯. በስጋ ክንድ አትመካ, ት. እና ቃ. ፩፥፲፱. ወደ መልካም በሚመራው መንፈስ ላይ እምነትህን አድርግ, ት. እና ቃ. ፲፩፥፲፪. በእኔ ይመን እናም ግራ አይጋባ, ት. እና ቃ. ፹፬፥፻፲፮.