ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፸፫


ክፍል ፸፫

በጥር ፲፣ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.)፣ በሀይረም ኦሀዮ ውስጥ፣ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ለስድኒ ሪግደን የተሰጠ ራዕይ። ካለፈው ህዳር መጀመሪያ ጀምሮ፣ ነቢዩ እና ስድኒ ሪግደን በመስበክ ተጠምደው ነበር፣ እናም በዚህም የተነሳ በቤተክርስቲያኗ ላይ ተነስቶ የነበረውን ጥላቻ ለመቀነስ ብዙ ነገሮችን አከናውነው ነበር (የክፍል ፸፩ ርዕስን ተመልከቱ)

፩–፪፣ ሽማግሌዎች በመስበክ ይቀጥሉ፤ ፫–፮፣ ጆሴፍ ስሚዝ እና ስድኒ ሪግደን መፅሀፍ ቅዱስ እስኪገባደድ ድረስ መተርጎምን ይቀጥሉ።

በእውነትም ጌታ እንዲህ ይላልና፣ እስከ ጉባኤ ድረስ ወንጌሌን በመስበክ፣ እናም በአካባቢው ዙሪያ የሚገኙትን ቤተክርስቲያኖችን በማበረታታት ይቀጥሉ ዘንድ ፍቃዴ ነው፤

እና ከዚያም፣ እነሆ፣ በጉባኤው ድምፅ የተለያዩት ተልዕኮአቸው ምን እንደሆኑም ይገለፅላቸዋል።

አሁንም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋዮቼ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ እና ስድኒ ሪግደን፣ ጌታም እንዲህ ይላል፣ ዳግም መተርጎም የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው፤

እናም፣ በተቻለ መጠን፣ እስከ ጉባኤው ድረስም በአካባቢው ዙሪያ ውስጥ ስበኩ፤ እናም ከዚያም ይህም እስኪገባደድ ድረስ የትርጉምን ስራ መቀጠላችሁ አስፈላጊ ነው።

እናም ተጨማሪ እውቀቶች እስከሚሰጣቸው ድረስ፣ እንዲሁም እንደተጻፈው፣ ይህም ለሽማግሌዎች ምሳሌ ይሁን።

አሁን ምንም ተጨማሪ በዚህ ጊዜ አልሰጣችሁም። ወገባችሁን ታጠቁ እናም በመጠን ኑሩ። እንዲህም ይሁን። አሜን።