ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፵፫


ክፍል፤ ፵፫

በየካቲት ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ኦሀዮ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። በዚህ ጊዜ አንዳንድ የቤተክርስቲያኗ አባላት ሰዎች በሀሰት ባለራዕይ ነን በሚሉ ሰዎች ተረብሸው ነበር። ነቢዩ ጌታን ጠየቀና ለቤተክርስቲያኗ ሽማግሌዎች ይህን መልስ ተቀበለ። የመጀመሪያው ክፍል ስለቤተክርስቲያኗ አመራር ጉዳይን የሚመለከት ነበር፤ የኋለኛው ክፍል ሽማግሌዎች ለአለም ህዝብ የሚሰጡትን ማስጠንቀቂያዎች የያዘ ነበር።

፩–፯፣ ራዕይ እና ትእዛዛት የሚመጡት በተመደበው በአንዱ በኩል ብቻ ነው፤ ፰–፲፬፣ ቅዱሳኑ የሚቀደሱት በጌታ ፊት በቅድስና በመስራት ነው፤ ፲፭–፳፪፣ ሽማግሌዎች ለንስሀ እንዲጮሁና ሰዎችን ለዚያ ለጌታ ታላቅ ቀን እንዲያዘጋጁ ተልከዋል፤ ፳፫–፳፰፣ ጌታ ሰዎችን የሚጠራው በራሱ ድምፅ እና በፍጥረት ሀይል ነው፤ ፳፱–፴፭፣ አንድ ሺ ዘመን እና ሰይጣን የሚታሰርበት ይመጣል።

የቤተክርስቲያኔ ሽማግሌዎች ሆይ፣ አድምጡ፣ እናም የምናገራችሁንም ቃላት ስሙ።

እነሆ፣ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ከእጄ ትእዛዛትን እና ራዕዮችን ለመቀበል በመደብኩት በእርሱ በኩል ትእዛዛትን እንደ ቤተክርስቲያኔ ህግ ተቀብላችኋልና።

እናም ይህንንም በእርግጥ ታውቃላችሁ—እርሱ በእኔ የሚያምን ቢሆን፣ እርሱ እስከሚወሰድ ጊዜ ድረስ ማንም ትእዛዛትን እና ራእዮችን ለመቀበል የሚመደብ የለም።

ነገር ግን፣ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በእርሱ በኩል ካልሆነ በስተቀር ማንም ለዚህ ስጦታ አይመደብም፤ ይህም ከእርሱ ከተወሰደ በእርሱን ምትክ ሌላ ከመመደብ በስተቀር ምንም ሀይል አይኖረውምና።

እናም፣ በፊታችሁ የሚመጡትን የማንንም እንደ ራእዮች እና ትእዛዛት እንዳትቀበሉ፣ ይህም ለእናንተ ህግ ይሆናል፤

እና ይህንንም የምሰጣችሁ እንዳትታለሉ፣ እነርሱም ከእኔ እንዳልሆኑ ታውቁ ዘንድ ነው።

እውነት እላችኋለሁ፣ በእኔ የተሾመ እርሱ በበሩ ይገባል እናም የተቀበላችሁትን እና በመደብኩት በኩል የምትቀበሏቸውን ራዕዮች ለማስተማር፣ አስቀድሜ እንደነገርኳችሁ ይሾማል።

አሁንም፣ እነሆ፣ ስትሰበሰቡ እርስ በራሳችሁ ትማማሩ እና ትተናነጹ ዘንድ፣ እንዴት እንደምትሰሩ እና ቤተክርስቲያኔን እንደምትመሩ፣ በሰጠኋችሁ ህጋዊ ነጥቦችና ትእዛዛት እንዴት እንደምትሰሩ በጥልቅ ታውቁ ዘንድ እሰጣችኋለሁ።

