ክፍል ፶፪
በሰኔ ፮፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ለቤተክርስቲያኗ ሽማግሌዎች የተሰጠ ራዕይ። በሰኔ ፫ ተጀምሮ በሰኔ ፮ የተዘጋ ጉባኤ ከርትላንድ ውስጥ ተካሂዶ ነበር። በዚህ ጉባኤ ውስጥም የመጀመሪያው ልዩ የሊቀ ካህን ሀላፊነት ሹመቶች ተደርገው ነበር፣ እናም የሀሰት እና የሚያታልሉ መናፍስትም ተገልጠው እና ተገስጸውም ነበር።
፩–፪፣ የሚቀጥለው ጉባኤ በሚዙሪ ውስጥ እንዲሆን ተወስኗል፤ ፫–፰፣ አንዳንድ ሽማግሌዎች አብረው እንዲጓዙም ተመድበዋል፤ ፱–፲፩፣ ሽማግሌዎችም ሐዋርያት እና ነቢያት የጻፉትን ያስተምሩ፤ ፲፪–፳፩፣ በመንፈስ የሚታነጹት የምስጋና እና የጥበብ ፍሬ ያመጣሉ፤ ፳፪–፵፬፣ ወደ ሚዙሪ ለጉባኤው እየተጓዙ እያሉ፣ ወንጌልን እየሰበኩ እንዲሄዱ የተለያዩ ሽማግሌዎች ተመድበዋል።
፩ እነሆ፣ ጌታ በእነዚህ በመጨረሻው ቀናት ሀለጠራቸው እና ለመረጣቸው ሽማግሌዎች በመንፈሱም ድምፅ፣ እንዲህ ይላል—
፪ እንዲህም አለ፤ እኔ ጌታ ሀበቃል ኪዳን ወራሾች ለሆኑት፣ እና ለያዕቆብ ለቅሪት ለሆኑት ህዝቤ፣ ሐበቀደስኩላቸው መምድር ላይ፣ በሚዙሪ ውስጥ የሚቀጥለው ጉባኤ እስከሚጠራ ድረስ ምን እንደምታደርጉ አስታውቃችኋለሁ።
፫ ስለዚህ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ቤታቸውን ትተው ለመሄድ ለመዘጋጀት በሚችሉበት፣ አገልጋዮቼ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ፣ እና ስድኒ ሪግደን ወዲያው ይጓዙ፣ እና ወደ ሚዙሪ ምድርም ይጓዙ።
፬ እናም ለእኔ ታማኝ እስከሆኑም ድረስ፣ ምን እንደሚያደርጉ እንዲያውቁም ይደረግላቸዋል፤
፭ እናም ደግሞ፣ ታማኝ እስከሆኑም ድረስ፣ የውርሳችሁን ሀምድር እንዲያውቁት ይደረጋል።
፮ እና ታማኝ እስካልሆኑም ድረስ፣ በእኔ ፈቃድ፣ እና መልካም እንደሚመስለኝምይገለላሉ።
፯ እና ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ ላይመን ዋይት እና አገልጋዬ ጆን ኮርል ፈጥነው ይጓዙ፤
፰ እና አገልጋዬ ጆን መርዶክ፣ እና አገልጋዬ ሀይረም ስሚዝ በድትሮይት በኩል ወደዚያ ይጓዙ።
፱ ከዚያም ስፍራ፣ ሀነቢያት እና ሐዋርያት ከጻፉት፣ እና በእምነት ጸሎት አማካይነት ለአፅናኙ ካስተማራቸው ሌላ ሐምንም ሳይሉ፣ ቃሉን በሚያልፉበት ስፍራዎች እየሰበኩ ይጓዙ።
፲ ሀሁለት በሁለት ሆነውም ይጓዙ፣ እና በዚህም በሚያልፉበትም ስፍራዎች፣ ለበውሀ በማጥመቅ እና በውሀውም አጠገብ ሐእጃቸውን በመጫን፣ በእያንዳንዱ ስብሰባዎች ውስጥ ይስበኩ።
