ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፻፪


ክፍል ፻፪

በየካቲት ፲፯፣ ፲፰፻፴፬ (እ.አ.አ.) የቤተክርስቲያኗ የመጀመሪያ ከፍተኛ ሸንጎ ሲመሰረት የተያዘ ቃለጉባኤ። የመጀመሪያዎቹ ቃለጉባኤዎች በሽማግሌዎች ኦሊቨር ካውድሪ እና ኦርሰን ሀይድ የተጻፉ ነበሩ። ነቢዩ ቃለጉባኤዎችን በሚቀጥለው ቀን አስተካከለ፣ እናም የተስተካከሉት ቃለጉባኤዎች በሚቀጥለው ቀን በከፍተኛ ሸንጎዎች “እንደ ቤተክርስቲያኗ መልክ እና ህገ መንግስት” በሙሉ ስምምነት ተቀባይነትን አገኙ። ይህ ክፍል በትምህርት እና ቃል ኪዳን ህትመት ሲዘጋጅ፣ ስለአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን የሆኑት ከ፴ እስከ ፴፪ ቁጥሮች በ፲፰፻፴፭ (እ.አ.አ.) በጆሴፍ ስሚዝ አመራር ተጨመሩ።

፩–፰፣ ከፍተኛ ሸንጎ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የሚነሱ አስቸጋሪ ጉዳዮች መፍትሄ ለማግኘት ተመድቧል፤ ፱–፲፰፣ ለሚቀርቡ ጉዳዮች ስነስርዓቶችም ተሰጥተዋል፤ ፲፱–፳፫፣ የሸንጎው ፕሬዘደንት የሚገባ ውሳኔን ይሰጣል፤ ፳፬–፴፬፣ የይገባኝ ስነስርዓትም ተሰጥቷል።

በዚህ ቀን ሀያ አራት የአጠቃላይ ሸንጎ ሊቀ ካህናት በጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ ቤት ውስጥ በራዕይ ተሰበሰቡ፣ እና አስራ ሑለት ሊቀ ካህናት እና፣ ጉዳዩ እንደሚያስፈልገው አንድ ወይም ሶስት ፕሬዘደንት ያለውን የክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ከፍተኛ ሸንጎ ማደራጀት ጀመሩ።

ከፍተኛ ሸንጎውም፣ ቤተክርስቲያኗ ወይም የኤጲስ ቆጶስ ሸንጎ በጉዳዩ የነበሩትን ሁሉ በማርካት መፍትሄ ለማግኘት የማይቻሉትን፣ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ሊነሱ በሚችሉ አስፈላጊ ችግሮች ላይ መፍትሄ ለማግኘት በራዕይ ተመድቧል።

ጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ፣ ስድኒ ሪግደንና ፍረድሪክ ጂ ዊሊያምስ በሸንጎው ድምፅ እንደ ፕሬዘደንቶች ተረጋግጠው ነበር፤ እና ሊቀ ካህናት ጆሴፍ ስሚዝ፣ ቀዳማዊ፣ ጆሴፍ ኮ፣ ጆን ዊትመር፣ ማርቲን ሀሪስ፣ ጆን ኤስ ካርተር፣ ጀርድ ካርተር፣ ኦሊቨር ካውድሪ፣ ሳሙኤል ኤች ስሚዝ፣ ኦርሰን ሀይድ፣ ስይልቨስተር ስሚዝ፣ እና ሉክ ጆንሰን ለቤተክርስቲያኗ ቋሚ ሸንጎ በመሆን፣ በሸንጎው በአንድ ድምፅ ተመርጠው ነበር።

ከዚያም ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ሸንጎዎች የተመደቡበትን እንደሚቀበሉ፣ እና በሰማይ ህግ መሰረት በዚያም ሀላፊነት እንደሚሰሩ ተጠይቀው ነበር፣ ለዚህም የተመደቡበትን እንደሚቀበሉ፣ እና ሀላፊነታቸውን በተሰጣቸው በእግዚአብሔር ጸጋ መሰረት እንደሚፈፅሙም መልስ ሰጡ።