በዚህም በቤተክርስቲያኔ ህግ መመሪያ ይሰጣችኋል፣ እናም በተቀበላችሁትም ትቀደሳላችሁ፣ እናም በፊት ለፊቴም በቅድስና ለመሄድ ራሳችሁን ታስተሳስራላችሁ—

ይህንም እስካደረጋችሁም ድረስ፣ ለተቀበላችሁት መንግስት ክብር ይጨመርላችኋል። ይህን ባታደርጉ ግን፣ የተቀበላችሁትም እንኳ ይወሰድባችኋል

፲፩ በመካከላችሁ ያለውን ክፋት አፅዱ፤ በፊቴም ራሳችሁን ቀድሱ፤

፲፪ የመንግስትን ክብሮች የምትሹ ከሆነ፣ አገልጋዬን ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊን መድቡ፣ እናም በጸሎት እምነት በፊቴ ደግፉት

፲፫ እና ደግሞም፣ እላችኋለሁ፣ የመንግስትን ሚስጥራት የምትሹ ከሆነ፣ ምግብና ልብሶች፣ እናም ያዘዝኩትን ስራዎች ያከናውነው ዘንድ የሚያስፈልጉትን ማናቸውንም ነገሮች ስጡት፤

፲፬ እናም ይህን ባታደርጉ፣ በፊቴ ንጹህ ህዝብን ለራሴ አስቀር ዘንድ፣ እርሱን ከሚቀበሉት ጋር ይቆያል።

፲፭ ደግሞም እላለሁ፣ የመደብኳችሁ የቤተክርስቲያኔ ሽማግሌዎች ሆይ አድምጡ፥ የተላካችሁት ልትማሩ አይደለም፣ ነገር ግን በመንፈሴ ሀይል በእጆቻችሁ የሰጠኋችሁን ነገሮች ለሰው ልጆች ታስተምሩ ዘንድ ነው፤

፲፮ እናም ከላይ ትማሩ ዘንድ ይገባል። ራሳችሁን ቀድሱ እና እንደተናገርኩት እንድትሰጡ ዘንድ፣ የሀይል መንፈሳዊ ስጦታም ይሰጣችኋል።

፲፯ አድምጡ፣ እነሆ፣ የጌታ ታላቅ ቀን ቀርቧልና።

፲፰ ጌታ ከሰማይ ድምጹን የሚሰጥበት ቀን ይመጣልና፤ ሰማያት ይንቀጠቀጣሉ እና ምድርም ትናወጣለች፣ እና ረጅም እና ጉልህ የሆነው የእግዚአብሔር መለከት ለሚያንቀላፉት ህዝብ እንዲህ ይላል፥ ቅዱሳን ሆይ ተነሱና ኑሩ፤ ኃጢአተኞች ሆይ ዳግም እስከምጣራ ድረስ ባላችሁበት ሁኑ እናም ተኙ

፲፱ ስለዚህ ራሳችሁን ከክፉዎች መካከል እንዳትገኙ ወገባችሁን ታጠቁ።

ድምጻችሁንም ከፍ አድርጉ እናም አትቆጥቡ። ለወጣቶችም ሆነ ለአዛውንቱ፣ ለታሰሩትም ሆነ ነፃ ለሆኑት፣ እንዲህ በማለት ህዝብን ለንስሀ መግባት ጥሯቸው፥ ራሳችሁን ለጌታ ታላቅ ቀን አዘጋጁ።

፳፩ እኔ፣ ሰው የሆንኩት፣ ድምጼን ከፍ ባደርግ እና ለንስሀ ብጠራችሁ እና ብትጠሉኝ፣ ንስሀ ግቡ፣ እና ለጌታ ታላቅ ቀን ተዘጋጁ፣ በማለት ህያው ለሆኑት ጆሮዎች ሁሉ ነጐድጓዶችም ከምድር ዳርቻ በታላቅ በድምፅ የሚናገሩበት ቀን ሲመጣ፣ ምንስ ትላላችሁ?

