ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፸፪


ክፍል ፸፪

በታህሳስ ፬፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በከርትላንድ ኦሀዮ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ብዙ ሽማግሌዎች እና አባላት ሀላፊነታቸውን ለመማር እና በቤተክርስቲያኗ ትምህርቶች ለመታነፅ ተሰብስበው ነበር። ይህ ክፍል በአንድ ቀን የተሰጡ ሶስት ራዕዮች የተቀናጁበት ነው። ከ፩ እስከ ፰ ያሉት ቁጥሮች ኒዌል ኬ ውትኒ እንደ ኤጲስ ቆጶስ የተጠራበትን ያሳውቃሉ። ከዚያም ተጠራ እና ተሾመ፣ ከዚያም፣ ስለ ኤጲስ ቆጶሱ ሀላፊነቶች ተጨማሪ ማስረጃዎች የሚሰጡበትን ከቁጥር ፱ እስከ ፳፫ ያለውንም ተቀብሎ ነበር። ከዚህም በኋላ፣ ከቁጥር ፳፬ እስከ ፳፮ ስለፅዮን መሰብሰብ መመሪያ ሰጥተው ነበር

፩–፰፣ ሽማግሌዎች የመጋቢነታቸውን መግለጫ ለኤጲስ ቆጶሱ ይስጡ፤ ፱–፲፭፣ ኤጲስ ቆጶሱ ግምጃ ቤትን ይጠብቃል፣ እናም ድሆችን እና ችግረኞችን የሚሹት ይንከባከባል፤ ፲፮–፳፮፣ ኤጲስ ቆጶሳት የሽማግሌዎችን ብቃነት ያረጋግጡ።

አድምጡ፣ እናም መንግስት እና ሀይል የተሰጣችሁ አቤቱ እናንት የተሰባሰባችሁት የቤተክርስቲያኔ ሊቀ ካህና ትየጌታን ድምፅ ስሙ።

በእውነትም ጌታ እንዲህ ይላል፣ ለእናንተ፣ ወይም ከእናንት በዚህ የጌታ የወይን ስፍራ በሆነች ቤተክርስቲያን፣ ኤጲስ ቆጶስ ይመረጥ ፍቃዴ ነው።

እናም በእውነት በዚህም ነገር ያደረጋችሁት ጥበብ ነው፣ ከእያንዳንዱ መጋቢ እጅ፣ በጊዜም ይሁን በዘለአለም፣ የመጋቢነቱን መግለጫ እንዲያቀርብ በጌታ ይጠበቅበታልና።

በጊዜ ታማኝ እና ብልህ የሆነው ለእርሱ በአባቴ የተዘጋጁትን መኖሪያዎች ለመውረስ ብቁ ሆኑ ይገኛል።

እውነት እላችኋለሁ፣ በቤተክርስቲያኗ በዚህ የወይን ስፍራ ውስጥ ያሉ ሽማግሌዎች የመጋቢነታቸውን መግለጫ በዚህ የወይን ስፍራዬ በእኔ ለሚመረጠው ኤጲስ ቆጶሱ ይስጡ።

እነዚህ ነገሮችም፣ በፅዮን ላለው ኤጲስ ቆጶሱ ተላልፈው እንዲሰጡ በመመዝገቢያው ውስጥ ይሁኑ።

እናም የኤጲስ ቆጶሱ ሀላፊነት በተሰጡት ትእዛዛት እና በጉባኤ ድምጽ እንዲታወቅ ይደረጋል።

እናም አሁን፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በዚህ ሀይል የሚመረጠው እና የሚሾመው ሰው አገልጋዬ ኒወል ኬ ውትኒ ነው። ይህም፣ የቤዛችሁ፣ የጌታ አምላካችሁ ፈቃድ ነው። እንዲህም ይሁን። አሜን።

ከተሰጠው ህግ በተጨማሪ፣ በዚህ የወይን ስፍራ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተሾመውን የኤጲስ ቆጶሱን ሀላፊነት የሚያሳውቀው የጌታ ቃል፣ በእውነትም ይህ ነው—

የጌታን ጎተራ መጠበቅ፤ በዚህ የወይን ስፍራ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገንዘቦችን መቀበል ነው፤

፲፩ አስቀድሞ እንደታዘዘው የሽማግሌዎችን መግለጫ ለመቀበል፤ እናም የሚከፍሉት እስካላቸው ድረስ፣ ለሚቀበሉት የሚከፍሉትን እንደፍላጎታቸው ለማስተዳደር ነው፤

