ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፺፱


ክፍል ፺፱

በነሀሴ ፳፱፣ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) በሀይረም ኦሀዮ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ለጆን መርዶክ የተሰጠ ራዕይ። ባለቤቱ ጁሊያ ክላፕ በሚያዝያ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) ከሞተች በኋላ፣ እናት የሌላቸው ልጆቹ ከሌሎች ቤተሰቦች ጋር እየኖሩ ሳሉ፣ ከአንድ አመት በላይ፣ ጆን መርዶክ ወንጌልን ይሰብክ ነበር።

፩–፰፣ ጆን መርዶክ ወንጌልን እንዲሰብክ ተጠራ፣ እና እርሱን የሚቀበሉትም ጌታን ይቀበላሉ እና ምህረትንም ያገኛሉ።

እነሆ፣ ለአገልጋዬ ጆን መርዶክ ጌታ እንዲህ ይላል—ወደ ምስራቅ ሀገሮች ከቤት ወደ ቤት፣ ከመንደር ወደ መንደር፣ እና ከከተማ ወደ ከተማ ዘለአለማዊ ወንጌሌን በዚያ ለሚኖሩት፣ በስደት እና በክፋት መካከል እያወጅህ እንድትሄድ ተጠርተሀል።

እና የሚቀበልህም ይቀበለኛል፤ እና በእኔ ቅዱስ መንፈስ መገለጥ ቃሌን ለማወጅ ሀይል ይኖርሀል።

እናማንም እንደ ትንሽ ልጅ የሚቀበልህም፣ መንግስቴን ይቀበላል፤ እነርሱም ብፁዓን ናቸው፥ ምህረት ያገኛሉና።

እና ማንም አንተን የሚቃወም ከአባቴ እና ከቤቱ ይወገዳል፤ እና በእግረ መንገድህ በእነርሱም ላይ ምስክር ይሆን ዘንድ በተሰወሩ ስፍራዎች እግሮችህን ታጸዳለህ።

እነሆ እና አስተውል፣ በመጽሐፍም ጥራዝ እንደ ተጻፈው፣ በእኔ ላይ ከፅድቅ በመራቅ ክፉ ሥራቸው ሁሉ እወቀሳቸው ዘንድ፣ ለፍርድ በቶሎ እመጣለሁ

አሁንም፣ እውነት እልሀለሁ፣ ልጆችህን እስክታስተዳድር እና በመልካም ወደ ፅዮን ኤጲስ ቆጶስ እስኪላኩ ድረስ እንድትሄድ ፍቃዴ አይደለም።

እና ከጥቂት አመታት በኋላ፣ በእኔ የምትሻ ከሆነ፣ ውርስህን ለመቀበል ወደ መልካሚቱ ምድር መሄድ ትችላለህ፤

አለበለዚያ እስከምትወሰድ ድረስ ወንጌሌን በማወጅ ትቀጥላለህ። አሜን።