፲፩ ጌታም እንዲህ ይላል፣ ሀበፅድቅም ስራዬን በአጭር እቆርጣለሁ፣ ድል ለመንሣት ፍርድን የማመጣበት ቀን ይመጣልና።
፲፪ አገልጋዬ ላይመን ዋይትም ይጠንቀቅ፣ ሰይጣን እንደ ሀገለባ ሊያበጥረው ይፈልጋልና።
፲፫ እናም እነሆ፣ ሀታማኝ የሆነው እርሱ በብዙ ነገሮች ላይ ገዢ ይሆናልና።
፲፬ እና ደግሞም፣ እንዳትታለሉም ለሁሉም ነገሮች ንድፍን እሰጣችኋለሁ፤ ሰይጣን በምድር ላይ አለና፣ እና አገሮችን እያሳታቸውም ይሄዳል—
፲፭ ስለዚህ የሚጸልየው፣ መንፈሱ ሀየተዋረደውም፣ ለስርዓቴን ካከበረ፣ እርሱም በእኔ ዘንድ ሐተቀባይነትን ያገኛል።
፲፮ መንፈሱ ትሁት፣ ቋንቋውም ቅንና የሚያንፅ የሆነው፣ የሚናገረውም፣ ስርዓቶቼን ቢያከብር፣ እርሱ ከእግዚአብሔር ነው።
፲፯ እና ደግሞም፣ በሀይሌ የሚንቀጠቀጠውም እርሱ ሀጠንካራ እንዲሆን ይደረጋል፣ እና በምሰጣችሁ ራዕዮች እና እውነቶች በኩልም የምስጋና እና ለየጥበብ ፍሬዎችን ያመጣል።
፲፰ እና ደግሞም የተሸነፈውም እና በዚህም ንድፍ አማካይነት፣ ፍሬ ሀየማያመጣውም ከእኔ አይደለም።
፲፱ ስለዚህ፣ ከሰማይ በታች ሁሉ በዚህ ንድፍ አማካይነት መናፍስትን በሁሉም ጉዳዮች ሀታውቃላችሁ።
፳ ቀኖቹም ቀርበዋል፤ ሰዎችም እንደ እምነታቸው ሀይከናወንላቸዋል።
፳፩ እነሆ፣ ይህ ትእዛዝ ለመረጥኳቸው ሽማግሌዎች ሁሉ የተሰጠው ነው።
፳፪ እና ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ ሀቶማስ ቢ ማርሽ እና አገልጋዬ እዝራ ቴይርም ቃሉን በየመንገዳቸው እየሰበኩ ወደ እዚያ ምድር ደግመውም ይጓዙ።
፳፫ እና ደግሞም፣ አገልጋዬ አይዛክ ሞርሊ እና አገልጋዬ እዝራ ቡዝ፣ ቃሉን በዚያም ምድር እግረ መንገዳቸውን እየሰበኩ፣ ደግመው ይጓዙ።
፳፬ እና ደግሞም፣ አገልጋዮቼ ሀኤድዋርድ ፓርትሪጅ እና ማርቲን ሀሪስ ከአገልጋዮቼ ስድኒ ሪግደን እና ጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ ጋር ይጓዙ።
፳፭ አገልጋዮቼ ዴቪድ ዊትመር እና ሀርቪ ውትሎክም፣ ደግመውም እግረ መንገዳቸውን እየሰበኩ ወደ እዚያው ምድር ይጓዙ።
፳፮ እናም አገልጋዮቼ ሀፓርሊ ፒ ፕራት እና ለኦርሰን ፕራትም፣ እግረ መንገዳቸውን፣ እንዲሁም ወደ እዚያው ምድር እየሰበኩ ይጓዙ።
፳፯ እናም አገልጋዮቼ ሰለሞን ሀንኮክ እና ሰሚየን ካርተርም ወደ እዚያ ምድርም ደግመውም ይጓዙ፣ እናም እግረ መንገዳቸውን ይስበኩ።
፳፰ አገልጋዮቼ ኤድሰን ፉለር እና ጄከብ ስኮትም እንዲሁ ይጓዙ።
