ክፍል ፻፴፰
በጥቅምት ፫፣ ፲፱፻፲፰ (እ.አ.አ.) በሶልት ሌክ ስቲ፣ ዩታ ውስጥ ለፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። በጥቅምት ፬፣ ፲፱፻፲፰ (እ.አ.አ.) በ፹፱ነኛው የቤተክርስቲያኗ የግማሽ አመት አጠቃላይ ጉባኤ መክፈቻ ንግግራቸው ላይ፣ ፕሬዘደንት ስሚዝ ባለፉት ወራት የተለያዩ መለኮታዊ መልእክቶችን እንደተቀበሉ ገለጹ። ፕሬዘደንት ስሚዝ ባለፈው ቀን ከተቀበሏቸው ከእነዚህ አንዱ አዳኝ ሰውነቱ በመቃብር ውስጥ እያለ የሙታንን መንፈስ መጎብኘቱን በሚመለከት ነበር። በጉባኤው መዝጊያ ወዲያውም ተፅፎ ነበር። በጥቅምት ፴፩፣ ፲፰፻፲፰ (እ.አ.አ.) ይህም ለቀዳሚ አመራር አማካሪዎች፣ ለአስራ ሑለቱ ቡድን፣ እና ለፔትሪያርክ ቀረበ፣ እና እነርሱም በአንድ ድምፅ ተቀብለውት ነበር።
፩–፲፣ ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ ስለ ጴጥሮስ ፅሁፎች እና ጌታ የመንፈስ አለምን ስለመጎብኘቱ ያሰላስሉ ነበር፤ ፲፩–፳፬፣ ፕሬዘደንት ስሚዝ የሞቱት ጻድቃን በገነት ውስጥ ተሰብስበው እና ክርስቶስም በመካከላቸው ያገለገለበትን አዩ፤ ፳፭–፴፯፣ በመናፍስትም መካከል ወንጌልን ለመስበክ እንዴት እንደተደራጀም ተመለከቱ፤ ፴፰–፶፪፣ ከሞት ከመነሳታቸው በፊት የመንፈስ ሁኔታቸውን እንደ ባርነት የሚመለከቱትን አዳምን፣ ሔዋንን፣ እና ብዙ ቅዱሳን ነቢያትን በመንፈስ አለም ውስጥ አዩአቸው፤ ፶፫–፷፣ ዛሬ በፅድቅ የሚሞቱ በመንፈስ አለም ውስጥ አገልግሎታቸውን ይቀጥላሉ።
፩ በጥቅምት ሶስተኛው ቀን፣ በአስራ ዘጠኝ መቶ አስራ ስምንት አመተ ምህረት ውስጥ፣ ቅዱሳን መጻህፍትን በክፍሌ ቁጭ ብዬ ሀአሰላስል ነበር፤
፪ እና ለአለም ሀቤዛነት፣ የእግዚአብሔር ልጅ ያደረገውን ታላቅ ለየኃጢአት ክፍያ እያሰብኩ ነበር፤
፫ እና ሀየቤዛው ወደአለም መምጣት አብ እና ወልድ ያሳዩትን ታላቅ እና አስደናቂ ለፍቅርም፤
፬ በእርሱ ሀየኃጢአት ክፍያ፣ እና በወንጌሉ መሰረታዊ መርሆች ለታዛዥነት፣ የሰው ዘር ይድን ዘንድ እንደ ሆነ አሰላስል ነበር።
፭ በዚህ ተይዤ እያለሁ፣ ከጌታ መሰቀል በኋላ ወንጌሉ ተሰብኮላቸው ለነበሩት ሀበጳንጦስ፣ በገላትያ፣ በቀጰዶቅያም፣ እና በሌሎች የእስያ ክፍሎች ውስጥ ለተበተኑት ለየጥንት ቅዱሳን ሐዋሪያው ጴጥሮስ ወደጻፈው አዕምሮዬ ተመለሰ።
፮ መፅሐፍ ቅዱስን ከፈትኩ እና የጴጥሮስን የመጀመሪያ መልእክት ሶስተኛ እና አራተኛውን ምዕራፎች አነበብኩኝ፣ እና ሳነብም ቀድሞ ከነበሩት በላይ በሚቀጥሉት ምንባቦች በጣም ተነካሁ፥
፯ “ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፥
