ክፍል ፴
መስከረም ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በፈየት ኒው ዮርክ በነቢዩ ጆሴፍ አማካይነት ከሶስት ቀን ጉባዔ በኋላ፣ ግን የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች ከመለያየታቸው በፊት፣ ለዴቪድ ዊትመር፣ ለፒተር ዊትመር ዳግማዊ፣ እና ለጆን ዊትመር የተሰጠ ራዕይ። ይህ ጽሁፍ በመጀመሪያ የታተመው እንደ ሶስት ራዕይዎች ነበር፣ ይህም በ፲፰፻፴፭ (እ.አ.አ.) ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ቅጂ ውስጥ በነቢዩ በአንድ ክፍል ውስጥ ተካትተው ነበር።
፩–፬፣ ዴቪድ ዊትመር በትጋት ባለመስራቱ ተገሰጸ፤ ፭–፰፣ ፒተር ዊትመር ዳግማዊ ከኦሊቨር ካውድሪ ጋር ወደላማናውያን ተልዕኮ ይሂድ፤ ፱–፲፩፣ ጆን ዊትመር ወንጌልን እንዲሰብክ ተጠራ።
፩ እነሆ፣ ሀዴቪድ እንዲህ እልሀለሁ፣ ሰውን ለበመፍራት ለጥንካሬ በእኔ ሐመደገፍ ያለብህን ያህል አልተደገፍክም።
፪ ነገር ግን አዕምሮህ በእኔ በፈጣሪህ ነገር እንዲሁም በተጠራህበት አገልግሎት ላይ ከመሆን ይልቅ ሀበምድር ነገሮች ላይ ሆኗል፤ እናም መንፈሴን እና ከአንተ በላይ ስልጣን የተሰጣቸውን አላደመጥክም፣ ነገር ግን እኔ ባላዘዝኳቸው ተወስደሀል።
፫ ስለዚህ፣ ከእጄ ለራስህ እንድትጠይቅ ተትተሀል፣ እናም ስለተቀበልካቸውም ነገሮች ሀአሰላስል።
፬ እናም ተጨማሪ ትእዛዛትን እስከምሰጥህ ድረስ መኖሪያህ በአባትህ ቤት ይሆናል። በቤተክርስቲያኗ ውስጥ እናም በአለም ፊት እና በአካባቢው ባሉት ዙሪያዎች ሀአገልግሎትን ትሰጣለህ። አሜን።
፭ እነሆ ሀፒተር፣ እንዲህ እልሀለሁ፣ ከወንድምህ ከኦሊቨር ጋር ለትጓዛለህ፤ ወንጌሌን ለማወጅ አንደበትህን ትከፍት ዘንድ ለእኔ አስፈላጊ የሚሆንበት ሐወቅት መጥቷል፤ ስለዚህ አትፍራ፣ ነገር ግን ወንድምህ የሚሰጥህን ምክር እና ቃላት መአድምጥ።
፮ እናም በስቃዩ ሁሉ ከእርሱ ጋር ሁን፣ ለአንተ እና ለእርሱ ደህንነት በጸሎት እና በእምነት ዘወትር ልብህን ወደ እኔ አንሳ፤ ሀበላማናውያን መካከል ለቤተክርስቲያኔን እንዲገነባ ኃይልን ሰጥቼዋለሁና፤
፯ እናም ከወንድሙ፣ ከጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ በቀር በእርሱ ሀላይ ማንንም የቤተክርስቲያኗን ነገሮች በተመለከተ የእርሱ አማካሪ እንዲሆን አልሾምኩም።
፰ ስለዚህ፣ እነዚህን ነገሮች አድምጥ እናም ትእዛዛቴን በመጠበቅ ትጋ፣ እናም በዘለአለማዊ ህይወት ትባረካለህ። አሜን።
፱ እነሆ፣ አገልጋዬ ጆን እንዲህ እልሀለሁ እንደመለከት ሀድምጽ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ወንጌሌን ለማወጅ ትጀምራለህ።
፲ እናም አገልግሎትህም ከእዚያ እንድትሄድ ትእዛዝ እስክሰጠህ ድረስ በወንድምህ በፊልፕ በሮው ስፍራና በአካባቢው፣ አዎን፣ እንዲሁም ድምጽህ በሚሰማበት ስፍራ ሁሉ ይሆናል።
፲፩ እናም ከዚህ ጊዜ ጀምሮም በሙሉ ነፍስህ አገልግሎትህ ሁሉ በፅዮን ይሆናል፤ አዎን፣ ሀሰው ሊያደርግ የሚችለውን ለሳትፈራ ለእኔ ስራ ዘወትር አንደበትህን ትክፍታለህ፣ እኔም ዘወትር ከአንተ ሐጋር እሆናለሁና። አሜን።