ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፷፩


ክፍል ፷፩

በነሀሴ ፲፪፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በመክኢልዋኢን መታጠፊያ፣ በሚዙሪ ወንዝ ዳርቻ ላይ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። ወደ ከርትላንድ በሚመለሱበት ጉዞ ነቢዩ እና አስር ሽማግሌዎች በሚዙሪ ወንዝ ላይ በታንኳዎች ተጉዘው ነበር። በጉዞአቸው ሶስተኛው ቀን ብዙ አደገኛ አጋጣሚዎች ነበሯቸው። ሽማግሌ ዊልያም ደብሊው ፌልፕስ፣ በቀን ራዕይ፣ አጥፊው በውሀ ገጽ ላይ በሀይል ሲንሳፈፍ አየው።

፩–፲፪፣ ጌታ በውሀዎች ላይ ብዙ ጥፋቶችን አውጇል፤ ፲፫–፳፪፣ ውሀዎች በዮሐንስ ተረግመዋል፣ እናም አጥፊው በእነዚህ ገጾች ላይ ይንሳፈፋል፤ ፳፫–፳፱፣ አንዳንዶች ውሀዎችን ለማዘዝ ሀይል አላቸው፤ ፴–፴፭፣ ሽማግሌዎች ሁለት በሁለት ይጓዙ እናም ወንጌልን ይስበኩ፤ ፴፮–፴፱፣ ለሰው ልጅ መመለስም ይዘጋጁ።

እነሆ፣ እናም ሁሉም ሀይል ያለውን፣ ከዘለአለም እስከ ዘለአለም የሆነውን፣ እንዲሁም አልፋና ኦሜጋ፣ የመጀመሪያና የመጨረሻውን የእርሱን ድምፅ አድምጡ።

እነሆ፣ እኔ ጌታ ኃጢአቶችን ስለምሰርይ፣ እና ኃጢአታቸውን በትሁት ልብ ለሚናዘዙት በምህረት የተሞላሁ ስለሆንኩ፣ ኃጢአታችሁ የተሰረየላችሁ፣ በዚህ ስፍራ የተሰበሰባችሁ የቤተክርስቲያኔ ሽማግሌዎች ሆይ፣ ጌታ እንዲህ ይላችኋል፤

ነገር ግን እንዲህ እላችኋለሁ፣ በዳርቻዎቹ ያሉት ኗሪዎች እምነት በማጣት እየጠፉ እያሉ፣ እነዚህ ሁሉም ሽማግሌዎቼ በውሀ ላይ በፍጥነት መጓዝ አያስፈልጋቸውም።

ይሁን እንጂ፣ ይህን የፈቀድኩት እናንት ምስክር እንድትሰጡ ነው፤ እነሆ፣ በውሀዎች ላይ፣ እና ከዚህ በኋላም ተጨማሪ ብዙ አደጋዎች አሉ፤

እኔ ጌታ፣ በቁጣዬ በውሀዎች ላይ ብዙ ጥፋቶችን አውጄአለሁ፤ አዎን፣ በተለይም በእነዚህ ውሀዎች ላይ።

ይሁን እንጂ፣ ሁሉም ስጋ በእጄ ነው፣ እናም ከመካከላችሁ ታማኝ የሆነው በውሀዎች አይጠፋም።

ስለዚህ፣ አገልጋዬ ስድኒ ጊልበርት እና አገልጋዬ ውልያም ደብሊው ፌልፕስ ወደ ጥሪአቸው እና ተልዕኮአቸው በፍጥነት መሄዳቸው አስፈላጊ ነው።

ይሁን እንጂ፣ አንድ እንድትሆኑ፣ በክፋትም እንዳትጠፉ፣ ለኃጢአታችሁ ሁሉ ከመገሰጻችሁ በፊት እንድትሄዱ አልፈቅድም፤

አሁን ግን፣ እንዲህ እላለሁ፣ መሄዳችሁ ፍቃዴ ነው። ስለዚህ፣ አገልጋዮቼ ስድኒ ጊልበርት እና ዊልያም ደብሊው ፌልፕስ በፊት አብረዋቸው የነበሩትን ይውሰዱ፣ እናም ተልዕኮአቸውን ለማሟላትም በፍጥነት ጉዞአቸውን ይጀምሩ፣ እናም በእምነትም ይቋቋማሉ፤