፰ “በእርሱም ደግሞ ሄዶ ሀበወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው፤
፱ “ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም።” (፩ ጴጥሮስ ፫፥፲፰–፳)።
፲ “እንደሰዎች በሥጋ እንዲፈረድባቸው በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ ስለዚህ ምክንያት ወንጌል ለሙታን ደግሞ ተሰብኮላቸው ነበርና።” (፩ ጴጥሮስ ፬፥፮)።
፲፩ ስለእነዚህ ሀስለተጻፉት ነገሮች ሳሰላስል፣ የመረዳት ለአይኖቼ ተከፈቱ፣ እና የጌታ መንፈስ ሐአረፈብኝ፣ እና ታላቁንና ታናሹን መየሙታን ሰራዊትን አየሁ።
፲፪ እና በዚያም በአንድ ስፍራም አብረው የተሰበሰቡ፣ በስጋ ሲኖሩ በኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ሀታማኝ የነበሩ፣ ቁጥራቸው ታላቅ የሆኑ ለየጻድቃን የመንፈስ ቡድኖች ነበሩ፤
፲፫ እና እንደ እግዚአብሔር ልጅ አይነት ታላቅ ሀመስዋዕት ያቀረቡ፣ እና በቤዛው ስምም ለስቃይንም የተቀበሉ ነበሩ።
፲፬ እነዚህ ሁሉ ሀበአብ እግዚአብሔር እና ለበአንድያ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐጸጋ አማካይነት ለክብሩ መትንሳኤ ፅኑ ሠተስፋ ኖሮአቸው ከስጋ ህይወት ተለይተው ነበር።
፲፭ ሀበደስታ እና በተድላ ተሞልተው እንደነበሩም አየሁ፣ እና የሚድኑበት ቀን ስለመጣ አብረው ተደስተው ነበር።
፲፮ ከሞት ሀእስራት ቤዛነታቸውን ይገለጽ ዘንድ የእግዚአብሔር ልጅ ወደ ለመንፈስ አለም መምጣትን ተሰብስበው ይጠባበቁ ነበር።
፲፯ ያንቀላፋውም ትቢያ የሆነው አካላቸው ወደ ፍጹም ትክክለኛው መልክ፣ ሀአጥንትም ከአጥንቱ፣ እና ጅማትና ስጋ በእነርሱም ላይ ለበዳግም እንዲመለስ፣ እና ሐመንፈስም ከሰውነት ጋር ደግሞም እንዳይለያዩ፣ መየደስታ ሙላትን ይቀበሉ ዘንድ ነበር።
፲፰ ብዙዎች ከሞት ሰንሰለት በሚድኑበት ሰአት እየተደሰቱ፣ እየጠበቁ ሲነጋገሩም፣ የእግዚአብሔር ልጅ ታማኝ ለነበሩት ለታሰሩት ሀነጻነትን በማወጅ መጣ፤
፲፱ እና እዛም ዘለአለማዊ ሀወንጌልን፣ የትንሳኤን እና የሰው ዘር ለከውድቀትና ከግል ኃጢአት ሐንስሀ ስለመግባት የቤዛነትን ትምህርት መሰበከላቸው።
፳ ነገር ግን ሀለክፉዎቹ አልሄደም፣ እና እግዚአብሔርን በሚጠሉት መካከል እና በስጋ እያሉ ንስሀ ላልገቡ ራሳቸውን ለወዳበላሹትም ድምጹ አለተነሳም።
፳፩ ወይም የጥንት ነቢያትን ምስክሮች እና ማስጠንቀቂያዎችን ያስወገዱት አመጸኞችም ፊቱን አላዩትም፣ ወይም ፊቱንም አልተመለከቱም።
