ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፵፬


ክፍል ፵፬

በየካቲት መጨረሻ አካባቢ፣ በ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ለስድኒ ሪግደን የተሰጠ ራዕይ። በዚህ ውስጥ የቀረቡትን ትእዛዛት በማክበር፣ ቤተክርስቲያኗ በሚቀጥለው ሰኔ መጀመሪያ ላይ ጉባኤ እንዲኖር መደበች።

፩–፫፣ ሽማግሌዎች በጉባኤ ይሰብሰቡ፤ ፬–፮፣ በምድሪቷ ህግጋት መሰረት እናም ደሆችንም ይንከባከቡ ዘንድ ራሳቸውን ያደራጁ።

፩ እነሆ፣ ጌታ ለእናንተ ለአገልጋዮቼ እንዲህ ይላል፣ የቤተክርስቲያኔ ሽማግሌዎች ከምስራቅና ከምእራብ፣ ከሰሜንና ከደቡብ፣ በደብዳቤ ወይም በሌላ መንገድ፣ መሰብሰባቸው ፍቃዴ ነው።

፪ እናም እንዲህ ይሆናል ያልፋል፣ ታማኝ ቢሆኑ፣ እና በእኔም ያላቸውን እምነት ቢጠቀሙ፣ ራሳቸውን በሚሰበስቡበት ቀን መንፈሴን አፈስባቸዋለሁ።

፫ እናም እንዲህ ይሆናል በአካባቢው ክፍለ ሀገሮች ይሂዱ፣ እና ለህዝቡ ንስሀን መግባትን ይስበኩ።

፬ እና፤ እንዲህም ሆኖ በሰው ህግጋት መሰረት ራሳችሁን ለማደራጀት ሀይልን እስካገኛችሁ ድረስ ብዙዎች ይለወጣሉ፤

፭ ጠላቶቻችሁ በእናንተ ላይ ስልጣን እንዳይኖራቸው በሁሉም ነገሮች እንድትጠበቁ፣ ህግጋቴንም ለመጠበቅ እንድትችሉ፣ ጠላትም ህዝቤን ለማጥፋት የሚሻባቸው ስምምነቶች ይሰበሩ ዘንድ ራሳችሁን ለማደራጀት ሀይል ታገኛላችሁ።

፮ እነሆ፣ እላችኋለሁ፣ ሁሉም ነገሮች በተቀበላችሁት ህጌ መሰረት እስከሚከናወኑ ድረስ ይጠበቁ ዘንድ፣ ደሆችንና ችግረኞችን ተንከባከቡ እና በሚያስፈልጋቸውም ነገሮች አገልግሏቸው። አሜን።