ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፻፲፯


ክፍል ፻፲፯

በሀምሌ ፰፣ ፲፰፻፴፰ (እ.አ.አ.) በፋር ዌስት ሚዙሪ ውስጥ የውልያም ማርክስ፣ የኒዌል ኬ ዊትኒ፣ እና የኦሊቨር ክሬንጀርን ሀላፊነት በሚመለከት ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ።

፩–፱፣ የጌታ አገልጋዮች ምድራዊ ነገሮችን መመኘት የለባቸውም፣ “ለጌታ ንብረት ምኑ ነውና?”፤ ፲–፲፮፣ የነፍስን አሳንሶ ማየትን ይተዉ፣ እና መስዋዕታቸውም ለጌታ የተቀደሰ ይሆናል።

ለአገልጋዬ ዊልያም ማርክስ፣ እና ለአገልጋዬ ኒዌል ኬ ዊትኒ ጌታ እንዲህ ይላል፣ ጉዳዮቻቸውን በፍጥነት ይፈፅሙ እና እኔ ጌታ በምድር ላይ በረዶ ከመላኬ በፊት ከከርትላንድ ምድር ይጓዙ።

ንቁ፣ እና ተነሱ፣ እና ኑ፣ እናም አትዘግዩ፣ እኔ ጌታ ይህን አዝዤአለሁና።

ስለዚህ ቢዘገዩ ከሆኑ መልካም አይሆንላቸውም።

ለኃጢአታቸው ሁሉ፣ እና ለምኞቶቻቸው ሁሉ በፊቴ ንስሀ ይግቡ ይላል ጌታ፤ ለእኔ ንብረት ምኔ ነው? ይላል ጌታ።

የከርትላንድ ንብረቶችም ለእዳ ይተው፣ ይላል ጌታ። ተዉአቸው፣ ይላል ጌታ፣ እና የሚቀረው ማንኛውም በእጆቻችሁ ይቆይ፣ ይላል ጌታ።

የሰማይን አዕዋፋት፣ እና የባህርን አሶች፣ እና የተራራዎቹ እንስሳት የሉኝምን? ምድርን አልሰራሁምን? የአለም ህዝብ ሰራዊት እጣ ፈንታ አልያዝኩምን?

ስለዚህ፣ ብቸኛ ስፍራዎችን እንዲፈኩ እና እንዲያብቡ፣ እና ብዙም እንዲያፈሩ አላደርግምን? ይላል ጌታ።

በአዳም-ኦንዳይ-አማን ተራራ ላይ፣ እና በኦሌያ ሺኔሀ ሜዳ ላይ፣ ወይም አዳም በኖረበት ምድር ብቁ ስፍራ ስለሌለ ነው ጠብታ የሆነውን የምትመኙት፣ እና ከፍተኛ ተፅዕኖ ያላቸውን ጉዳዮች ችላ የምትሉት?

ስለዚህ፣ ወደዚህ ወደ ህዝቤ ምድር፣ እንዲሁም ወደ ፅዮን ኑ።

አገልጋዬ ውልያም ማርክስ በትንሽ ነገሮች ታማኝ ይሁን፣ እና እርሱም በብዙ ነገሮች መሪ ይሆናል። በፋር ዌስት ከተማ ውስጥ በህዝቤ መካከል ይምራ፣ እና በህዝቤ በረከቶችም ይባረክ።

፲፩ አገልጋዬ ኒውል ኬ ዊትኒ ስለ ኒቆላውያንን ስራ እና ስለ ስውር ርኩሰታቸው ሁሉ፣ እና በፊቴ ነፍስን አሳንሶ ማየትን ሁሉ ይፈር፣ ይላል ጌታ፣ እና ወደ አዳም-ኦንዳይ-አማን ምድር ና፣ እና የህዝቤም ኤጲስ ቆጶስ ሁን፣ ይላል ጌታ፣ በስም ብቻ ሳይሆን በተግባር ይሁን፣ ይላል ጌታ።

፲፪ ደግሞም እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ ኦሊቨር ግሬንጀርን አስታውሳለሁ፤ እነሆ፣ እውነት እለዋለሁ ስሙ ከትውልድ ወደ ትውልድ፣ ለዘለአለም በቅዱስ መታሰቢያ ይያዛል፣ ይላል ጌታ።

፲፫ ስለዚህ፣ ለቤተክርስቲያኔ ቀዳሚ አመራር ደህንነት በቅንነት ይስራ፣ ይላል ጌታ፤ እና ቢወድቅ ዳግም ይነሳል፣ መስዋዕቱ ለእኔ ከፍሬው በላይ ቅዱስ ነው፣ ይላል ጌታ።

፲፬ ስለዚህ፣ ፈጥኖም ወደዚህ፣ ወደፅዮን ምድር ይምጣ፤ እና በጊዜውም ለህዝቤ ጥቅም በስሜ የሚያተርፍ ይሆናል፣ ይላል ጌታ።

፲፭ ስለዚህ፣ ማንም ሰው አገልጋዬ ኦሊቨር ግሬንጀርን አይጥላው፣ ነገር ግን የህዝቤ በረከቶች በእርሱ ላይ ለዘለአለም ይሁኑ።

፲፮ ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በከርትላንድ ምድር ውስጥ ያሉት አገልጋዮቼ ጌታ አምላካቸውን፣ እና ደግሞም ቤቴን እንዲቀድሱ እና እንዲጠብቁ፣ እና የገንዘብ ለዋጮችን በጊዜዬ ይሽሩ ዘንድ ያስታውሱ፣ ይላል ጌታ። እንዲህም ይሁን። አሜን።