ከላይ የተጠቀሱትን ሸንጎዎች ለመመደብ በቤተክርስቲያኗ ስም እና ለቤተክርስቲያኗ ድምጻቸውን የሰጡት ሸንጎዎች ቁጥር እንደሚከተለው ነበሩ፥ አርባ ዘጠኝ ሊቀ ካህናት፣ አስራ ሰባት ሽማግሌዎች፣ አራት ካህናት፣ እና አስራ ሶስት አባላት።

ድምፅ ሰጡ፥ ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ሸንጎዎች፣ ወይም በእነርሱ ወኪል የተመደቡት ምትኮች ሰባቱ ካልተገኙ በስተቀር ከፍተኛ ሸንጎው ለመስራት ሀይል ሊኖረው አይችልም።

እነዚህ ሰባቱም ብቁ እና ሸንጎዎቹ በማይኖሩበት ጊዜ በእነርሱ ምትክ ለመስራት ችሎታ አላቸው ብለው የሚያስቡአቸውን ሌሎች ሊቀ ካህናትን ለመመደብ ሀይል አላቸው።

ድምፅ ሰጡ፥ ከላይ የተጠቀሱት ማንኛቸውም ሸንጎዎች በሞት፣ በመተላለፍ ምክንያት ከሀላፊነት ቢወገዱ፣ ወይም ከቤተክርስቲያኗ መንግስት አካባቢ በመውጣት በመወገድ ምክንያት ክፍተት ቢኖር፣ በፕሬዘደንቱ ወይም ፕሬዘደንቶቹ ጥቆማ፣ እና ለዚህ አላማ በቤተክርስቲያኗ ስም ለመስራት በተሰበሰቡት በሊቀ ካህናቱ ከፍተኛ ሸንጎ ድምፅ ቅበላ ይህም ስፍራ ይሞላል።

የሸንጎው ፕሬዘደንት የሆነው የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንት የሚመደበው በራዕይ ነው፣ እና በቤተክርስቲያኗም ድምፅ አስተዳደሪነቱ እውቅና ይሰጠው

እና ይህም በሀላፊነቱ ክብር ምክንያት በቤተክርስቲያኗ ሸንጎ ይሰየማል፤ እና እርሱ በመተደበበት አይነት በተመደቡት ሁለት ሌሎች ፕሬዘደንቶች ይረዳ ዘንድም መብቱ ነው።

፲፩ እንዲረዱት የተመደቡት አንዱ ወይም ሁለቱ የማይኖሩ ቢሆን፣ ካለረዳቶቹ ሸንጎን ለመምራት ሀይል አለው፤ እና እርሱም ባይኖር፣ ሌሎቹ፣ ከሁለቱ አንዱ ወይም ሁለቱም ፕሬዘደንቶች በእርሱ ስፍራ ለመምራት ይችላሉ።

፲፪ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ሸንጎ በትክክለኛው አሰራር በየጊዜው በሚደራጅበት ጊዜ፣ አስራ ሁለቱ ሸንጎዎች ምርጫን በእጣ የመወሰን ሀላፊነት አላቸው፣ በዚህም፣ ከቁጥር አንድ ጀምሮ ተከታትሎ እስከ አስራ ሁለት ድረስ፣ ከአስራ ሁለቱ የትኛው አስቀድሞ እንደሚናገር ይወሰናሉ።

፲፫ በማንኛውም ጉዳይ ላይ ለመስራት ሸንጎው ሲሰበሰብ፣ አስራ ሁለቱ ሸንጎዎች ጉዳዩ አዳጋች መሆን አለመሆን ያስቡበት፤ ይህ ካልሆነ፣ ከላይ በተጻፈው ምሳሌ መሰረት ሁለት የሸንጎው አባላት ብቻ ይነጋገሩበታል።

፲፬ ነገር ግን አስቸጋሪ እንደሚሆን የሚታሰብበት ከሆነ፣ አራት ይመደባሉ፤ ከዚያም በላይ አስቸጋሪ ከሆነም፣ ስድስት፤ ነገር ግን በማንኛውም ጉዳይ ከስድስት በላይ እንዲናገሩ አይመደቡም።

