ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፳፯


ክፍል ፳፯

በነሀሴ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በሀርመኒ ፔንስልቫኒይ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። የዳቦ እና ወይን ቅዱስ ቁርባን ሀይማኖታዊ አገልግሎት ለመስጠት ለማዘጋጀት፣ ጆሴፍ ወይን ያገኝ ዘንድ ሄደ። የሰማይ መልአክም ተገናኘው እናም ይህንን ራዕይ ተቀበለ፣ የዚህም ራዕይ አማካይ ክፍል በወቅቱ ሲጻፍ ቀሪው በቀጣዩ ወር መስከረም የተጻፈ ነበር። በአሁን ወቅት በቤተክርስቲያኗ የቅዱስ ቁርባን አገልግሎት ውስጥ በወይን ፋንታ ውሀ ጥቅም ላይ ውሏል።

፩–፬፣ በቅዱስ ቁርባን ወቅት በምሳሌነት መውሰድ ያለባቸው ተገለጡ፤ ፭–፲፬፣ ክርስቶስ እና ከሁሉም ዘመናት ያሉ ደቀመዛሙርቱ ቅዱስ ቁርባንን መውሰድ ይኖርባቸዋል፤ ፲፭–፲፰፣ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር እቃ ልበሱ።

ፈጣን እና ኃያል የሆኑትን፣ የጌታህን፣ የአምላክህን እና የአዳኝህን የኢየሱስ ክርስቶስን ቃላት አድምጥ።

ስለሆነም፣ እነሆ፣ በአባቴ ፊት ለእናንተ የሰዋሁትን አካሌን እናም ለኃጢአታችሁ ስርየት የፈሰሰውን ደሜን እያስታወሳችሁ ሙሉ አይናችሁን ወደ ክብሬ ካደረጋችሁ፣ ቅዱስ ቁርባንን ስትወስዱ የምትበሉት ወይም የምትጠጡት ነገር ለውጥ አያመጣም።

ስለዚህ፣ ወይንም ሆነ ጠንካራ መጠጥ ከጠላቶቻችሁ እንዳትገዙ ትእዛዝን እሰጣችኋለሁ፤

ስለዚህ፣ በመካከላችሁ፣ አዎን በምድር ላይ በሚገነባው በዚህ በአባቴ መንግስት፣ አዲስ ካልተሰራ በስተቀር ምንም ነገር እንዳትወስዱ፤

እነሆ፣ ይህ በእኔ ዘንድ ጥበብ ነው፤ ስለዚህ፣ ከእናንተ ጋር እና ወደ እናንት የዘለአለም ወንጌሌን ሙላት የያዘውን መፅሐፈ ሞርሞንን እንዲገልጥ ከላኩት፣ የኤፍሬምን በትር ጽሁፍ ቁልፎች ከሰጠሁት ከሞሮኒ ጋር በምድር ላይ የወይን ፍሬውን የምጠጣበት ሰዓት ስለሚመጣ አትደነቁ፤

እናም እንዲሁም አለም ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያት አንደበት የመጨረሻውን ቀን በተመለከተ የተነገሩትን የሁሉም ነገሮች ዳግም መመለስ ቁልፍ ከሰጠሁት ከኢልያ ጋር፤

እናም ደግሞ፣ እርሱ (ኢልያ) የጎበኝው እና ልጅ እንደሚኖረው እና ስሙም ዮሐንስ እንዲሚሆን በኤልያስም መንፈስ እንደሚሞላ የተነገረለት የዘካሪያስ ልጅ ከሆነው ዮሐንስም ጋር፤

ይህም ዮሐንስ ለእናንተ ለአገልጋዮቼ፣ ለጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ እና ለኦሊቨር ካውድሪ እንደ አሮን እንድትጠሩ እና እንድትሾሙ የተቀበላችሁትን የመጀመሪያውን ክህነትን እንድትቀበሉ የላክሁት ነው፤

እናም እንዲሁም መላው ምድር በእርግማን እንዳይመታ የአባቶችን ልብ ወደልጆች፣ የልጆችን ልብ ወደአባቶች እንዲመልስ የሚያስችለውን የኃይል ቁልፍ ከሰጠሁት ኤልያስ

እንዲሁም ቃል ኪዳኖቹ በጸኑባቸው ከአባቶቻችሁ ከዮሴፍና ያዕቆብና፣ ይስሀቅና፣ አብርሐም ጋር፣

፲፩ እንዲሁም የሁሉም አባት፣ የሁሉም ልዑል፣ በዘመናት ከሸመገለው ከሚካኤል ወይም አዳም ጋር፣

፲፪ እናም ሐዋርያት ትሆኑ ዘንድ በሾምኳችሁ እና ባጸደቅኩላችሁእናም የስሜ ልዩ ምስክሮች እንድትሆኑ እና የአገልግሎታችሁን እናም ለእነርሱ የገለጥኩላቸውን ተመሳሳይ ነገሮች ቁልፍ እንድትይዙ በላኳቸው ከጴጥሮስ፣ እና ከያእቆብ፣ እና ዮሐንስ ጋር፤

፲፫ ለእነርሱም በሰማይ እና በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ በአንድ በምጠቀልልበት በዘመናት ሙላት፣ የዚህን የዘመነ ፍጻሜን ወንጌልንና የመንግስቴን ቁልፎች ለመጨረሻው ጊዜ ከሰጠኋቸው ጋር፤

፲፬ እናም እንዲሁ አባቴ ከአለም ከሰጠኝ ሁሉ ጋር የምጠጣበት ሰዓት ስለሚመጣ አትደነቁ።

፲፭ ስለዚህ፣ ልባችሁን ከፍ አድርጋችሁ ተደሰቱ፣ ወገባችሁን አጥብቁ፣ ክፋውን ቀን ለመቃወም ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን የጦር እቃ ሁሉ ልበሱ።

፲፮ ስለዚህ መላእክቴ እንዲሰጧችሁ ያደረኩትን፣ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁየጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፣ በሰላም ወንጌል በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤

፲፯ የሚንበለበሉትን የክፉን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ በማንሳት፤

፲፰ እናም የመዳንንም ራስ ቁር፣ እናም በእናንተ ላይ የማፈሰውን የመንፈስንም ሰይፍ እናም የምገልጥላችሁን ቃሌን ያዙ፣ እናም የምትጠይቁኝንም ነገሮች በተመለከተም ተስማሙ፣ እስከምመጣም ድርስ ታማኝ ሁኑ፣ እናም እናንተም እኔ ወደአለሁበት ትሆኑትም ዘንድ ትነጠቃላችሁ። አሜን።