፳፪ አዎን፣ ደግሞም፣ እነዚህም ቃላት—ንስሀ ግቡ፣ የጌታ ታላቅ ቀን መጥቷልና በማለት መብረቆች ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ሲታዩ፣ እናም ህያው ለሆኑት ሁሉ በድምጽ ሲናገሩ፣ እና የሚሰሙትን ጆሮዎች ሁሉ ሲሰነጥቁ፣ ምንስ ትላላችሁ?

፳፫ ደግሞም፣ ጌታ ከሰማይ ቃሉን እንዲህ በማለት ይሰጣል፥ የምድር ህዝብ ሆይ፣ አድምጡ እና የሰራችሁን የእግዚአብሔርን ቃላት ስሙ።

፳፬ የምድር ህዝብ ሆይ፣ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ስንት ጊዜ በአንድነት ሰበሰብኳችሁ፣ እናንት ግን አልወደዳችሁም!

፳፭ በአገልጋዮቼ አንደበት፣ እና በመላዕክት አገልግሎት፣ እና በራሴም ድምፅ፣ እና በነጎድጓድ ድምጽ፣ እና በመብረቅ ድምጽ፣ እና በማዕበል ድምጽ፣ በምድር በመናወጥ ድምጽ፣ እና በበረዶ ናዳ ድምጽ፣ እና በረሀብ እናም በሁሉም ዓይነት ቸነፈር ድምጽ፣ እና በታላቅ የመለከት ድምፅ፣ እና በፍርድ ድምጽ፣ እና ቀኑን ሙሉ ምህረት ድምፅ፣ እና በዘለአለማዊ ህይወት ክብር እና ባለጠግነት ድምጽ ስንት ጊዜ ጠራኋችሁ፣ እናም በዘለአለማዊ ደህንነት አድናችሁም ዘንድ ወደድሁ፣ እናንት ግን አልተቀበላችሁኝም!

፳፮ እነሆ፣ የቁጣዬ ጽዋ የሚሞላበት ቀን መጥቷል።

፳፯ እነሆ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ የጌታ አምላካችሁ ቃላት ናቸው።

፳፰ ስለዚህ፣ ስሩ፣ በወይን ስፍራዬ ለመጨረሻ ጊዜ ስሩ—ለመጨረሻም ጊዜ በምድር የሚኖሩትን ጥሩ።

፳፱ በጊዜዬ በምድር ላይ ለፍርድ እገለጣለሁና፣ እናም ህዝቤም ይድናሉ፣ እና ከእኔም ጋር በምድር ይነግሳሉ።

በአገልጋዮቼ አንደበት የተናገርኩት ታላቁ አንድ ሺህ ዘመን ይመጣልና።

፴፩ ሰይጣን ይታሰራልና፣ ደግሞም ሲፈታ ለጥቂት ጊዜ ብቻ ይነግሳል፣ ከዚያም የምድርም ፍጻሜ ይሆናል።

፴፪ እና በጽድቅ የሚኖረውም በቅጽበት ይለወጣል፣ እና ምድርም በእሳት በሚመስል ሁኔታ ትጠፋለች።

፴፫ እና ክፉዎችም ወደ እቶኑ እሳት ይጣላሉ፣ እና በፊቴ ለፍርድ እስከሚመጡም ድረስ፣ መጨረሻቸውን ማንም ሰው በምድር አያውቀውም፣ ወይም መቼም አያውቁትም።

፴፬ እነዚህን ቃላት አድምጡ። እነሆ፣ እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የአለምሁሉ አዳኝ ነኝ። እነዚህን ነገሮች በልባችሁ አኑሩዋቸው፣ እናም የዘለአለም ማስተዋልም በአዕምሮዎቻችሁ ላይ ይረፍ

፴፭ የተረጋጋችሁ ሁኑ። ትእዛዛቴን ሁሉ ጠብቁ። እንዲህም ይሁን። አሜን።