ቅድመ ምድራዊ ህይወት ደግሞም መጀመሪያ; ሰው፣ ሰዎች; የሰማይ ሸንጎ; የሰማይ ጦርነት ተመልከቱ ከምድር ህይወት በፊት የነበረ ህይወት። ወንዶች እና ሴቶች ወደ ምድር እንደ ስጋዊ ፍጥረቶች እስከሚመጡ ድረስ ከእግዚአብሔር ጋር እንደ መንፈስ ልጆቹ ኖሩ። ይህም አንዳንድ ጊዜ የመጀመሪያው ሁኔታ ተብሎ ይጠራል (አብር. ፫፥፳፮)። እግዚአብሔር የምድርን መሰረት ሲመሰርት፣ የእግዚአብሔር ልጆች በደስታ ጮሁ, ኢዮብ ፴፰፥፬–፯. ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ይመለሳል, መክ. ፲፪፥፯. በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ, ኤር. ፩፥፬–፭. እኛ ደግሞ ዘመዶቹ ነን, የሐዋ. ፲፯፥፳፰. ዓለም ሳይፈጠር በፊቱ መረጠን, ኤፌ. ፩፥፫–፬. ለመናፍስት አባት እንገዛ, ዕብ. ፲፪፥፱. የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘላለም እስራት ከጨለማ, ይሁዳ ፩፥፮ (አብር. ፫፥፳፮). ዲያብሎስ መላእክቱ ከእርሱ ጋር ተጣሉ, ራዕ. ፲፪፥፱. ከዓለም መፈጠር ጀምሮ ተጠርተዋል፣ እናም ተዘጋጅተዋል, አልማ ፲፫፥፫. ክርስቶስ አለም ከመፈጠሩ በፊት የሰፊና ገላጣ ቦታ ዘላለማዊነትን እና ሁሉን የሰማይ ሱራፌላዊ ሰራዊቶች ተመለከተ, ት. እና ቃ. ፴፰፥፩. ሰው ደግሞ በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋር ነበር, ት. እና ቃ. ፺፫፥፳፱ (ሔለ. ፲፬፥፲፯; ት. እና ቃ. ፵፱፥፲፯). ልዑል ነፍሳት የቤተክርስቲያኗ መሪ እንዲሆኑ ከመጀመሪያው ጀምሮ ተመርጠው ነበር, ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፶፫–፶፭. ብዙዎቹ የመጀመሪያ ትምህርታቸውን በመንፈሶች አለም ውስጥ ተቀበሉ, ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፶፮. ሁሉም ነገሮች በምድር ከመፈጠራቸው በፊት በምንፈስ ተፈጥረው ነበር, ሙሴ ፫፥፭. አለምን፣ እና ስጋ ከማግኘታቸው በፊት፣ ሰዎችን የፈጠርኩኝ ነኝ, ሙሴ ፮፥፶፩. አብርሐም እውቀተኛዎች አለም ከመፈጠሩ በፊት እንደተደራጁ አየ, አብር. ፫፥፳፩–፳፬.