እናም ታማኝ ከሆኑም ይጠበቃሉ፣ እና እኔ፣ ጌታም፣ ከእነርሱ ጋር ነኝ።

፲፩ እናም የሚቀሩት ለልብስ የሚያስፈልገውን ይውሰዱ።

፲፪ አገልጋዬ ስድኒ ጊልበርትም፣ እንደተስማማችሁበት፣ አስፈላጊ ያልሆኑትን ይውሰድ።

፲፫ እናም አሁን፣ እነሆ፣ ስለእነዚህ ነገሮች በተመለከተ ትእዛዝን የምሰጣችሁ ለጥቅማችሁ ነውና፤ እናም እኔ ጌታ፣ እንደ ቀደሙት ቀናት ከሰዎች ጋር እንዳደረግሁ አነጋግራችኋለሁ።

፲፬ እነሆ፣ እኔ ጌታ በመጀመሪያ ውሀዎችን ባረኩአቸው፤ ነገር ግን በመጨረሻዎቹም ቀናት፣ በአገልጋዬ ዮሐንስ አንደበትም ውሀዎችን ረገምኩ

፲፭ ስለዚህ፣ ማንኛውም ስጋ በውሀዎች ላይ ደህና የማይሆንበት ቀናት ይመጣሉ።

፲፮ እና በመጪዎቹ ቀናትም፣ ልቡ ቅን ከሆነው በስተቀር፣ ማንም ወደ ፅዮን ምድር በውሀዎች ላይ ለመጓዝ አይችልም ይባላል።

፲፯ እናም፣ እኔ ጌታ በመጀመሪያው ምድርን እንደረገምኩት፣ እንዲሁም በመጨረሻዎቹም ቀናት፣ በጊዜውም ለቅዱሳን ጥቅም፣ ከዚህም ስቡን እንዲካፈሉ ባርኬዋለሁ።

፲፰ እና አሁንም ለአንዱ የተናገርኩትን ለሁሉም እንደተናከርኩ፣ እምነታቸው ወድቆ እና እንዳይጠመዱ፣ ስለእነዚህ ውሀዎች ወንድሞቻችሁን እንድታስጠነቅቁ ትእዛዝን እሰጣችኋለሁ፤

፲፱ እኔ ጌታ አውጄአለሁ፣ እናም አጥፊውም በዚህ ፊት ይንሳፈፋል፣ እናም አዋጁን አልሽርም።

ትላንትና፣ እኔ ጌታ፣ ተቆጥቼአችሁ ነበር፣ ነገር ግን ዛሬ ቁጣዬ ከእናንተ ተመልሷል።

፳፩ ስለዚህ፣ በፍጥነት እንዲጓዙ የነገርኳቸውም—ደግሞም እንዲህ እላችኋለሁ፣ ጉዞአቸውን በፍጥነት ይጀምሩ።

፳፪ እናም ከትንሽ ጊዜ በኋላ፣ ተልዕኮአቸውን እስካሟሉ ድረስ፣ በውሀም ይሁን በምድር መሄዳቸው በእኔ ዘንድ ለውጥ አያመጣም፤ ከዚህም በኋላ እንዲያውቁት እንደተደረገው እንደ ውሳኔአቸው ይሁን።

፳፫ እናም አሁን፣ አገልጋዮቼን ስድኒ ሪግደንን፣ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊን፣ እና ኦሊቨር ካውድሪ ን በተመለከተም፣ ወደ ቤቶቻቸው ሲጓዙ፣ በመስኖ ላይ ካልሆነ በስተቀር፣ ደግመው በውሀዎች እንዳይመጡ፤ ወይም በሌላ አባባልም በመስኖ ካልሆነ በስተቀር በውሀዎች አይጓዙ።

፳፬ እነሆ፣ እኔ ጌታ ለቅዱሳኔ የመጓዣ መንገድን ሰጥቻቸዋለሁ፤ እናም እነሆ፣ ይህም መንገዱ ነው—እንዲጓዙ እና ወደፅዮን ምድር እንዲሄዱ ትእዛዝ እስከተሰጣቸው ድረስ፣ ከመስኖው ከወጡ በኋላ፣ በምድር ይጓዛሉ፤