፳፪ እነዚህም በነበሩበት ሀጭለማ ነገሰ፣ ነገር ግን በጻድቃን መካከል ለሰላም ነበር፤
፳፫ እና ቅዱሳንም ሀበቤዛነታቸው ተደሰቱ፣ እናም ለበጉልበታቸው ተንበርክከው የእግዚአብሔርን ልጅ እንደቤዛቸው እና ከሞት እና ከገሀነም ሐሰንሰለት ያዳናቸው እንደሆነም አምነው ተቀበሉ።
፳፬ መልካቸውም በራ፣ እና የጌታ ሀድምቀትም በእነርሱ ላይ አረፈ፣ እና ለቅዱስ ስሙም ምስጋናን ለዘመሩ።
፳፭ አዳኝ በአይሁድና በእስራኤል ቤት መካከል በአገልግሎቱ፣ ዘለአለማዊ ወንጌልን ሊያስተምራቸው እንደተጋ እና ለንስሀም ለመጥራት ሶስት አመታትን እንዳሳለፈ ስለገባኝ ተደነቅሁኝም፤
፳፮ እና ግን፣ ምንም እንኳን በታላቅ ሀሀይል እና ስልጣን ታላቅ ስራዎች፣ እና ተዕምራትን ቢሰራም እውነትንም ቢያውጅ፣ ከጥቂቶች በስተቀር ድምጹን ያደመጡና በመገኘቱም የተደሰቱ፣ እና ከእጆቹም ደህንነትን የተቀበሉ ብዙ አልነበሩም።
፳፯ ነገር ግን ከሞቱት መካከል የነበረው አገልግሎቱ በተሰቀለበት እና በትንሳኤው መካከል በነበረው ሀጥቂት ጊዜ የተወሰነ ነበር፤
፳፰ ስለጴጥሮስ ቃላትም አሰብኩ—በዚህም ውስጥ እንዲህ አለ የእግዚአብሔር ልጅ ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው፤ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ ላልታዘዙትም—እና ከእነርሱ ጋር በነበረው አጭር ጊዜ ለእነዚያ መንፈሶች ለመስበክ እና አስፈላጊ የሆነውን አገልግሎት ለመፈጸም እንዴት ነበር የቻለው።
፳፱ እና ስለዚህም ሳስብ፣ አይኖቼ ተከፈቱ፣ እና ሀተረዳሁኝም፣ እና በክፉዎች እና ታዛዥ ባልሆኑት እውነትንም በካዱት መካከል እንዲያስተምራቸው ጌታ እንዳልሄደም ታየኝ፤
፴ ነገር ግን እነሆ፣ ከጻድቃን መካከል ሀይሎቹን አደራጀ እና ሀሀይል እና ስልጣንን የተላበሱ መልእክተኞቹን መደበ፣ እና እንዲሄዱና የወንጌሉን ብርሀን ለበጭለማ ላሉት፣ እንዲሁም ሐለሁሉም የሰዎች መንፈሶች እንዲወስዱ ሀላፊነትን ሰጣቸው፤ እና በዚህም ወንጌሉ ለሙታን ተሰብኮ ነበር።
፴፩ እና የተመረጡት መልእክተኞችም ጌታን ሀየመቀበልን ቀን በማወጅ እና ለታሰሩት፣ እንዲሁም ለኃጢአታቸው ንስሀ በመግባት ወንጌሉን ለሚቀበሉት ለነጻነትን በመግለጥ ሄዱ።
፴፪ እንደዚህም ነበር በኃጢአታቸው፣ እውነትን ሀያለማወቅ ወይም በመተላለፍ፣ ነቢያትን አስወግደው ለለሞቱት ወንጌሉ የተሰበከው።
፴፫ እነዚህም በእግዚአብሔር ሀእምነትን፣ ለኃጢአት ንስሀ መግባትን፣ ለኃጢአት ለስርየት ሐየውክልና ጥምቀትን፣ እጆችን በመጫን የመንፈስ ቅዱስ መስጦታን ተምረው ነበር።
