ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፴፯


ክፍል ፴፯

ታህሳሥ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በፈየት፣ ኒው ዮርክ፣ አቅራቢያ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ለስድኒ ሪግደን የተሰጠ ራዕይ። በዚህ ዘመን መሰባሰብን በተመለከተ የመጀመሪያው ትእዛዝ የተሰጠው በዚህ ውስጥ ነው።

፩–፬፣ ቅዱሳን በኦሀዮ እንዲሰባሰቡ ተጠሩ።

እነሆ፣ ኦሀዮ እስክትሄዱ ድረስ መተርጎም መቀጠልህ ለእኔ አስፈላጊ አይደለም፣ እና ይህም የሚሆነው በጠላት ምክንያት እና ለአንተ ደህንነት ነው።

እናም ዳግም እንዲህ እልሀለሁ፣ በእነዚያ ስፍራዎች ወንጌሌን እስክትሰብክ እናም ቤተክርስቲያኔ በሚገኝበት ስፍራ ሁሉ፣ በተለይም በኮስቪል የሚገኘውን እስከምታጠነክር ድረስ አትሄድም፤ እነሆም፣ በታላቅ እምነትም ወደ እኔ ይጸልያሉና።

እናም ዳግም፣ አገልጋዬ ኦሊቨር ካውድሪ ለሚመለስበት ጊዜ ለመዘጋጀት፣ በኦሀዮ አንድ ላይ መሰብሰባቸው አስፈላጊ እንደሆነ ትእዛዝን ለቤተክርስቲያኗ እሰጣለሁ።

እነሆ፣ ጥበብ በእዚህ ይላል፣ እናም እኔ እስክመጣ ድረስ እያንዳንዱ ሰው ለራሱ ይምረጥ። እንዲህም ይሁን። አሜን።