ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፵፱


ክፍል ፵፱

በግንቦት ፯፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ ለስድኒ ሪግደን፣ ለፓርሊ ፒ ፕራት፣ እና ለሊመን ኮፕሊ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ሊመን ኮፕሊ ወንጌልን ተቀብሎ ነበር፣ ነገር ግን ቀደም ሲል አባል የነበረበትን የሼከሮቹን [የተወዛዋዦቹ] (ዩናይትድ ሶሳይቲ ኦፍ ብሊቨርስ እን ክራይስትስ ሰክንድ አፒሪንግ [በክርስቶስ ዳግም ምፅዓት የሚያምኑ የአንድነት ህብረተሰብ]) አንዳንድ ትምህርቶችን ይዞ ነበር። አንዳንዶቹ የሼከሮቹ እምነቶች የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ቀደም ሲል እንደተከሰተ፣ እና አን ሊ በምትባል ሴት አምሳል እንደተገለጠ ነበር። የውሀ ጥምቀት እንደ አስፈላጊ ድርገት አይመለከቱትም ነበር። ጋብቻን አስወግደው፣ ግብረ ስጋ በማይፈጸምበት ኑሮ ያምኑ ነበር። አንዳንድ ሼከሮችም ስጋ መብላትን ይከለክሉ ነበር። ለዚህ ራዕይ መቅድምም፣ የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ እንዲህ ይገልጻል፣ “ስለ ርዕሱ ፍጹም እውቀት ለማግኘት፣ ጌታን ጠየቅሁ፣ እናም የሚከተለውን ተቀበልሁ።” ራዕዩም የሼከሮቹ ቡድን መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦችን ያፈርሳል። ከዚህ በፊት የተጠቀሱት ወንድሞችም ይህን ራዕይ (ክሊቭላንድ ኦሀዮ አካባቢ ላለው) ወደ ሼከሮቹ ማህብረሰብ ወስዱት፣ እና ለእነርሱም ሁሉንም አነበቡላቸው፣ ነገር ግን አልተቀበሉትም ነበር።

፩–፯፣ የክርስቶስ ምጽአት ቀንና ሰአት እርሱ እስከሚመጣ ድረስ አይታወቅም፤ ፰–፲፬፣ ደህንነትን ለማግኘት፣ ስዎች ንስሀ መግባት፣ በወንጌሉ ማመን፣ እና ስርዓቶችን ማክበር አለባቸው፤ ፲፭–፲፮፣ ጋብቻ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ነው፤ ፲፯–፳፩፣ ስጋን መመገብ የተፈቀደ ነው፤ ፳፪–፳፰፣ ከክርስቶስ የዳግም ምፅአት በፊት፣ ፅዮን ትበለፅጋለች እና ላማናውያንም እንደ ፅጌረዳ ያብባሉ።

አገልጋዮቼ ስድኒ፣ ፓርሊ፣ እና ሊመን ቃሌን አድምጡ፤ እነሆም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ የተቀበላችሁትን ወንጌሌን፣ እንደተቀበላችሁ እንዲሁ፣ ወደ ሼከሮቹ ሄዳችሁ እንድትሰብኩላቸው ትእዛዝን እሰጣችኋለሁ።

እነሆ፣ እላችኋለሁ፣ ሙሉ እውነትን ሳይሆን ከፈሉን ብቻ ለማወቅ ይሻሉ፣ ንስሀ መግባትም አለባቸው እና በፊቴ ትክክል አይደሉምና።

ስለዚህ፣ አገልጋዮቼ ስድኒን እና ፓርሊን፣ ወንጌልን እንድትሰብኩላቸው እሰዳችኋለሁ።

ከእነርሱ በተቀበላቸው ሳይሆን፣ በእናንተ በአገልጋዮቼ በኩል በሚማራቸው በኩል እነርሱን በሚገባ እንዲያስረዳ አገልጋዬ ሊመንም ለዚህ ስራ ይሾማል፤ ይህን በማድረግም እባርከዋለሁ፣ አለዚያም አይበለጽግም።

ጌታ እንዲህም ይላል፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ እና አንድያ ልጄን ለአለም ቤዛነት ወደ አለም ልኬአለሁ፣ እና እርሱን የሚቀበልው ይድናል፣ እናም እርሱንም ያልተቀበለው ይኮነናል ብዬ እደነግጋለሁና—

እናም የሰውን ልጅም የወደዱትን ሁሉ አደረጉበት፤ እና ሀይሉንም በክብሩ ቀኝ በኩል ወስዷል፣ እናም አሁንም በሰማያት ነግሷል፣ እናም በምድር ላይ ወርዶ ሁሉንም ጠላቶች ሁሉ ከእግሩ በታች እስከሚያደርጋቸው ጊዜ ድረስም ይነግሳል፤ እና ይህም ጊዜ ተቃርቧል—

እኔ፣ ጌታ አምላክ፣ ይህን ተናግሬአለሁ፤ ነገር ግን ሰአቱንና ቀኑን የሰማይ መላእክትም ይሁን ሰው የሚያውቅ የለም፣ እስከሚመጣም ድረስ አያውቁትም።

