ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፺፭


ክፍል ፺፭

በሰኔ ፩፣ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ኦሀዮ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ይህ ራዕይ የማምለኪያ እና የመማሪያ ቤት፣ በልዩም የጌታ ቤት፣ እንዲሰሩ ቀጣይ መለኮታዊ መመሪያ የተሰጠበት ነው (ክፍል ፹፰፥፻፲፱–፻፴፮ን ተመልከቱ)።

፩–፮፣ ቅዱሳን የጌታን ቤት ለመስራት ባሳዩት ድክመት ይገሰጻሉ፤ ፯–፲፣ ጌታ ቤቱን በመጠቀም ህዝቡን ከላይ ሀይልን ሊያለብሳቸው ይፈልጋል፤ ፲፩–፲፯፣ ቤቱም የማምለኪያ ቦታ እና ለሐዋርያት ትምህርት ቤት እንዲሆን ይቀደስ።

በእውነት ለምወዳችሁ ለእናንተ ጌታ እንዲህ ይላል፣ እና የምወዳቸውንም ኃጢአታቸውን ለመሰረይ እገስጻቸዋለሁ፣ በቅጣትም ከፈተና በሁሉም ነገሮች የሚድኑበትን መንገድ አዘጋጃለሁና፣ እና ወድጃችኋለሁም—

ስለዚህ፣ በፊቴ መቀጣት እና መገሰፅ ያስፈልጋችኋል፤

ቤቴን ስለመገንባት የሰጠኋችሁን፣ ታላቅ ትእዛዝ በሁሉም ነገሮች ስላላሰባችሁበት፣ አስከፊ የሆነን ኃጢአት በእኔ ላይ ሰርታችኋልና፤

እንግዳ የሆነን ስራዬን አከናውን ዘንድ፣ በሁሉም ስጋ ለባሽ ላይ መንፈሴን አፈስ ዘንድ፣ ሐዋሪያቴን ለመጨረሻ ጊዜ የወይኑ ስፍራዬን እንዲመለምሉ ለማዘጋጀት ያዘጋጀሁት ንድፍ ታላቅ ትእዛዝ በሁሉም ነገሮች አላሰባችሁበትም፤

ነገር ግን እነሆ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በመካከላችሁ የጠራኋቸው የተሾሙ ብዙ አሉ ነገር ግን የተመረጡት ጥቂቶች ናቸው።

ያልተመረጡትም በጣም አሳዛኝ ኃጢአት ሰርተዋል፣ በዚያም በቀትርም ጊዜ በጨለማ ይሄዳሉ።

እና ለዚህም ምክንያት ጾማችሁ እና ልቅሶአችሁ፣ ወደ ፀባኦት ጌታ፣ ይህም ሲተረጎም የመጀመሪያው ቀን ፈጣሪ፣ የመጀመሪያው እና የመጨረሻው ወደሆነው፣ ወደ እርሱ ጆሮዎች ይመጡ ዘንድ የክብር ስብሰባችሁን እንድትጠሩ ትእዛዝን ሰጠኋችሁ።

አዎን፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ቤትን ትገነቡ ዘንድ ትእዛዝ ሰጠኋችሁ፣ በዚህ ቤትም የመረጥኳቸውን ከላይ መንፈሳዊ ስጦታ ልሰጣችሁ አቅጃለሁ፤

ይህም አብ ለእናንተ የሚገባው ቃል ኪዳን ነውና፤ ስለዚህ እንደ ኢየሩሳሌም ሐዋሪያቴ፣ እንድትቆዩ አዛችኋለሁ።

ይህም ቢሆን፣ አገልጋዮቼ በጣም አሳዛኝ ኃጢአትን ሰርተዋል፤ እና በነቢያት ትምህርት ቤትም አለመስማማት ተነስቷል፤ ይህም ለእኔ በጣም አሳዛኝ ነው ይላል ጌታ፤ ስለዚህ እንዲገሰጹ ላኳቸው።

፲፩ እውነት እላችኋለሁ፣ ቤትን እንድትገነቡ ፍቃዴ ነው። ትእዛዛቴን ብታከብሩ ይህን ለመገንባት ሀይል ይኖራችኋል።

፲፪ ትእዛዛቴን ካላከበራችሁ፣ የአብ ፍቅር ከእናንተ ጋር አይቀጥልም፣ ስለዚህ በጭለማ ትሄዳላችሁ።

፲፫ አሁን ይህ ጥበብ፣ እና የጌታ አዕምሮ ነው—በአለም በሚሰሩበት ሳይሆንም፣ ቤት ይሰራ፣ በአለም አይነት ኑሮ እንድትኖሩ አልሰጠኋችሁምና፤

፲፬ ስለዚህ፣ ለዚህ ሀይል ለምትመድቡት እና ለምትሾሙት ለሶስታችሁ በማሳያችሁ ስርዓት ይሰራ።

፲፭ እና በዚህ ውስጠኛ አደባባይም፣ መጠኑ አስራ ሰባት ሜትር ስፋት ይሁን፣ እና ርዝመቱም ሀያ ሜትር ይሁን።

፲፮ እና የውስጠኛው አደባባይ የታች ክፍል ለቅዱስ ቁርባን ለማቅረብ፣ እና ለስብከታችሁ፣ እና ለጾማችሁ፣ እና ለጸሎታችሁ፣ እና ከሁሉም በላይ የሆነውን ፍላጎታችሁን ለምታቀርቡበት ለእኔ ይቀደስ፣ ይላል ጌታ።

፲፯ እና የውስጠኛው አደባባይ ከፍተኛው ክፍልም ለሐዋሪያቴ ትምህርት ቤት ለእኔ ይቀደስ፣ አለ አህመን ልጅ፤ ወይም በሌላ ቃላት አልፈስ፤ ወይም በሌላ ቃላት፣ ኦሜገስ፤ እንዲሁም ጌታችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ። አሜን።