ክፍል ፸፬
በ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.)፣ በዌይን አውራጃ፣ ኒው ዮርክ፣ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። ቤተክርስቲያኗ ከመደራጀቷ በፊትም፣ ነቢዮ ስለ ርዕሱ መልስ እንዲፈልግ ያደረጉ ስለትክክለኛው የጥምቀት መንገድ ጥያቄዎች ነበሩ። የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ እንደሚገልጸው፣ ይህ ራዕይ የህጻናት ጥምቀት ተቀባይነትን ለማሳየት ሁልጊዜም የሚጠቀሙበትን የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሰት፣ ፩ ቆሮንቶስ ፯፥፲፬ን የሚያብራራ ነው።
፩–፭፣ ጳውሎስ በጊዜው የነበረችውን ቤተክርስቲያን የሙሴን ህግጋትን እንዳታከብር መከረ፤ ፮–፯፣ ህጻናት ልጆች ቅዱስ ናቸው እናም በኃጢአት ክፍያውም የተቀደሱ ናቸው።
፩ ሀያላመነ ባል በሚስቱ ተቀድሶአልና፥ ያላመነችም ሚስት በባልዋ ተቀድሳለች፤ አለዚያ ልጆቻችሁ ርኵሳን በሆኑ ነበር፤ አሁን ግን የተቀደሱ ናቸው።
፪ አሁን፣ በሐዋርያት ዘመን የግርዘት ህግ በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በማያምኑት አይሁዶች ዘንድ ይተገበር ነበር።
፫ እናም እንዲህ ሆነ በህዝብም መካከል የግርዘት ህግን የሚመለከት ታላቅ ሀክርክር ተነስቶ ነበር፣ ያላመነ ባል ልጆቹ ለእንዲገረዙ እና ተፈጽሞ ለነበረውም ለሙሴ ሐህግ ተገዢ እንዲሆን ፍላጎት ነበረውና።
፬ እናም እንዲህም ሆነ፣ ልጆቹም በሙሴ ህግ ተገዢ ሆነው በማደጋቸው፣ የአባቶቻቸውን ሀባህሎች ተከተሉ እናም በክርስቶስም ወንጌል አላመኑም፣ በዚህም ያልተቀደሱ ሆኑ።
፭ ስለዚህ፣ በዚህም ምክንያት ነው ሐዋሪያው ለቤተክርስቲያኗ ከጌታ ሳይሆን ከራሱ፣ በመካከላቸው የሙሴ ሀህግ ካልተሻረ በስተቀር የሚያምኑ ከማያምኑ ጋር ለአንድነት የላቸውምበማለት የጻፈው፣
፮ ልጆቻቸው እንዳይገረዙ፤ እና ይህም በአይሁዶች መካከል ይተገበር ስለነበር፣ ህጻናት ልጆች አይጸደቁም የሚለው ባህልም እንዲቀር የትእዛዝን ፅሑፍ ሰጣቸው፤
፯ ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሀየኃጢአት ክፍያ አማካይነት ለስለተቀደሱ ህጻናት ሐልጆች መየተቀደሱ ናቸው፤ እና ይህም የቅዱሳት መጻህፍት ትርጉም ነው።