፲፭ በሁሉም ጉዳዮች፣ ስድብ ወይም ግፍን አስቀድሞ ለመከላከል፣ ተከሳሹ በሸንጎው ግማሽ አባላት የመዳኘት መብት አለው።

፲፮ እና በሸንጎው ፊት ለመናገር የተመደቡት አማካሪዎች፣ ማስረጃው ከተመረመረ በኋላ፣ በእውነት ግልጽ ጉዳዩን በሸንጎው ፊት ያቅርቡ፤ እና እያንዳንዱም ሰው በእኩልነት እና በፍትህዊነት መሰረት ይናገር።

፲፯ ሙሉ ቁጥሮችን የያዙ፣ ማለትም ፪፣ ፬፣ ፮፣ ፰፣ ፲፣ እና ፲፪ን የመረጡት አማካሪዎች ለተከሰሰው ሰው የሚቆሙለት፣ እና ስደብ ወይም ግፍን አስቀድሞ የሚከላከሉ ግለሰቦች ናቸው።

፲፰ በሁሉም ጉዳዮች፣ መረጃዎቹ ከተሰሙ እና በጉዳዩ እንዲናገሩ የተመረጡት አማካሪዎች ንግግራቸውን ከፈጸሙ በኋላ፣ የተከሰሰው እና ከሳሹ በሸንጎው ፊት ለራሳቸው ለመናገር መብት አላቸው።

፲፱ መረጃዎቹ ከተሰሙ በኋላ፣ አማካሪዎቹ፣ ከሳሹ፣ እና ተከሳሹ ከተናገሩ በኋላ፣ ፕሬዘደንቱ በጉዳዩ ባለው መረጃ መሰረት ውሳኔ ይሰጣል፣ እና አስራ ሁለቱን አማካሪዎችንም ይህን በምርጫቸው እንዲቀበሉ ይጠራቸዋል።

ነገር ግን፣ መረጃውን እና ያለገለልተኛነት አቤቱታውን ከሰሙ በኋላ፣ የሚቀሩት ያልተናገሩት አማካሪዎች ወይም ማንኛቸውም በፕሬዘደንቱ ውሳኔ ስህተት ቢያገኙ፣ ይህንንም ይግለጹ፣ እና ጉዳዩም እንደገና ይቀርባል።

፳፩ እና በጥንቃቄ እንደገና ከሰሙት በኋላ፣ ተጨማሪ ብርሀን በጉዳዩ ላይ ከታየ፣ በዚህም መሰረት ውሳኔው ይቀየር።

፳፪ ምንም ተጨማሪ ብርሀን ባልተሰጠበት ጉዳይ ግን፣ የሸንጎ አብላጫው እንደነበረ የመወሰን ሀይል ስላለው፣ የመጀመሪያው ውሳኔ አይለወጥም።

፳፫ ትምህርትን ወይም መሰረታዊ መርህን በሚመለከት የችግር ጉዳይ፣ ለሸንጎውን አዕምሮዎች ጉዳዩን ግልፅ ለማድረግ ብቁ ፅህፈት ባይኖር፣ ፕሬዘደንቱ መጠየቅ እና የጌታን አስተሳሰብ በራዕይ ለማግኘት ይችላል።

፳፬ ሊቀ ካህናት፣ በውጪ እያሉ፣ ከዚህ በፊት እንደ ተመደበው፣ ሰዎቹ ወይም እያንዳንዳቸው ሲጠይቁ ለችግሮች መፍትሄ ለማግኘት ሸንጎን ለማደራጀት እና ለመጥራት ሀይል አላቸው።

፳፭ እና የተጠቀሰውም የሊቀ ካህናት ሸንጎ ከቁጥራቸው አንዱን በዚህ አይነት ሸንጎ ላይ ለጊዜው እንዲመራ ለመመደብ ሀይል አላቸው።

