ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፸፱


ክፍል ፸፱

በመጋቢት ፲፪፣ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) በሀይረም ኦሀዮ ውስጥ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ።

፩–፬፣ ጄርድ ካርተር በአፅናኙ ወንጌልን እንዲሰብክ ተጠርቷል።

በእውነት እልሀለሁ፣ አገልጋዬ ጄሪድ ካርተር ዳግም ወደ ምስራቅ አገሮች፣ ከስፍራ ወደ ስፍራ፣ እናም ከከተማ ወደ ከተማ፣ በተሾመበት ሹመት ሀይል ውስጥ ታላቅ ደስታ የምስራች፣ እንዲሁም ዘለአለማዊ ወንጌልን፣ እየሰበከ እንዲሄድ ፍቃዴ ነው።

እናም እውነትን እና የሚሄድበትን መንገድ የሚያስተምረውን አፅናኝንም እልክለታለሁ፤

እናም የታመነ ቢሆን፣ ደግሞም በነዶም አነግሰዋለሁ።

ስለዚህ፣ ልብህ ይደሰት፣ አገልጋዬ ጄርድ ካርተር፣ እናም አትፍራ፣ ይላል ጌታህ፣ እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ። አሜን።