ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፺


ክፍል ፺

በመጋቢት ፰፣ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ኦሀዮ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። ይህ ራዕይ የቀዳሚ አመራርን ለመመስረት የቀጠለ እርምጃ ነው (የክፍል ፹፩ ርዕስን ተመልከቱ)፤ በዚህም ምክንያት፣ የተጠቀሱት አማካሪዎች በመጋቢት ፲፰፣ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) ተሾሙ።

፩–፭፣ የመንግስት ቁልፎች ለጆሴፍ ስሚዝ እና በእርሱም በኩል ለቤተክርስቲያኗ ተሰጥተዋል፤ ፮–፯፣ ስድኒ ሪግደን እና ፍረድሪክ ጂ ዊሊያምስ በቀዳሚ አመራር ያገልግሉ፤ ፰–፲፩፣ ወንጌሉ ለእስራኤል ህዝብ፣ ለአህዛብ፣ እና ለአይሁድ፣ እያንዳንዱም ሰው በሚሰማው ቋንቋ ይሰበክለት፤ ፲፪–፲፰፣ ጆሴፍና አማካሪዎቹ ቤተክርስቲያኗን በስርዓት ያደራጁ፤ ፲፱–፴፯፣ የተለያዩ ግለሰቦች በቅንነት እንዲሄዱ እና በመንግስቱ እንዲያገለግሉ በጌታ ተመክረዋል።

ጌታ እንዲህ ይላል፣ ልጄ ሆይ እውነት፣ እውነት እልሀለሁ፣ በልመናህ መሰረት፣ ኃጢአቶችህ ተሰርየውልሀል፣ የአንተ እና የወንድሞችህ ጸሎቶች ወደ ጆሮዎቼ መጥተዋልና።

ስለዚህ፣ የተሰጠህን የመንግስት ቁልፎች ለመያዝ ከዚህ ጀምሮ ተባርከሀል፤ ይህም መንግስት ለመጨረሻ ጊዜ እየመጣ ያለው ነው።

እውነት እልሀለሁ፣ በዚህ አለምም ሆነ በሚመጣው አለም ሳለህ፣ የመንግስት ቁልፎች ከአንተ በምንም መንገድ አይወሰድብህም፤

ይህም ቢሆን፣ አዎን፣ በአንተ በኩል የእግዚአብሔር ቃላት ለሌላ፣ እንዲሁም ለቤተክርስቲያኗ፣ ይሰጣሉ።

እና የእግዚአብሔርን ቃላት የሚቀበሉ ሁሉ፣ እንደ ቀላል ነገር እንዳይቆጥሯቸው፣ እና በዚህም ፍርድ እንዳይመጣባቸው፣ እና ማእበሉ ሲወርድ፣ እና ነፋሱም ሲነፍስ፣ እና ዝናብም ሲጥል፣ እና ቤታቸውንም ሲገፋው እንዳይደናቀፉ እና እንዳይወድቁ፣ እንዴት እንደሚይዟቸው ይጠንቀቁ

ደግሞም፣ ለወንድሞችህ ስድኒ ሪግደንና ፍረድሪክ ጂ ዊሊያም እውነት እላቸዋለሁ፣ ኃጢአቶቻቸውም ደግሞ ተሰርየዋል፣ እና የዚህን የመጨረሻ መንግስት ቁልፎችን መያዝን በተመለከተ ከአንተ ጋር እንደ እኩል ይቆጠራሉ፣

ደግሞም እንዲደራጅ ያዘዝኩትን የነብያት ትምህርት ቤት ማስተዳደሪያ ቁልፎችን መያዝን በተመለከተ ከአንተ ጋር እንደ እኩል ይቆጠራሉ፤

በዚህም፣ የሚያምኑት ሁሉ፣ ለፅዮን፣ እና ለእስራኤል ህዝብ፣ እና ለአህዛብ ደህንነት በአገለግሎታቸው ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ፤

በአገልግሎትህ ቃልን ይቀበሉ ዘንድ፣ እና በአገልግሎታቸውም ቃል፣ እስከ ምድር ዳርቻ ይሄድ ዘንድ፤ መጀመሪያ ወደ አህዛብ፣ እና ከዚያም እነሆ አስተውሉ፣ ወደ አይሁድም ይዞራሉ።

ከዚያም ህዝብን፣ የአህዛብን አገሮች፣ የጆሴፍን ቤት፣ የደህንነታቸውን ወንጌል ለማሳመን የጌታ እጅ በሀይል የሚገለጥበት ቀን ይመጣል።

፲፩ በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፣ የወንጌል ሙላትን ለዚህ ሀይል በተሾሙት በኩል፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ራዕይ በሚፈስባቸው በአፅናኙ አገልግሎት፣ እያንዳንዱ ሰው በገዛ ልሳን እና በራሱ ቋንቋ ይሰማል

፲፪ አሁንም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በአገልግሎቱ እና በአመራሩ እንድትቀጥሉ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።

፲፫ እና የነቢያትን ትርጉም ስትጨርሱ፣ ከዚህ በኋላ የቤተክርስቲያኗን እና የትምህርት ቤቱን ጉዳዮች ትመራላችሁ

፲፬ እና ከጊዜ ወደ ጊዜም፣ በአፅናኙ እንደሚገለጸው፣ ተነግረው የማይታወቁ የመንግስትን ሚስጥራት በራዕይ ተቀበሉ፤

፲፭ እና ቤተክርስቲያኖችንም በስርዓት አደራጁ፣ እና አጥኑና ተማሩ፣ እና ሁሉንም መልካም መጻህፍት፣ ቋንቋዎች፣ ልሳኖች፣ እና ህዝብን እወቁ።

