ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፻፰


ክፍል ፻፰

በታህሳስ ፳፮፣ ፲፰፻፴፭ (እ.አ.አ.)፣ በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ይህን ክፍል የተሰጠው ከዚህ በፊት እንደ ሰባ የተሾመውና ሀላፊነቱን እንዲያውቅ ራዕይ ለመጠየቅ ወደ ነቢዩ የመጣው ላይመን ሸርመን በጠየቀበት አይነት ነበር።

፩–፫፣ ላይመን ሸርመን ኃጢአቱ ተሰርዮለታል፤ ፬–፭፣ ከቤተክርስቲያኗ መሪ ሽማግሌዎች ጋር አብሮ ይቆጠር፤ ፮–፰፣ ወንጌሉን እንዲሰብክና ወንድሞቹን እንዲያጠናክር ተጠርቷል።

አግልጋዬ ላይመን ጌታ ለአንተ እንዲህ ይሏል፥ በዚህ ማለዳ ከመደብኩት ምክር ትቀበል ዘንድ ወደዚህ በመምጣትህ ምክንያት ኃጢአትህ ተሰርዮልሀል።

ስለዚህ፣ ስለመንፈሳዊ አቋምህ በሚመለከት ነፍስህ ትረፍ እና ድምጼን መቋቋምህንም አቁም።

እና ተነሳ እና የገባሀውንና የምትገባውን ቃል ኪዳንህን ታከብር ዘንድ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በተጨማሪ ተጠንቀቅ፣ እና በጣም ታላቅ በሆኑ በረከቶችም ትባረካለህ።

አገልጋዮቼ በክብር ስብሰባ እንዲሰበሰቡ እስኪጠሩ ድረስ በትእግስት ጠብቅ፣ ከዚያም ከመጀመሪያ ሽማግሌዎቼ ጋር ትታወሳለህ፣ እና ከመረጥኳቸው ከሚቀሩት ሽማግሌዎቼ ጋር መብትን በሹመት ትቀበላለህ።

እነሆ፣ በታማኝነት ከቀጠልክ ይህም ለአንተ የአብ ቃል ኪዳን ነው።

እና ከዚያም ጊዜ በኋላ በምልክህ በማንኛውም ስፍራ ወንጌሌን ለመስበክ መብት ይኖርህ ዘንድ በዚያም ቀን ይህ ይሟላልሀል።

ስለዚህ፣ በንግግርህ ሁሉ፣ በጸሎቶችህ ሁሉ፣ በምታበረታታው ሁሉ፣ እና በምታደርገው ሁሉ ወንድሞችህን አጠናክር

እነሆም እና አስተውል፣ ልባርክህ እና ላድንህ ለዘለአለም ከአንተ ጋር ነኝ። አሜን።