ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፳፮


ክፍል ፳፮

በሐምሌ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በሀርመኒ ፔንስልቫኒያ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ለኦሊቨር ካውድሪ፣ እና ለጆን ዊትመር የተሰጠ ራዕይ። (የክፍል ፳፬ ርዕስን ተመልከቱ)።

፩ ቅዱሳን መጻህፍትን እንዲያጠኑ እና እንዲሰብኩ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል፤ ፪፣ የጋራ ስምምነት ህግ ጸደቀ።

፩ እነሆ፣ እውነት እላችኋለሁ ወደ ምዕራብ የሚቀጥለውን ጉባዔ ለማድረግ እስክትሄዱ ድረስ ጊዜአችሁን በቅዱሳን መጻህፍት ጥናት፣ ስብከት፣ በኮለስቪል ያለውን ቤተክርስቲያን በማጠንከር፣ በምድሩ ላይ ስራችሁን እንድታከናውኑ ይጠበቅባችኋል፣ እናም በመቀጠልም ምን እንደምታከናውኑ ይነገራችኋል።

፪ እናም ሁሉም ነገሮች በቤተክርስቲያን በጋራ ስምምነት፣ በብዙ ጸሎት እና እምነት ይከናወናሉ፣ ሁሉንም ነገሮች በእምነት ትቀበላላችሁ። አሜን።