፳፱ አገልጋዮቼ ሊቫይ ደብሊው ሀንኮክ እና ዘበዲ ኮልትርንም እንዲሁ ይጓዙ።
፴ አገልጋዮቼ ሬኖልድዝ ካሁን እና ሳሙኤል ኤች ስሚዝም እንዲሁ ይጓዙ።
፴፩ አገልጋዮቼ ዊለር ቦልድውን እና ውልያም ካርተርም እንዲሁ ይጓዙ።
፴፪ እናም አገልጋዮቼ ሀኑወል ናይት እና ሴላ ጄ ግርፍንም ይሾሙ፣ እናም እንዲሁ ይጓዙ።
፴፫ አዎን፣ እውነት እላለሁ፣ እነዚህ ሁሉ ወደ አንድ ስፍራ በተለያዩ መንገዶቻቸው ይጓዙ እናም አንድ በሌላው ሰው ሀመሰረት ላይ አያንጽም፣ ወይም በሌላ ሰውም መንገድ አይጓዝም።
፴፬ ታማኝ የሆነው፣ እርሱ ይጠበቃል እና ብዙ ሀፍሬ በማፍራትም ይባረካል።
፴፭ እና ደግሞም፣ እንዲህ እላችኋለሁ፣ አገልጋዮቼ ጆሴፍ ዌክፊልድና ሰለሞን ሀምፍሪ ወደ ምስራቅ አገሮች ይጓዙ፤
፴፮ ትንቢቶቹ እንዲሟሉ፣ ሀካዩት እና ከሰሙት እናም በእርግጥ ለከሚያምኑት፣ ከነቢያትና ከሐዋርያት በቀር ምንም ነገሮችን ሐሳያውጁ፣ ከቤተሰቦቻቸው ጋርም ያገልግሉ።
፴፯ በኃጢአት ምክንያትም፣ ለሂምን በሰት የተሰጠውም ሀይወሰድበት፣ እናም ለሳይመንድስ ራይደር ይሰጥ።
፴፰ እና ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ጀርድ ካርተር እንደ ካህን ሀይሾም፣ ጆርጅ ጄምስም እንዲሁ እንደ ለካህን ይሾም።
፴፱ የሚቀሩት ሽማግሌዎችም ቤተክርስቲያኖችን ሀይጠብቁ፣ እና በአካባቢያቸውም ቃሉን ያውጁ፤ እናም ለየጣኦት አምላኮም እንዳይኖር እና ጥፋት እንዳይሰራም በገዛ እጆቻቸው ይስሩ።
፵ እናም በሁሉም ነገሮችም ሀድሀውን እና ለችግረኛውን፣ የታመመውን እና የተሰቃየውን አስታውሱ፣ ይህን የማያደርግም፣ እርሱ ደቀ መዝሙሬ አይደለምና።
፵፩ እና ደግሞም፣ አገልጋዮቼ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ፣ እና ስድኒ ሪግደን እና ኤድዋርድ ፓርትሪጅ ከቤተክርስቲያኗ ሀማስተዋወቂያ ይውሰዱ። እና አንድ ደግሞ ለአገልጋዬ ኦሊቨር ካውድሪ ይሰጠው።
፵፪ እና በዚህም፣ እንዲሁም እንዳልኩት፣ ታማኝ ከሆናችሁ፣ ሀየውርሳችሁ ምድር በሆነው፣ እና አሁንም የጠላቶቻችሁ ምድር በሆነው፣ ለበሚዙሪ ምድር ለመደሰት ራሳችሁን ትሰበሰባላችሁ።
፵፫ ነገር ግን፣ እነሆ፣ እኔ ጌታ ከተማውን በጊዜው አፈጥነዋለሁ፣ እና ታማኝ የሆነውንም ሀበደስታ እና በሀሴት አነግሰዋለሁ።
፵፬ እነሆ፣ እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፣ እናም በኋለኛው ቀን ሀአነሳቸዋለሁ። እንዲሁም ይሁን። አሜን።