ክፍል ፵ ጥር ፮፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) በፈየት፣ ኒው ዮርክ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ለሲድኒ ሪግደን የተሰጠ ራዕይ። ይህ እራይ ከመመዝገቡ ቀደም ብሎ፣ የነቢዩ ታሪክ እንደሚገልጸው፣ “ጄምስ [ኮቪል] የጌታን ቃል ስላልተቀበለ እና ወደ ቀድሞው መሰረታዊ መርሆችና ሰዎች ስለተመለሰ፣ ጌታ ለእኔ እና ለስድኒ ሪግደን ተከታዩን ራዕይ ሰጠን” (ክፍል ፴፱ን ተመልከቱ)። ፩–፫፣ የስደት ፍራቻ እና ለአለም መጨነቅ ወንጌልን አለመቀበልን ያመጣል። ፩ እነሆ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ቃሌን ለመታዘዝ ቃል ኪዳንን ስለገባ፣ የአገልጋዬ ሀየጄምስ ኮቪል ልብ በፊቴ መልካም ነበር። ፪ እናም ቃሉን በደስታ ሀተቀበለ፣ ነገር ግን ወዲያውኑ ሰይጣን ፈተነው፤ እናም ለየስደት ፍራቻና ለአለም መጨነቅ ቃሉን ሐእንዳይቀበል አደረገው። ፫ ስለዚህም ቃል ኪዳኔን አፈረሰ፣ እናም መልካም የመሰለኝን በእርሱ ላይ አደርግ ዘንድ ፍቃዴ ነው። አሜን።