ክፍል ፳፩
ሚያዝያ ፮፣ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በፈየት፣ ኒው ዮርክ፣ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። ራዕዩ የተሰጠው ቤተክርስቲያኗ በተደራጀችበት ቀን በዴቭድ ዊትመር ቀዳማዊ፣ ቤት ውስጥ ነበር። ቀደም ብለው የተጠመቁት ስድስት ሰዎች ተሳትፈዋል። እነዚህ ሰዎች በአንድ ድምጽ እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ለማቋቋም ፍላጎታቸውን እና ውሳኔያቸውን ገልጸዋል (ክፍል ፳ን ተመልክቱ)። ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊን እና ኦሊቨር ካውድሪን እንደ ቤተክርስቲያኗ አመራር ለመቀበል መርጠዋል። እጅ በመጫን ጆሴፍ ኦሊቨርን ለቤተክርስቲያን ሽማግሌነት ሾሞታል ኦሊቨር በተመሳሳይ ሁኔታ ጆሴፍን ሾሞታል። ከቅዱስ ቁርባን ስርዐት በኋላ፣ ጆሴፍ እና ኦሊቨር በእያንዳንዱ ተሳታፊዎች ላይ እጅ በመጫን መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ አድርገዋል እንዲሁም እንደቤተክርስቲያን አባልነት አጽንተዋቸዋል።
፩–፫፣ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ባለራዕይ፣ ተርጓሚ፣ ነቢይ፣ ኃዋሪያ እና ሽማግሌ እንዲሆን ተጠራ፤ ፬–፰፣ የእርሱም ቃል የፅዮንን መነሻ ይመራል፣ ፱–፲፪፣ አጽናኝ በሆነው ሲናገር የሚናገረውን ቅዱሳን ያምናሉ።
፩ እነሆ፣ በመካከላችሁ ሀመዝገብ ይቀመጣል፤ እናም ለባለራዕይ፣ ተርጓሚ፣ ነቢይ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐሐዋርያ፣ በእግዚአብሔር በአብ ፈቃድ እና በጌታህ በኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ የቤተክርስቲያኗ ሽማግሌ ተብለህ ትጠራለህ፣
፪ በመንፈስ ቅዱስ በመመራት መሰረቱን ለመጣል ሀበመነሳሳት፣ እናም ወደተቀደሰ እምነት ትገነባው ዘንድ ተጠርተሀል
፫ ሀቤተክርስቲያኗ በጌታ ዓመት በአስራ ስምንት መቶ ሰላሳኛው ሚያዚያ ተብሎ በሚጠራው አራተኛው ወር በስድስተኛው ቀን ለተመሰረተች።
፬ ስለዚህ፣ በፈቴ ሀበቅድስና በመራመድ የሚቀበላቸውን ለቃላቱን እና ትእዛዛቶቹን እናንት የቤተክርስቲያኗ አባላት ታደምጣላችሁ፤
፭ ሀቃሉን ልክ ከእኔ አንደበት እንደወጣ አድርጋችሁ ሁሉ ትዕግስት እና እምነት ትቀበላላችሁ።
፮ ምክንያቱም ይህንን ስታደርጉ የሲዖል ሀደጆችም አያሸንፏችሁም፤ አዎን እናም ጌታ አምላክ ለየጭለማን ኃይል ከላያችሁ ላይ ይገፋል እናም ለእናንተ ጥቅም እና ለስሙ ሐክብር ሰማያት መእንዲንቀጠቀጡ ያደርጋል።
፯ ጌታ አምላክ እንዲህ ይላል፥ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ሀየፅዮንን መሰረት ለማስፋት በታላቅ ኃይል አነሳስቼዋለሁ፣ እናም ትጋቱን አውቃለሁ፣ እንዲሁም ጸሎቱን ሰምቻለሁ።
፰ ለፅዮን የሚያለቅሰውን ልቅሶ ተመልክቼአለሁ፣ እናም ለእርሷ ካሁን በኋላ እንዳያዝን አደርገዋለሁ፣ ለኃጢአቱ ሀስርየት የሚደሰትበት እና በረከቴ በስራው ላይ የሚገለጥበት ቀን መጥቷል።
፱ ስለሆነም፣ እነሆ፣ ሀበወይኑ ስፍራዬ የሚሰሩትን በታላቅ በረከት ለእባርካቸዋለሁ፣ እና እነርሱም ሐበኃጢአተኛ ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስ መለአለም ኃጢአት፣ አዎን፣ ኃጢአት ስርየት ሠልባቸውን ለሚያዋርዱ ረእንደተሰቀለ በእኔ በኩል ሰበአጽናኙ ሸበሚሰጡት ቃሉ ያምኑታል።
፲ ስለዚህ በአንተ በሐዋሪያዬ በኦሊቨር ካውድሪ ሀእንዲሾም ፍቃዴ ነው፤
፲፩ በ እሱ እጅ ሽማግሌ ስለሆንክ እርሱ ለአንተ ሀየመጀመሪያ ስለሆነ ስሜን በመሸከም ለዚህች የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሽማግሌ ትሆን ዘንድ ይህ ለአንተ ስርዐት ነው።
፲፪ እናም ለቤተክርስቲያኗ ለዚህ ቤተክርስቲያን፣ እናም በአለም ፊት፣ አዎን፣ በአህዛብ ፊት፤ የመጀመሪያ ሰባኪ ትሆን ዘንድ፤ አዎን፣ ሀለአይሁድም እንዲሁ ሰባኪ ትሆናለህ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። አሜን።