፲፮ እና ይህም፣ ኮሚቴውን መምራት፣ እና የዚህን ቤተክርስቲያን እና መንግስት ጉዳዮች በስርዓት ማደራጀት፣ በህይወታችሁ ሁሉ ጉዳያችሁ እና ተልዕኮአችሁ ይሆናል።

፲፯ አትፈሩ፣ ወይም አትዋረዱ፤ ነገር ግን በትዕቢታችሁ እና በኩራታችሁም ተገሰጹ፣ በነፍሶቻችሁ ወጥመድ ያመጣልና።

፲፰ ቤቶቻችሁንም በስርዓት አስተካክሉ፤ ስራ ፈትነትን እና ጽዱ አለመሆንን ከእናንተ አርቁ።

፲፱ አሁን፣ እውነት እልሀለሁ፣ ወድያውኑ ሲቻል፣ ለአማካሪህ እና ለጸሀፊህ፣ እንዲሁም ለፍረድሪክ ጂ ዊሊያምስ ቤተሰብ ስፍራ ይሰጥ።

እና አዛውንቱ አገልጋዬ፣ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ቀዳማዊም፣ አሁን በሚኖርበት ስፍራ ከቤተሰቡ ጋር ይቀጥል፤ እና የጌታ አንደበት እስከሚወስንበትም ድረስ አይሸጥ።

፳፩ እና አማካሪዬ፣ እንዲሁም ስድኒ ሪግደን፣ የጌታ አንደበት እስከሚወስንበት ድረስ አሁን በሚኖርበት ይቆይ።

፳፪ እና ኤጲስ ቆጶሱ በቅንነት ወኪልን ለማግኘት ይፈልግ፣ እና ይህም ሰው ሀብት ያከማቸ፣ የእግዚአብሔር ሰው፣ እና ጠንካራ እምነት ያለው ይሁን—

፳፫ በዚህም እያንዳንዱን እዳ ለመክፈል ችሎታ ይኖረው ዘንድ፤ የጌታ ጎተራ በሰዎቹ አይኖች ፊት መጥፎ ስም አይኖረው ዘንድ ወኪሉ ሀብት ያከማቸ የእግዚአብሔር ሰው፣ እና ጠንካራ እምነት ያለው ይሁን።

፳፬ ተግታችሁ ፈልጉ፣ ዘወትር ጸልዩ፣ እናም እመኑ፣ እና በቅንነት ከተራመዳችሁ እና እርስ በራስ ቃል ኪዳን የገባችሁበትን ቃል ኪዳን ካስታወሳችሁ፣ ሁሉም ነገሮች ለእናንተ በጎነት አብረው ይሰራሉ።

፳፭ ቤተሰቦቻችሁ አነስተኛ ይሁኑ፤ በተለይም የቤተሰባችሁ አባል ያልሆኑትን በሚመለከት፤ በተለይም የአዛውንቱ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ቀዳማዊ ቤተሰብም፤

፳፮ ስራዎቼ እንዲከናወኑ፣ ለእናንተ የተሰጧችሁ ነገሮች ከእናንተ እንዳይወሰዱ እና ብቁ ላልሆኑት እንዳይሰጥ ዘንድ—

፳፯ እና በዚህም ያዘዝኳችሁን ነገሮች ለማከናወን እንዳትደናቀፉ ቤተሰቦቻችሁ አነስተኛ ይሁኑ።

፳፰ ደግሜ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ባሪያዬ ቪየና ዣክ ወጪዋን እንድትችል፣ እና ወደ ፅዮን ምድር ለመሄድ ገንዘብ ይሰጣት ዘንድ ፍቃዴ ነው፤

፳፱ እና የሚቀረው ገንዘብም ለእኔ ይቀደስ፣ እና በጊዜዬም ዋጋዋን ታገኛለች።

እውነት እላችኋለሁ፣ ወደ ፅዮን ምድር እንድትሄድ፣ እና ከኤጲስ ቆጶስ እጅ ውርሷን እንድትቀበል ፍቃዴ ነው፤

፴፩ ታማኝ እስከሆነች ድረስ በሰላም እንድትሰፍር፣ እና ከዚህ በኋላ በቀኖቿ ስራ ፈት እንዳትሆን ፍቃዴ ነው።

፴፪ እነሆም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ይህን ትእዛዝ ጻፉ፣ እና በፅዮን ውስጥ ያሉ ወንድሞቻችሁን፣ በፍቅር ሰላምታ፣ በጊዜዬ በፅዮን እንድትመሩ እንደተጠራችሁ ንገሯቸው።

፴፫ ስለዚህ፣ በዚህ ጉዳይ እኔን ማድከማቸውን ያቁሙ።

፴፬ እነሆ፣ እላችኋለሁ በፅዮን ያሉት ወንድሞቻችሁ ንስሀ ይግቡ፣ እና መላእክት በእነርሱ ይደሰቱ።

፴፭ ይህም ቢሆን፣ በብዙ ነገሮች አልተደሰትኩም፤ እና በአገልጋዬ ዊሊያም ኢ መክሌይን፣ ወይም በአገልጋዬ ስድኒ ጊልበርት አልተደሰትኩም፤ እና ኤጲስ ቆጶሱና ሌሎች ንስሀ የሚገቡበት ብዙ ነገሮች አላቸው።

፴፮ ነገር ግን እውነት እላችኋለሁ እኔ ጌታ ከፅዮን ጋር እጣላለሁ፣ እና ጠንካራዋን ለምኛለሁ፣ እና እስክትሸነፍ እና በፊቴ ንጹህ እስክትሆን ድረስ እገስጻለሁ

፴፯ ከስፍራዋ ልትነቃነቅ አትችልምና። እኔ ጌታ ተናግሬዋለሁ። አሜን።