፳፭ እናም፣ በመንገዱም ድንኳኖቻቸውን በመትከል፣ እንደ እስራኤል ልጆችም ያደርጋሉ።

፳፮ እናም፣ እነሆ፣ ይህም ለወንድሞቻችሁ ሁሉ የምትሰጡት ትእዛዝ ነው።

፳፯ ይሁን እንጂ፣ ለአንዱ ውሀዎችን ለማዘዝ ሀይል ተሰጥቶታል፣ ለሌላውም በመንፈስ መንገዶቹን ሁሉ እንዲያውቅም ተሰጥቶታል፤

፳፰ ስለዚህ፣ ከዚህ በኋላ የሚሆነው በእኔ ስለሚወሰን፣ በምድርም ይሁን ወይም በውሀ ላይ፣ የህያው እግዚአብሔር መንፈስ እንደሚመራው ያድርግ።

፳፱ እናም ለእናንተም የቅዱሳኑ መንገድ፣ ወይም የጌታ ሰራዊት ቅዱሳን መጓዣ መንገድ ተሰጥቷችኋል።

እና ደግሞም፣ በእውነት እላችኋላሁ፣ ስንሰናቲ እስኪደርሱ ድረስ፣ አገልጋዮቼ ስድኒ ሪግደን፣ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ፣ እና ኦሊቨር ካውድሪ በኃጢአተኞቹ ጉባዔዎች መካከል አንደበቶቻቸውን አይክፈቱ፤

፴፩ እና በዚያም ስፍራ ወደ እግዚአብሔር፣ አዎን፣ በኃጢአታቸው ምክንያት ንዴቱ ወደተቀጣጠለው፣ በእነዚያ ሰዎች፣ ለጥፋትም በደረሱት ሰዎች ላይ፣ ድምጻቸውን ከፍ ያደርጋሉ።

፴፪ እና ከእዚያም ወደ ወንድሞቻቸው ጉባኤዎች ይጓዙ፣ እንዲሁም አሁን አግልግሎታቸው ከኃጢአተኞቹ ጉባኤ በላይ በእነርሱ መካከል በጣም የሚፈለግ ነውና።

፴፫ እናም አሁን፣ የሚቀሩትን በተመልከተ፣ ይጓዙ እናም፣ እንደሚሰጣቸውም፣ በኃጢአተኞቹ ጉባኤ መካከልም ቃልን ይስበኩ

፴፬ እናም ይህን እስካደረጉ ድረስ ልብሳቸውን ያጸዳሉ፣ እናም በፊቴም እንከን አይኖራቸውም።

፴፭ እናም አብረው፣ ወይም መልካም እንደሚመስላቸው፣ ሁለት በሁለት ሆነውም ይጓዙ፣ የተደሰትኩባቸውን አገልጋዬ ሬኖርልድስ ካሁን እና አገልጋዬ ሳሙኤል ኤች ስሚዝ ብቻ ወደ ቤቶቻቸው እስከሚመለሱ ድረስ አይለያዩ፣ እና ይህም በእኔ የላቀ ጥበብ እቅድ ነው።

፴፮ እና አሁን፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እናም ለአንዱ የተናገርኩትን ለሁሉ እንደምናገር ነው፣ ህጻናት ሆይ፣ ተደሰቱ፤ በመካከላችሁ ነኝ፣ እናም አልተውኳችሁምና

፴፯ እናም ራሳችሁን በፊቴ ዝቅ እስካደረጋችሁ ድረስ፣ የመንግስቱ በረከቶች የእናንተ ናቸው።

፴፰ የሰው ልጅ መምጣትን እየጠበቃችሁ፣ ታጠቁ፣ እናም የነቃችሁ ሁኑ፣ እናም በመጠንም ኑሩ፣ ባላሰባችሁበት ሰዓት ይመጣልና።

፴፱ ወደ ፈተናም እንዳትገቡ፣ የሚመጣበትን ቀን በህይወት ወይም በሞት መታገስ ትችሉ ዘንድ ዘወትር ጸልዩ። እንዲህም ይሁን። አሜን።