ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፶፩


ክፍል ፶፩

በግንቦት ፳፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በቶምሰን ኦሀዮ ውስጥ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። በዚህ ጊዜ ከምስራቅ አገሮች የተሰደዱ ቅዱሳን ኦሀዮ እየደረሱ ነበር፣ እናም የሚኖሩበትን ስፍራ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆነ። የዚህ ስራ መከናወን የኤጲስ ቆጶሱ ሀላፊነት ስለነበር፣ ኤጲስ ቆጶስ ኤድዋርድ ፓርትሪጅ ስለጉዳዩ መመሪያ ፈለገ፣ እና ነቢዩም ጌታን ጠየቀ።

፩–፰፣ ኤድዋርድ ፓርትሪጅ ሀላፊነትንና ንብረትን እንዲቆጣጠር ተሹሟል፤ ፱–፲፪፣ ቅዱሳን በቅንነት ይስሩ እና በእኩልነትም ይቀበላሉ፤ ፲፫–፲፭፣ የኤጲስ ቆጶስ ጎተራ ይኑራቸው እና ንብረቶችንም በጌታ ህግ አማካይነት ይቆጣጠሩ፤ ፲፮–፳፣ ኦሀዮ ጊዜያዊ የመሰብሰቢያ ስፍራ ትሆናለች።

አድምጡኝ፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ፣ እና ለአገልጋዬ ኤድዋርድ ፓርትሪጅ እናገራለሁ፣ እና መመሪያዎችን እሰጠዋለሁ፤ ምክንያቱም እነዚህን ህዝብ የሚያደራጅበትን መንገድ ይቀበል ዘንድያስፈልገዋልና።

በህግጋቴ አማካይነትም መደራጀት አለባቸውና፤ ይህ ካልሆነ፣ እነርሱም ተለይተው ይጠፋሉ።

ስለዚህ፣ የተደሰትኩባቸው፣ አገልጋዬ ኤድዋርድ ፓርትሪጅ እና እርሱ የመረጣቸውም፣ ለእነዚህ ህዝብ፣ እያንዳንዱም ሰው እንደየቤተሰቡ፣ እንደ ሁኔታው እና እንደሚያስፈልገው መጠን፣ ድርሻቸውን በእኩል ይስጧቸው።

እናም አገልጋዬ አኤድዋርድ ፓርትሪጅ ለሰው ድርሻውን በሚመድብበት ጊዜ፤ ይህንንም በቤተክርስቲያን ያለውን መብትና ውርስ ኃጢአትን እስካልሰራ እና በቤተክርስቲያንም ድምጽ ተጠያቂ እስካልሆነ ድረስ እንደቤተክርስቲያኗ ህግጋት እና ቃልኪዳኖች መሰረት በቤተክርስቲያኗም ይዞታ ስር እንዲሆን ድርሻውን የሚያረጋግጥለት ጽሁፍ ይስጠው።

እናም ኃጢአት ከሰራ እና የቤተክርስቲያን አባል ለመሆን ብቁ ሆኖ ካልተገኘ ግን፣ ለኤጲስ ቆጶሱ በቅድስና ለቤተክርስቲያኔ ድሆች እና ችግረኞች የሰጠውን ድርሻውን የመጠየቅ መብት አይኖረውም፤ ስለዚህ፣ ስጦታውን ቀጥሎ ለመያዝ አይችልም፣ ነገር ግን ለእርሱ በተሰጠው ድርሻ ላይ ግን የመጠየቅ መብት ሊኖረው ይችላል።

እና በዚህም በምድሩ ህግጋት በኩል ሁሉም ነገሮች ይረጋገጣሉ።

እናም ለእነዚህ ህዝብ ተገቢ የሆኑት ነገሮችም ለእነዚህ ህዝብ ይሰጡ።

እና ለእነዚህ ህዝብ የተረፈውም ገንዘብገንዘቡንም በመውሰድ፣ በህዝቦቹ ፍላጎታቸው መሰረት፣ ምግብ እና ልብሶችን የሚያስገኝ ወኪል ለእነዚህ ህዝብ ይመደብ።

እንዳዘዝኳችሁ አንድ ትሆኑ ዘንድ፣ እያንዳንዱ ሰው በቅንነት ይስራ፣ እና በእነዚህ ህዝብም መካከል እኩልም ይሁኑ፣ እና በእኩልም ይቀበሉ።

ለእነዚህ ህዝብ ተገቢ የሆነውም ተወስዶ የሌላ ቤተክርስቲያን ለሆነው አይሰጥ።

፲፩ ስለዚህ፣ ሌላ ቤተክርስቲያን ከዚህች ቤተክርስቲያን ገንዘብ ከተቀበለ፣ በተስማሙበትም መጠን መልሰው ለቤተክርስቲያኗ ይክፈሉ።

፲፪ እና ይህም፣ በቤተክርስቲያኗ ድምፅ በተወከለው፣ በኤጲስ ቆጶሱ ወይም በወኪሉ በኩል የሚደረግ ይሁን።

፲፫ እና ደግሞም፣ ኤጲስ ቆጶሱ ለዚህች ቤተክርስቲያን የግምጃ ቤት ይመስርት፤ እናም ህዝቡ ከሚፈልገው በላይ የሆነው፣ ሁሉም ነገሮችን፣ በገንዘብ እና በምግብ በኤጲስ ቆጶሱ እጆች በኩል ይጠበቁ።

፲፬ እናም፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ስለሚሰራ፣ ለራሱ ፍላጎቶች፣ እናም ለቤተሰቦቹ ፍላጎቶች፣ የሚሆንን ይዞ ያስቀምጥ።

፲፭ እና ስለዚህም ራሳቸውን በህግጋቴ በኩል የሚያደራጁበት መብት ለእነዚህ ህዝብ ሰጥቻቸዋለሁ።

፲፮ እኔ ጌታ ሌላ እስከምሰጣቸው ድረስ፣ እና ከዚህም እንዲሄዱ እስከማዛቸው ድረስ፣ ይህን ምድር ለጥቂት ወቅት ቀድሼ እሰጣቸዋለሁ፤

፲፯ እናም ሰዓቱ እና ቀኑ አልተሰጣቸውም፣ ስለዚህ ይህን ምድር ለአመታት እንደሚኖሩበት አይነት ይስሩበት፣ እና ይህም ለእነርሱ የሚጠቅም ይሆንላቸዋል።

፲፰ እነሆ፣ ይህም በሌሎች ስፍራዎች፣ በሁሉም ቤተክርስቲያኖች ውስጥ፣ ለአገልጋዬ ኤድዋርድ ፓርትሪጅ ምሳሌ ይሆናል።

፲፱ እና ታማኝ፣ ሐቀኛ፣ እና ብልህ መጋቢ ሆኖ የተገኘውም ወደ ጌታው ደስታ ይገባል፣ እና ዘለአለማዊ ህይወትንም ይወርሳል።

በእውነትም፣ እንዲህ እላችኋለሁ፣ በማታውቁበት ሰአት ቶሎ የምመጣው፣ እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ። እንዲህም ይሁን። አሜን።