ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፹


ክፍል ፹

በመጋቢት ፯፣ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) በሀይረም ኦሀዮ ውስጥ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ለስቲቨን ቢዩረት የተሰጠ ራዕይ።

፩–፭፣ ስቲቨን ባርነት እና ኢድን ስሚዝ በሚመርጡበት ስፍራ እንዲሰብኩ ተጠርተዋል።

፩ በእውነት ጌታ ለአንተ አገልጋዬ ስቲቨን ባርነት እንዲህ ይላል፥ ሂድ፣ ወደ አለም ሂድ እናም በድምፅህ አካባቢ ለሚመጣው ፍጥረት ሁሉ ወንጌልን ስበክ።

፪ እናም የጉዞ ጓደኛ ከፈለግህ፣ አገልጋዬን ኢድን ስሚዝን እሰጥሀለሁ።

፫ ስለዚህ፣ ሂዱ እናም ወንገሌን ስበኩ፣ ወደ ሰሜን ይሁን ወደ ደቡብ፣ ወደምስራቅ ይሁን ወደምእራብ ግድ የለም፣ አትሳሳቱምና።

፬ ስለዚህ፣ የሰማችሁትን ነገሮች አውጁ፣ እናም በእውነት እመኑ፣ እናም እውነት እንደሆነ እወቁ።

፭ እነሆ፣ ይህ የጠራችሁ፣ የቤዛችሁ፣ እንዲሁም የእርሱ የኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ ነው። አሜን።