ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፺፩


ክፍል ፺፩

በመጋቢት ፱፣ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ኦሀዮ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ነቢዩ በዚህ ጊዜ ብሉይ ኪዳንን በመተርጎም ላይ ነበር። አፖክርፋ በሚባለው የጥንት ፅሁፎች ክፍል ላይ ሲደርስ፣ ጌታን ጠየቀ እና ይህን መመሪያ ተቀበለ።

፩–፫፣ አፖክርፋው በትክክል የተተረጎመ ነው ነገር ግን በውስጡ በሰዎች እጆች እውነት ያልሆኑ ብዙ ተጨማሪዎች ነገሮችን ይይዛል፤ ፬–፮፣ ይህም መንፈስ የበራላቸውን ይጠቅማል።

በእውነት፣ ጌታ አፖክርፋን በሚመለከት እንዲህ ይላል—በውስጡ እውነት የሆኑ አያሌ ነገሮችን ይዟል፣ እና አብዛኛውም በትክክል የተተረጎመ ነው፤

በውስጡ፣ በሰዎች እጆች የተጨመሩ፣ እውነት ያልሆኑ ብዙ ነገሮችም አሉ።

እውነት እላችኋለሁ፣ አፖክርፋው መተርጎሙ አስፈላጊ አይደለም።

ስለዚህ፣ የሚያነበው፣ ይረዳው፣ መንፈስ እውነትን ይገልጣልና፤

እና መንፈስ ያበራለት እርሱም ከዚህ ጥቅም ያገኛል፤

እና በመንፈስ የማይቀበለውም፣ አይጠቀምበትም። ስለዚህ መተርጎሙ አስፈላጊ አይደለም። አሜን።