፴፬ እና እንደሰዎች በሥጋ ሀእንዲፈረድባቸው በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር ይኖሩ ዘንድ ራሳቸውን ብቁ ለማድረግ የሚያስፈልጋቸውን የወንጌል መሰረታዊ መርሆችን ሁሉ ተምረው ነበር።
፴፭ እና ስለዚህ በታናሹና በታላቁ፣ ጻድቅ ባልሆነው እና በታማኙ፣ ቤዛነት በእግዚአብሔር ልጅ ሀበመስቀል ላይ ባቀረበው ለመስዋዕት በኩል እንደመጣ በሙታኑ መካከል ታወቀ።
፴፮ እንደዚህም አዳኛችን በመንፈስ አለም በቆየበት ጊዜ በስጋቸው ስለእርሱ የመሰከሩትን ታማኝ ሀነቢያት መናፍስትን በማስተማር እና በማዘጋጀት ጊዜውን አንዳሳለፈ ታውቋል፤
፴፯ ሀበአመጻቸው እና በመተላለፋቸው ምክንያት ራሱ በግል ሊሄድላቸው ለማይችለው፣ እነርሱም በአገልጋዮቹ አገልግሎት በኩል ቃላቶቹን ይሰሙ ዘንድ፣ የቤዛነት መልእክትን ለሙታን ሁሉ እንዲወስዱ ታውቋል።
፴፰ በዚህ ታላቅ የጻድቃን ስብሰባ ከተሰበሰቡት ታላቅ እና ሀያል ከሆኑት መካከል በዘመናት የሸመገለውና የሁሉም አባት፣ አባት ሀአዳም ነበር፣
፴፱ እና የክብርም እናት ሀሔዋን፣ በዘመናት ውስጥ የኖሩት እና እውነት እና ህያው እግዚአብሔርን ካመለኩ ከብዙዎቹ ታማኝ ሴት ልጆቿ ጋር።
፵ የመጀመሪያው ሀሰማዕት ለአቤል እና አባቱን አዳምን ሐየሚመስለው ከሀይለኞቹ አንዱ ወንድሙ መሴትም በዚያ ነበሩ።
፵፩ ስለጎርፉ ማስጠንቀቂያ የሰጠው ሀኖኅ፤ ታላቁ ለሊቀ ካህን ሐሴም፤ የታማኞቹ አባት መአብርሐም፤ ሠይስሀቅ፣ ረያዕቆብ፣ እና የእስራኤል ታላቅ ህግ ሰጪ ሰሙሴ፤
፵፪ እና በትንቢትም አዳኙ ልባቸው የተሰበረውን ይጠግን ዘንድ፣ ሀለተማረኩትም ነጻነትን ለለታሰሩትም መፈታትን ይናገር ዘንድ ተቀብቷል ያለው ሐኢሳይያስም በዚያ ነበሩ።
፵፫ በተጨማሪም፣ በራዕይ እንደ ህያው ነፍሳት ሙታን ሀበትንሳኤ እንደገና ሲመጡ ወደፊትም በስጋ የሚሸፈኑትን ለየደረቁ አጥንቶች የተሞሉበት ታላቅ ሸለቆ ያየው ሐሕዝቅኤል፤
፵፬ ደግሞም የማይጠፋው ወይም ለሌሎች ሰዎች የማይሰጠው የእግዚአብሔር ሀመንግስት በኋለኞቹ ቀናት መመስረትን ቀድሞ አይቶ እና ቀድሞ ነግሮ የነበረው ለዳንኤልም፤
፵፭ ከሙሴ ጋር ሀበክብር የመለወጥ ተራራ ላይ የነበረው ለኢልያ፤
፵፮ እና ሀስለኤልያስ መምጣት የመሰከረው ነቢዩ ለሚልክያስ—ስለዚህም ሞሮኒ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝና የሚያስፈራው ሐየጌታ ቀን ከመምጣቱ በፊት ይመጣል በማለት ያወጀው ሞሮኒም—በዚያ ነበሩ።
፵፯ ነቢዩ ኤልያስ በልጆች ሀልብ ውስጥ የአባቶቻቸውን ቃል ኪዳኖች ይተክላል፣
፵፰ ለሙታን ቤዛነት፣ እና ልጆችን ከወላጆቻቸው ጋር ሀለማስተሳሰር፣ መላው ምድር በምጽአቱ እንዳይረገሙ እና እንዳይጠፉ ዘንድ፣ ለበዘመን ፍጻሜ በጌታ ሐቤተመቅደሶች ውስጥ የሚደረገውን ታላቅ መስራ ቀድሞ ለማሳየት።
