ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፬


ክፍል ፬

የካቲት ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) በሀርመኒ ፔንስልቬንያ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ለአባቱ ለጆሴፍ ስሚዝ ቀዳማዊ የተሰጠ ራዕይ።

፩–፬፣ የጌታን አገልጋዮች የጀግና አገልግሎት ያድናቸዋል፤ ፭–፮፣ አምላካዊ ባህሪያት ላገልግሎቱ ብቁ ያደርጋቸዋል፤ ፣ የእግዚአብሔር ነገሮች መሻት አለባቸው።

አሁን እነሆ፣ በሰዎች ልጆች መካከል ድንቅ ስራ ሊመጣ ነው።

ስለዚህ እናንት በእግዚአብሔር አገልግሎት ውስጥ መሳተፍ የጀመራችሁ፤ በመጨረሻው ቀን በእግዚአብሔር ፊት ያለወቀሳ ትቆሙ ዘንድ፣ በሙሉ ልባችሁ፤ ኃይላችሁ፣ አዕምሮአችሁ እና ጉልበታችሁ እንደምታገለግሉት አረጋግጡ።

ስለዚህ፣ እግዚአብሔርን ለማገልገል ፈቃድ ካላችሁ ወደስራው ተጠርታችኋል

ስለሆነም እነሆ እርሻው ነጥቷል አዝመራውም ዝግጁ ነው፤ እናም አስተውሉ፣ በጥንካሬው የሚያጭድ እንዳይጠፋ ዘንድ በጎተራው ይከምራል፣ ነገር ግን ለነፍሱ ደህንነትን ያመጣል፤

እናም እምነትተስፋለጋስነትና ፍቅር፣ ሙሉ አይኑን ወደ እግዚአብሔር ክብር ከማድረግ ጋር ለስራ ብቁ ያደርጉታል።

እምነት፣ ምግባረ በጎነት፣ ዕውቀት፣ ራስን መግዛት፣ ትዕግስት፣ ወንድማዊ ደግነት፣ አምላካዊነት፣ ልግስና፣ ትህትናትጋትን አስታውሱ።

ለምኑ፣ እናም ይሰጣችኋል፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል። አሜን።