፲፪ ይህም ደግሞ ለቤተክርስቲያኗ ጥቅም፣ ለድሀው እና ለችግረኛው፣ ይቀደስ ዘንድ ነው።

፲፫ እናም ለመክፈል ችሎታ የሌለው ለእርሱ፣ መግለጫው ይወሰድ እናም፣ ጌታ በእጆቹ ከሚያስቀምጣቸው ገንዘቦች እዳውን ለሚከፍልለት፣ ለፅዮን ኤጲስ ቆጶስ ይሰጥ።

፲፬ እናም በመንፈሳዊ ነገሮች፣ ወንጌሉን እና የመንግስቱን ጉዳዮች ለቤተክርስቲያኗ እና ለአለም በማስተዳደር የሚያገለግለውም ታማኝ አገልጋይ፣ እዳውን ለፅዮን ኤጲስ ቆጶስ በዚህ ይከፍላል፤

፲፭ በመሆኑም ከቤተክርስቲያኑ ይወጣል፣ በህጉ መሰረት ወደ ፅዮን የሚመጣው እያንዳንዱ ሰው በፅዮን ኤጲስ ቆጶስ ፊት ሁሉንም ነገሮች ማቅረብ ይኖርበታልና።

፲፮ እናም አሁን፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በዚህ የወይን ስፍራ ያሉት እያንዳንዱ ሽማግሌዎች በዚህ የወይን ስፍራ ለሚገኘው ኤጲስ ቆጶስ የሀላፊነቱን መግለጫ መስጠት ይኖርበታል—

፲፯ ከዚህ የወይን ስፍራ ዳኛ ወይም ኤጲስ ቆጶስ በፅዮን ባለ ኤጲስ ቆጶስ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት እያንዳንዱን ሰው ተቀባይ ያደርገዋል፣ እናም ለሁሉም ነገሮች መልስ ይሰጣል፣ እንደ ብልህ መጋቢ እና ታማኝ አገልጋይም ያስቆጥረዋል፤

፲፰ አለበለዚያም በፅዮን ኤጲስ ቆጶስ ተቀባይነትን አያገኝም።

፲፱ እናም አሁን፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ለዚህ የወይን ስፍራ ቤተክርስቲያን ኤጲስ ቆጶስ መግለጫ የሚሰጥ እያንዳንዱ ሽማግሌ፣ ለራሱ እና ለመግለጫው በሁሉም ነገሮች ማረጋገጫ ይሆንለት ዘንድ እንዲያቀርብ፣ ባገለገለባት ቤተክርስቲያን ወይም ለቤተክርስቲያናቱ ብቁ ስለመሆኑ ምስክር ይሰጥ።

እና ደግሞም፣ የተጻፉትን ነገሮችን በመመልከት ሀላፊነት የተሰጣቸው አገልጋዮቼም ከኤጲስ ቆጶስ ወይም ከኤጲስ ቆጶሳት በሁሉም ነገሮች እርዳታ የማግኘት መብት አላቸው—

፳፩ ያም ራዕዮችም እንዲታተሙ፣ እናም እስከ ምድር ዳርቻ እንዲሄዱ፤ ቤተክርስቲያኗን በሁሉም ነገሮች የሚረዷትን ገንዘቦች ያገኙ ዘንድ፤

፳፪ በሁሉም ነገሮች ራሳቸውን ተቀባይ እንዲያደርጉ፣ እናም እንደ ብልህ መጋቢም ይረጋገጥላቸው ዘንድ ነው።

፳፫ እናም አሁን፣ እነሆ፣ ይህም፣ በተመሰረተችበት በማንኛውም ምድር ውስጥ፣ ለቤተክርስቲያኔ ቅርንጫፎች ሁሉ ምሳሌ ይሆናል። እናም አሁን፣ የምለውን አበቃለሁ። አሜን።

፳፬ ስለቤተክርስቲያኗ አባላት፣ ከመንግስት ህግጋት በተጨማሪም ጥቂት ቃላት—በመንፈስ ቅዱስ ወደ ፅዮን እንዲሄዱ የተመደቡት፣ እናም ወደ ፅዮን ለመጓዝ እድለኛም የሆኑት—

፳፭ ከቤተክርስቲያኗ ሶስት ሽማግሌዎች፣ ወይም ከኤጲስ ቆጶስ የምስክር ወረቀትን፣ ለኤጲስ ቆጶሱ ይውሰዱ፤

፳፮ አለበለዚያም ወደ ፅዮን ምድር የሚሄደውም እንደ ብልህ መጋቢ አይረጋገጥለትም። ይህም ደግሞ ምሳሌ ነው። አሜን።