ክፍል ፳፰
በመስከረም ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በፈየት ኒው ዮርክ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት ለኦሊቨር ካውድሪ የተሰጠ ራዕይ። የቤተክርስቲያን አባል የሆነው ሀይረም ፔጅ፣ አንድ የሆነ ድንጋይ ነበረው እናም በዚህ ድንጋይ በመረዳት የፅዮንን ግንባታ በተመለከተ እና የቤተክርስቲያኗን ስርዐት በተመለከተ ራዕይን እንደተቀበለ ተናገረ። በዚህም ብዙ አባላት ተታለሉ፣ እናም ኦሊቨር ካውድሪም መጥፎ ተጽዕኖ አደረበት። ከተቀጠረው ጉባዔ ቀደም ብሎ፣ ነቢዩ ጌታን ስለነገሩ በትጋት ጠየቀው፣ እና ይህም ራዕይ ተከተለ።
፩–፯፣ ጆሴፍ ስሚዝ የሚስጥሩን ቁልፍ ይዟል፣ እናም ለቤተክርስቲያኗ ራዕይ የሚቀበለው እርሱ ብቻ ነው፤ ፰–፲፣ ኦሊቨር ካውድሪ ለላማናውያን ይስበክ፤ ፲፩–፲፮፣ ሰይጣን ሀይረም ፔጅን አታለለው እናም የሀሰት ራእዮችን ሰጠው።
፩ እነሆ፣ እንዲህ እልሀለሁ፣ ሀኦሊቨር፣ ለበአጽናኙ የሰጠሁትን ራእዮች እና ትእዛዛትን በተመለከተ ሐየምታስተምራቸው ነገሮች ሁሉ በቤተክርስቲያን እንድትሰማ ለአንተ ይሰጥሀል።
፪ ነገር ግን፣ እነሆ፣ እውነት እውነት እልሀለሁ፣ በዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከአገልጋዬ ሀከጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ በስተቀር ለማንም ሰው ትእዛዛትን እና ራእዮችን እንዲቀበል አይሾምም፣ እርሱም እንደ ሙሴ ሁሉ ይቀበላቸዋል።
፫ እና አንተም፣ ልክ እንደ ሀአሮን፣ ለእርሱ ለምሰጣቸውን ነገሮች፣ በእምነት ትዛዛቱን እና ራእዮቹን በኃይል እና ለበስልጣን ለቤተክርስቲያኗ ለማወጅ ታዛዥ ትሆናለህ።
፬ እናም ሀለመናገር ወይም ለማስተማር በአጽናኙ ወይም በሁሉም ጊዜ ለቤተክርስቲያኗ በትእዛዝ መልክ ከተመራህ፣ ይህንንም ልታደርገው ትችላለህ።
፭ ነገር ግን በጥበብ እንጂ በትእዛዝ መልክ አትጻፍ፤
፮ እናም የቤተክርስቲያኗ የበላይ እና ከአንተም የበላይ የሆነውን አታዝዘውም፤
፯ ስለሆነም በእርሱ ምትክ ሌላ አስክሾም ድረስ ሀየሚስጥራትን ለቁልፎች እና የታተሙትን ራዕዮች ሰጥቼዋለሁ።
፰ እናም፣ እነሆ፣ እልሀለሁ ሀወደላማናውያን ሄደህ ለወንጌሌን ትሰብክላቸዋለህ፤ እናም ትምህርትህን በተቀበሉ መጠን በመካከላቸው ቤተክርስቲያኔን ትመሰርታለህ፤ እናም ራእዬን ትቀበላለህ ነገር ግን በትእዛዝ መልክ አትጻፋቸው።
፱ እናም አሁን፣ እነሆ፣ እልሀለሁ፣ ይህ አልተገለጠም፣ እናም ሀየፅዮን ለከተማ የት እንዲሚገነባ ማንም አያውቅም፣ ነገር ግን ከዚህ በኋላ ይሰጣል። እነሆ እልሀለሁ፣ በላማናውያን ድንበር ላይ ይሆናል።
፲ ጉባዔው እስኪፈጸም ድረስ ከዚህ ስፍራ እንዳትሄድ፤ እናም አገልጋዬ ጆሴፍ በጉባኤውም ድምጽ ጉባዔውን እንዲመራ ይሾማል፣ እናም የሚልህን ሁሉ ትናገራለህ።
፲፩ እናም ዳግም፣ ወንድምህን ሀይረም ፔጅን ወስደህ በአንተ እና በእርሱ ሀመካከል ብቻ ከድንጋዩ የጻፈው ነገሮች ከእኔ እንዳልሆኑ እና ለሰይጣንም ሐእንዳታለለው ንገረው።
፲፪ ስለሆነም፣ እነሆ እነዚህ ነገሮች ለእርሱ አልተሰጡትም፣ ማናቸውም ነገሮች ቢሆኑ ለማንም የቤተክርስቲያን አባል የቤተክርስቲያኗን ቃል ኪዳን በሚጻረር መልክ አይሰጠውም።
፲፫ ስለሆነም ሁሉም ነገሮች በስራዐት እና በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ሀበጋራ ስምምነት፣ በእምነት ጸሎት መከናወን አለባቸው።
፲፬ እናም በላማናውያን መካከል ከመሄድህ በፊት እንደ ቤተክርስቲያኗ ቃል ኪዳን መሰረት ይህ ነገር እንዲረጋጋ ትረዳለህ።
፲፭ እናም ከምትሄድበት ጊዜ ጀምሮ እስከምትመለስበት ጊዜ ድረስ የምታከናውነው ነገር ሀይሰጥሀል።
፲፮ እናም ወንጌሌን በደስታ ድምጽ በማወጅ በሁሉም ጊዜ አንደበትህን መክፈት ይገባሀል። አሜን።