ስለዚህ፣ ለራሴ ካስቀረኋቸው፣ ከማታውቋቸው ቅዱሳን ሰዎች በስተቀር፣ ሁሉም ኃጢአተኞች ስለሆኑ፣ ሁሉም ሰዎች ንስሀ ይገቡ ዘንድ ፍቃዴ ነው።

ስለዚህ፣ እላችኋለሁ ከመጀመሪያ ጊዜ ጀምሮ የነበረውን ዘለአለማዊ ቃል ኪዳኔን ለእናንተ ልኬላችኋለሁ።

እናም ቃል የገባሁትን ፈጽሜአለሁ፣ እና የምድር ህዝብ ለዚህ ይሰግዳሉ፤ እናም፣ በራሳቸውም ካላደረጉት፣ በሀይል ዝቅ ይላሉ፣ አሁን ራሳቸውን ከፍ ከፍ ያደረጉትም በሀይል ይዋረዳሉና።

፲፩ ስለዚህ፣ በእነዚህ ህዝብ መካከል እንድትሄዱና፣ ስሙ ጴጥሮስ እንደነበረው እንደ ቀደመው ሐዋርያዬ፣ እንዲህም እንድትሏቸው ትእዛዝን እሰጣችኋለሁ፥

፲፪ በመጀመሪያውና በመጨረሻው፣ በምድር ላይ በነበረው፣ እና ተመልሶም በሚመጣው፣ በጌታ ኢየሱስ ስም እመኑ፤

፲፫ በቅዱስ ትእዛዝ መሰረት፣ ለኃጢአቶች ስርየት፣ ንስሐ ግቡ እናም በኢየሱስ ክርስቶስም ስም ተጠመቁ፤

፲፬ ይህን የሚያደርጉም በቤተክርስቲያኗ ሽማግሌዎች እጆችን በመጫን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ይቀበላሉ።

፲፭ እናም ዳግም፣ እንዲህ እላችኋለሁ፣ ጋብቻን የሚከለክል በእግዚአብሔር የተሾመ አይደለም፣ ጋብቻ ለሰው ከእግዚአብሔር የተሰጠ ነውና።

፲፮ ስለዚህ፣ ሰው አንዲት ሚስት እንድትኖረው ህግ ነው፣ እናም ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ፣ እናም ይህም የሆነው ምድር የተፈጠረችበትን አላማ ታሟላ ዘንድ ነው፤

፲፯ እናም ምድር ከመፈጠሯ አስቀድሞ እንደፍጥረቱ፣ ምድር በተመደበላት የሰው ቁጥርም ትሞላ ዘንድ ነው።

፲፰ እናም ሰውን ስጋ እንዳይበላ፣ ከስጋም እንዲለይ የሚከለክል በእግዚአብሔር የተሾመ አይደለም፤

፲፱ ስለሆነም፣ የምድር አራዊት እና የሰማይ አዕዋፋት እና በምድር የሚበቅለውም፣ ለሰው ምግብና ልብስ ጥቅም፣ እናም በበቂም እንዲኖረው የተመደበ ነው።

ነገር ግን አንድ ሰው ከሌላው በላይ እንዲኖረው አልተሰጠም፣ ስለዚህም አለም በኃጢአት ወድቃለች።

፳፩ ሳያስፈልገው፣ ደምን ለሚያፈሰው ወይም ስጋን ለሚያባክነው ሰው፣ ወዮለት።

፳፪ እና ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ የሰው ልጅ የሚመጣው በሴት ወይም በምድር በሚጓዝ ሰው አምሳል አይደለም።

፳፫ ስለዚህ፣ አትታለሉ፣ ነገር ግን ጸንታችሁ ቆዩ፣ ሰማያት የሚንቀጠቀጡበትን፣ እና ምድርም እንደሰካራም የምትንቀጠቀጥበትን እና ወዲህና ወዲያ የምትናወጥበትን፣ እና ሸለቆዎችም ከፍ ከፍ የሚሉበትን፣ እና ተራራዎችም ዝቅ የሚሉበትን፤ ስርጉጥጓጡም ሜዳ የሚሆንበትን ይህንን ጠብቁ—እና ይህ ሁሉ የሚሆነውም መላዕክቱ መለከቱን ሲነፋ ነው።

፳፬ ነገር ግን የጌታ ታላቅ ቀን ከመምጣቱ በፊት፣ ያዕቆብ በዱር ይበለፅጋል፣ እና ላማናውያንም እንደ ፅጌረዳ ያብባሉ

፳፭ ፅዮንም በኮረብታዎች ላይ ትበለፅጋለች እናም በተራራዎችም ላይ ሀሴትን ታደርጋለች፣ እናም በመረጥኩትም ስፍራ ላይ አብራ ትሰበሰባለች።

፳፮ እነሆ፣ እንዲህ እላችኋለሁ፣ እንዳዘዝኳችሁ ሂዱ፤ ለኃጢአታችሁ ሁሉ ንስሀ ግቡ፤ ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችሁማል።

፳፯ እነሆ፣ ከፊታችሁ እሄዳለሁ እናም እከተላችኋለሁ፤ እና በመካከላችሁ እሆናለሁ፣ እና እናንተም አታፍሩም

፳፰ እነሆ፣ እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ፣ በቶሎም እመጣለሁኝ። እንዲህም ይሁን። አሜን።