፵፱ እነዚህ ሁሉ እና ብዙ ተጨማሪዎች፣ እንዲሁም በኔፋውያን መካከል የኖሩት እና ስለእግዚአብሔር ልጅ መምጣት የመሰከሩት ሀነቢያት፣ በታላቁ ስብሰባ ውስጥ በመደባለቅ እና ደህንነታቸውን ለመጠበቅ፣
፶ ሙታን ሰውነታቸው ሀከመንፈሳቸው ለረዥም ጊዜ መለየቱን እንደ ለባርነት ተመልክተውታልና።
፶፩ እነዚህንም ጌታ አስተማረ፣ እና ከትንሳኤው በኋላ ወደ አባቱ መንግስት በመግባት፣ ሀበህያውነት እና ለበዘለአለም ህይወት አክሊል ይጫንላቸው ዘንድም እንዲመጡ ሐሀይልን ሰጣቸው፣
፶፪ እና ከዚህም በኋላ በጌታ ቃል እንደተገባው በአገልግሎታቸው እንዲቀጥሉ፣ እና ለሚወዱትም ተጠብቀው የነበሩትን ሀበረከቶች ሁሉ ተካፋይ እንዲሆኑ።
፶፫ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ፣ እና አባቴ ሀይረም ስሚዝ፣ ብሪገም ያንግ፣ ጆን ቴይለር፣ ዊልፈርድ ዉድረፍ፣ እና በዘመን ሙላት በታላቁ የኋለኛ ቀን ስራዎች ሀመሰረትን ለመመስረት እንዲመጡ ለየጠበቁት ሌሎች ምርጥ መናፍስት፣
፶፬ በተጨማሪም ቤተመቅደሶችን ለመገንባት እና በእነዚያም ውስጥ ሀለሙታን ቤዛነት ስነስርዓቶችን ለማከናወን የጠበቁት ምርጥ መናፍስትም በመንፈስ አለም ውስጥ ነበሩ።
፶፭ እነርሱም በመጀመሪያ በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ውስጥ መሪዎች እንዲሆኑ ሀየተመረጡት ለበተከበሩትና በታላቆቹ መካከል እንደነበሩም አየሁ።
፶፮ ከመወለዳቸውም በፊት ከብዙ ሌሎች ጋር የመጀመሪያ ትምህርታቸውን በመንፈስ አለም ውስጥ የተቀበሉት እና በጌታ ሀጊዜ ለበወይን ስፍራው ለሰዎች የነፍስ ደህንነት እንዲያገለግሉ ለመምጣት ሐተዘጋጅተውም ነበር።
፶፯ የዚህ ዘመን ታማኝ ሀሽማግሌዎችም ከዚህ ህይወት ሲሄዱ የንስሀ መግባት እና በእግዚአብሔር አንድያ ልጅ መስዋዕት በኩል የቤዛነት ወንጌልን ለበጭለማ ውስጥ እና በሙታን መንፈሶች ታላቅ አለማት ውስጥ በኃጢአት ባርነት ላሉት በመስበክ አገልግሎታቸውን እንደሚቀጥሉ አየሁ።
፶፰ ንስሀ የገቡ ሙታንም የእግዚአብሔር ቤት ሀስርዓቶችን በማክበር ለይድናሉ፣
፶፱ እና የተላለፉት ቅጣታቸውን ከተቀበሉና ሀለመንጻትም ከታጠቡ በኋላ፣ ለበስራዎቻቸው መሰረት ደመወዛቸውን ይቀበላሉ፣ የደህንነት ወራሾች ናቸውና።
፷ እንደዚህም ነበር የሙታን ቤዛነት የተገለጠልኝ፣ እና እመሰክራለሁም፣ እና በጌታ እና አዳኝ በሆነው፣ እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በረከት በኩል ይህ መዝገብ ሀእውነት እንደሆነ አውቃለሁ፣ እንዲህም ይሁን። አሜን።