ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፹፮


ክፍል ፹፮

በታህሳስ ፮፣ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ነቢዩ ይህን ራዕይ የተቀበለው የመፅሐፍ ቅዱስ ትርጉም ያልታተመ ጽሁፍን ሲገመግም እና ሲያርም ነበር።

፩–፯፣ ጌታ ስለስንዴ እና እንክርድ ምሳሌ ትርጉም ሰጠ፤ ፰–፲፩፣ በስጋ መሰረት ህጋዊ ወራሾች ለሆኑት የሚመጣውን የክህነት በረከቶች ገለፀ።

ስለስንዴ እና እንክርድ ምሳሌ በሚመለከት በእውነት ለእናንተ አገልጋዮቼ ጌታ እንዲህ ይላል፥

እነሆ፣ በእውነት እላለሁ፣ እርሻው አለም ሲሆን፣ እናም ሐዋርያትም ዘሩን የዘሩት ነበሩ፤

እናም ካንቀላፉ በኋላ የቤተክርስቲያኗ አሳዳጅ፣ ከሀዲ፣ ጋለሞታ፣ እንዲሁም አህዛብን የእርሷን ጽዋ እንዲጠጡ የምታደርገው ባቢሎን፣ በልቧም ጠላት፣ እንዲሁም ሰይጣን፣ ለመንገስ የተቀመጠው—እነሆ እርሱም እንክርዳዶችን ይዘራል፤ ስለዚህ፣ እንክርዳዶቹም ስንዴውን ያንቃሉ፣ እናም ቤተክርስቲያኗ ወደበረሀ እንድትበር ያደርጋታል።

ነገር ግን፣ እነሆ፣ በመጨረሻ ቀናት፣ እንዲሁም ጌታ ቃልን በሚያመጣበት ጊዜ፣ እና ስለትቱም እያቆጠቆጠ ነው እናም ገና እየለመለመም ነው—

እነሆ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ሄደው እርሻውን ለማጨድ ተዘጋጅተው የሚጠባበቁ መላእክት ወደ ጌታ በቀን እና በማታ ይለምናሉ፤

ነገር ግን ጌታ እንዲህ ይላቸዋል፣ ስለቱ ገና እየለመለመ እያለ እንክርዳዶችን አትንቀሉ (በእውነት እምነታችሁ ደካማ ነውና)፣ አለበለዚያም ስንዴውንም ደግማችሁ ታጠፉታላችሁና።

ስለዚህ፣ መከሩ ሁሉ እስከሚያብብ ድረስ ስንዴዎቹ እና እንክርዳዶቹ አብረው ይደጉ፤ ከዚያም መጀመሪያ ስንዴዎቹን ከእንክርዳዶቹ መካከል ስብስቡ፣ እናም ስንዴዎቹ ከተሰበሰቡ በኋላ፣ እነሆ እናም አስተውሉ፣ በነዶው ታስረዋል፣ እናም እርሻውም ለመቃጠል ይቀራል።

ስለዚህ፣ በአባቶቻችሁ ዘር ክህነት ለሚቀጥሉላችሁ ጌታ እንዲህ ይላችኋል—

እናንተ፣ በስጋ መሰረት ህጋዊ ወራሾች ናችሁና፣ እናም በእግዚአብሔር ውስጥ ከክርስቶስ ጋር ከአለም ተሰውራችኋል

ስለዚህ ህይወታችሁ እና ክህነቱ ይቀራሉ፣ እናም በእናንተም እና በዘራችሁም አለም ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ በሁሉም ቅዱሳን ነቢያት አንደበት የተነገሩት ሁሉም ነገሮች በዳግም እስከሚመለሱ ድረስም መቅረት ያስፈልጋቸዋናል።

፲፩ ስለዚህ፣ በመልካምነት፣ ለአህዛብ ብርሀን ሆናችሁ፣ እና በዚህ ክህነት በኩልም የህዝቤ እስራኤል አዳኝ በመሆን ከቀጠላችሁ የተባረካችሁ ናችሁ። ጌታ ይህን ብሎታል። አሜን።