፳፮ ወዲያውም የሸንጎ ሂደታቸውን፣ ከውሳኔአቸው ጋር ሙሉ ምስክርን አያይዘው፣ ለቤተክርስቲያኗ ቀዳሚ አመራር ከፍተኛ ሸንጎ መቀመጫ የመላክ ሀላፊነትም ለተጠቀሱት ሸንጎዎችም ነው።

፳፯ ሰዎቹ ወይም እያንዳንዳቸው በተጠቀሱት ሸንጎ ውሳኔ የማይደሰቱ ቢሆን፣ ለቤተክርስቲያኗ ቀዳሚ አመራር ከፍተኛ ሸንጎ መቀመጫ ይገባኝ ለማቅረብ እና የምስክር ቃል ዳግም ሊያሰሙ ይችላሉ፣ ይህም ጉዳይ ከዚህ ቀደም በተጻፈው መሰረት ምንም ውሳኔ እንዳልተሰጠ በሚመስል አይነት ይደረግ።

፳፰ ይህ በውጪ ያሉት የሊቀ ካህናት ሸንጎ የሚጠሩት በጣም አስቸጋሪ ለሆኑት የቤተክርስቲያን ጉዳዮች ነው፤ እና ምንም ተራ ወይም ልዩ ያልሆኑ ጉዳዮች እንደዚህ አይነት ሸንጎን ለመጥራት ብቁ አይደሉም።

፳፱ በውጪ የሚጓዙት እና የሚገኙት ሊቀ ካህናት እንደዚህ አይነት ሸንጎ ለመጥራት ወይም ላለመጥራት አስፈላጊ እንደሆነም ለመወሰን ሀይል አላቸው።

በከፍተኛ ሸንጎ ወይም በሚጓዙ ሊቀ ካህናት እና የሚጓዙ የአስራ ሁለቱን ሐዋሪያት በያዘ ከፍተኛ ሸንጎ መካከል በውሳኔዎቻቸው ልዩነት አለ።

፴፩ ከመጀመሪያው ውሳኔ ይገባኝ ሊኖር ይችላል፤ ነገር ግን ከኋለኛው ውሳኔ ይግባኝ አይኖርም።

፴፪ የኋለኛው መጠራት የሚቻለው በቤተክርስቲያኗ አጠቃላይ ባለስልጣናት ብቻ፣ ይህም በመተላለፍ ጉዳይ ጊዜ ነው።

፴፫ ውሳኔ፥ የቤተክርስቲያኗ ቀዳሚ አመራር መቀመጫ ፕሬዘደንት ወይም ፕሬዘደንቶች ለይገባኝ ለመቅረብ የሚችል፣ እንደዚህ አይነት ማንኛውም ጉዳይ፣ ይገባኙን እና ከእርሱ ጋር ያለውን መረጃና ምስክር ከመረመሩ በኋላ፣ ዳግም እንዲሰማ መብት እንደሚገባው ለመወሰን ሀይል አላቸው።

፴፬ አስራ ሁለቱ አማካሪዎች ከዚያም አስቀድሞ ማን እንደሚናገር ለመወሰን፣ እጣ ወይም መምረጫ ወረቀት ጣሉ፣ እና የሚቀጥለውም ውጤቱ ነበር፥ ፩፣ ኦሊቨር ካውድሪ፤ ፪፣ ጆሴፍ ኮ፤ ፫፣ ሳሙኤል ኤች ስሚዝ፤ ፬፣ ሉክ ጆንሰን፤ ፭፣ ጆን ኤስ ካርተር፤ ፮፣ ስይልቨስተር ስሚዝ፤ ፯፣ ጆን ጆንሰን፤ ፰፣ ኦርሰን ሀይድ፤ ፱፣ ጄርድ ካርተር፤ ፲፣ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ቀዳማዊ፤ ፲፩፣ ጆን ስሚዝ፤ ፲፪፣ ማርቲን ሀሪስ።ከጸሎት በኋላ ጉባኤው ተበተነ።

ኦሊቨር ካውድሪ፣

ኦርሰን ሀይድ፣

ጸሀፊዎች