ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፶፯


ክፍል ፶፯

በሀምሌ ፳፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በፅዮን፣ በጃክሰን የአገዛዝ ክፍል ሚዙሪ ውስጥ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። “የውርሳችሁን ምድር” ወደሚገልጽበት ምዙሪ እንዲሄዱ ጌታ ያዘዘውን በመከተል (ክፍል ፶፪)፣ ሽማግሌዎች ከኦሀዮ ወደ ሚዙሪ ምዕራባዊ ድንበር ተጉዘዋል። ጆሴፍ ስሚዝ ስለላማናውያን ጉዳይ በማሰብ፣ ነቢዩ እንዲህ አለ፥ “ምድረበዳው እንደ ጽጌረዳ የሚያብበው መቼ ነው? ፅዮን በክብሯ የምትገነባውስ መቼ ነው፣ እና በኋለኛው ቀናት ሁሉም አገሮች የሚመጡበት ቤተመቅደስህ የት ነው የሚቆመው?” ከዚህ በኋላም ይህን ራዕይ ተቀበለ።

፩–፫፣ ኢንዲፔንደንስ ሚዙሪ የፅዮን ከተማ እና የቤተመቅደስ ስፍራ ነው፤ ፬–፯፣ ቅዱሳንም መሬቶችን ይግዙ እና በዚያም አካባቢ ውርሶችን ይቀበላሉ፤ ፰–፲፮፣ ስድኒ ጊልበርት ግምጃ ቤትን ያቋቁም፣ ዊልያም ደብሊው ፈልፕስ አሳታሚ ይሁን፤ እና ኦሊቨር ካውድሪም የሚታተሙትን ፅሁፎች ያርም።

ለቅዱሳኑ መሰብሰቢያ የመደብኩት እና በቀደስኩት በዚህ በሚዙሪ ምድር ውስጥ በትእዛዜ አማካይነት የተሰበሰባችሁ የቤተክርስቲያኔ ሽማግሌዎች ሆይ፣ አድምጡ፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ።

ስለዚህ፣ ይህም የቃል ኪዳን ምድር፣ እና ለፅዮን ከተማ ስፍራም ነው።

እና ጌታ አምላካችሁ እንዲህ ይላል፣ ጥበብን የምትቀበሉ ከሆነ እነሆ ጥበብም። እነሆ፣ አሁን ኢንዲፔንደንስ ተብሎ የሚጠራው አማካዩ ስፍራ ነው፤ እናም የቤተመቅደሱ ስፍራ ከፍርድ ቤቱ ሳይርቅ፣ ወደ ምዕራብ የሚገኘው ነው።

ስለዚህ፣ ይህ ምድር፣ እናም ከዚያ ወደ ምዕራብ ያሉትም መሬቶች፣ እንዲሁም በአይሁድና በአህዛብ መካከል እስከሚሄደው መስመር ያሉትን መሬቶች በቅዱሳኑ መገዛታቸው ጥበብ ነው፤

እና ደቀ መዛሙርቶቼ ምድርን ለመግዛት እስከቻሉም ድረስ፣ የሳር መስክ ድንበር ላይ ያሉትን መሬቶች እንዲሁ ጥበብ ነው። እነሆ፣ ይህን ለዘለአለም ውርስ ማግኘታቸው ጥበብ ነው።

እና አገልጋዬ ስድኒ ጊልበርትም፣ በፅድቅ ለመደረግ እስከተከናወነ ድረስ እና ጥበብም እንደመራው መጠን፣ ገንዘብን ለመቀበል፣ ለቤተክርስቲያኗ ወኪል በመሆን፣ በአካባቢዎችም ሁሉ መሬቶችን ለመግዛት በሾምኩት ሀላፊነት ይቁም።

እናም አገልጋዬ ኤድዋርድ ፓርትሪጅም በሰጠሁት ሀላፊነት ይቁም፣ እና በትእዛዜም አማካይነት ለቅዱሳኑ ውርሳቸውን ያካፍል፤ እናም እንዲረዱት የመረጣቸውም ይህን ያድርጉ።

እና ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ ስድኒ ጊልበርት እራሱን በዚህ ስፍራ ያቋቁም፣ እናም ያለማታለል እቃዎችን በመሸጥ ምድርን ለቅዱሳኑ እርዳታ ለመግዛት እና ደቀ መዛሙርትን በሚወርሱበት ስፍራ ላይ እንዲቋቋሙ የሚያስፈልጋቸውን ማንኛውንም ነገሮች ለማግኘት የሚያስችሏቸውን ገንዘብ ለማግኘትም የግምጃ ቤትን ይመስርት።

እናም በእርሱ እንደ ጸሀፊ ከተቀጠሩት ሰዎች ማናቸውም በኩል ለህዝቡ እቃዎች ለመላክ እንዲችል፣ አገልጋዬ ስድኒ ጊልበርት ፈቃድ ያግኝ—እነሆ ይህ ጥበብ ነው፣ እና ማንም የሚያነበው ቢኖር ይረዳው፤

እናም በጭለማ እና በሞት አካባቢ እና ጥላ ውስጥ ላሉት ወንጌሌም እንዲሰበክ፣ እንደዚህም ቅዱሳኔን ያስተዳድራቸው።

፲፩ እና ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ ውልያም ደብሊው ፈልፕስ በዚህ ስፍራ ላይ ይስፈር፣ እናም ለቤተክርስቲያኑም አንድ አሳታሚ ሰው ይመስረት።

፲፪ እናም እነሆ፣ አለምም ፅሁፉን ከተቀበሉ—እነሆ ጥበብም እነሆ—ለቅዱሳኑ ጥቅም፣ ምንም የሚያገኘውን በፅድቅ ያግኝ።

፲፫ እናም አገልጋዬ ኦሊቨር ካውድሪ፣ በምመድብለት በማንኛውም ስፍራ፣ መንፈሱም በእርሱ በኩል ይህን ስለሚሰጥ፣ ሁሉም ነገሮች በፊቴ ትክክል እንዲሆኑ ፅሑፍ በመገልበጥ፣ በማስተካከል፣ እና በመምረጥ እንዳዘዝኩት እርሱን ይርዳው።

፲፬ እናም የተናገርኩባቸውም ሰዎች ሁሉ፣ በሚቻለው ፍጥነት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ነገሮችን እንደተናገርኳቸው ለማከናወን በፅዮን ምድር ውስጥ ይመስረቱ።

፲፭ እና አሁን ስለ መሰብሰቡ ጉዳይ—ኤጲስ ቆጶሱና ወኪሉ ወደዚህ ምድር እንዲመጡ ለታዘዙት ቤተሰቦች በሚቻልበት በኩል ወዲያውም ይዘጋጁ፣ እናም በሚወርሱበትም ስፍራ ይትከሉ።

፲፮ እናም ለሚቀሩትም ሽማግሌዎች እና አባላትም ሌሎች መረጃዎች ከዚህ በኋላ ይሰጣቸዋል። እንዲህም ይሁን። አሜን።