ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፻፴፩


ክፍል ፻፴፩

በግንቦት ፲፮ እና ፲፯፣ ፲፰፻፵፫ (እ.አ.አ.) በራመስ ኢለኖይ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጡ መመሪያዎች።

፩–፬፣ የሰለስቲያል ጋብቻ ከፍ ባለው ሰማይ ዘለአለማዊ ክብር ለማግኘት አስፈላጊ ነው፤ ፭–፮፣ ሰዎች ለዘለአለም ህይወት እንዴት እንደታተሙ ተገልጿል፤ ፯–፰፣ መንፈስ ሁሉ ግዝፈት ያለው ነው።

፩ በሰለስቲያል ክብር ውስጥ ሶስት ሰማያት ወይም ደረጃዎች አሉ፤

፪ ከፍተኛውን ለማግኘት፣ ሰው ወደ እዚህ የክህነት ስርዓት መግባት አለበት [ይህም አዲስ እና ዘለአለማዊ የጋብቻ ቃል ኪዳን ማለት ነው]፤

፫ እና ይህን ባያደርግ፣ ሊያገኘው አይችልም።

፬ ወደሌሎቹ ለመግባት ይችላል፣ ነገር ግን ያም የሚያደርገው መጨረሻው መንግስቱ ነው፤ ተጨማሪም ሊያገኝ አይችልም።

፭ [ግንቦት ፲፯፣ ፲፰፻፵፫ (እ.አ.አ.)]። በተጨማሪ እርግጠኛ የትንቢት ቃል ማለት በራዕይ እና በትንቢት መንፈስ፣ በቅዱስ የክህነት ሀይል አማካይነት፣ ሰው ለዘለአለም ህይወት እንደታተመ አውቋል ማለት ነው።

፮ ሰው በድንቁርና ይድን ዘንድ አይችልም።

፯ ስለዚህ፣ ህልውና የሌለው ህልው ነገር የሚባል ነገር የለም። መንፈስ ሁሉ ህልውና ያለው ነው፣ ነገር ግን ይህም የጠራ እና ንጹህ ነው፣ እና ሰውም ሊለየው የሚችለው በነጹ አይኖች ብቻ ነው፤

፰ እናየውም ዘንድ አይቻለንም፤ ነገር ግን ሰውነቶቻችን ሲነጹ ግዝፈት ያለው እንደሆነ ሁሉ እናያለን።