ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፲፯


ክፍል ፲፯

ሰኔ ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) በፈየት፣ ኒው ዮርክ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት የመፅሐፈ ሞርሞንን ታሪክ የተቀረጸበትን ሰሌዳዎች ከማየታቸው በፊት ለኦሊቨር ካውድሪ፣ ዴቪድ ዊትመር እና ማርቲን ሀሪስ የተሰጠ ራዕይ። ጆሴፍ ስሚዝ እና ጸሀፊው፣ ኦሊቨር ካውድሪ፣ ሶስት ልዩ ምስክሮች እንደሚመረጡ ከመፅሐፈ ሞርሞን ሰሌዳ ትርጉም ተገንዝበው ነበር (ኤተር ፭፥፪–፬፪ ኔፊ ፲፩፥፫፳፯፥፲፪ን ተመልከቱ)። ኦሊቨር ካውድሪ፣ ዴቪድ ዊትመር እና ማርቲን ሀሪስ በልዩ መሻት በመነሳሳት ሶስቱ ምስክሮች መሆንን ፈልገው ነበር። ነቢዩ ጌታን ጠየቀ፣ እናም ይህ ራዕይ በኡሪም እና ቱሚም አማካይነት የተሰጠ መልስ ነበር።

፩–፬፣ ሰሌዳዎቹ እና ሌሎች የተቀደሱ ነገሮችን ሶስቱ ምስክሮች በእምነት ይመለከታሉ፤ ፭–፱፣ ስለ መፅሐፈ ሞርሞን መለኮታዊነት ክርስቶስ ምስክርነቱን ሰጠ።

እነሆ፣ በቃሌ ላይ መደገፍ አለባችሁ እላችኋለሁ፣ ዓላማም በተሞላበት ልብ ካደረጋችሁ፣ ሰሌዳዎቹን፣ እንዲሁም ጥሩርን፣ የላባንን ሰይፍ፣ ከጌታ ጋር ፊት ለፊት በተነጋገርንበት ጊዜ ለያሬድ ወንድም የተሰጡትን ኡሪም እና ቱሚም፣ እናም በቀይ ባህር ዳርቻ በምድረበዳ ለሌሒ የተሰጠውን ተዓምረኛ ጠቋሚ ትመለከታላችሁ

እናም እነርሱን የምትመለከቱት በእምነታችሁ፣ እንዲሁም ጥንታዊ ነቢያት በነበራቸው አይነት እምነት ነው።

እምነት ካገኛችሁ እና በአይኖቻችሁ ካያችኋቸው በኋላ በእግዚአብሔር ሀይል ስለእነርሱ ትመሰክራላችሁ

እናም አገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ፣ እንዳይጠፋ ዘንድ፣ በዚህ ስራ ለሰው ልጆች የጽድቅ አላማዬን አመጣ ዘንድ ይህንን ታደርጋላችሁ።

እናም አገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ፣ እንደተመለከታቸው ሁሉ፤ እናንተም እንዲሁ እንደተመለክታችሁ ትመሰክራላችሁ፣ እናም እርሱም የተመለከታቸውም በእኔ ኃይል ነው፣ ምክንያቱም እምነት ስለነበረው ነበር።

እና እርሱም መፅሐፍን፣ እንዲሁም እኔ ያዘዝኩትን ክፍል፣ ተርጉሟል፣ እናም ጌታ እና አምላካህ ህያው እንደሆነ ይህም እውነት ነው።

ስለዚህ ልክ እንደ እርሱ አንድ አይነት ሀይል፣ እናም አንድ አይነት እምነት፣ እናም አንድ አይነት ስጦታ ተቀብላችኋል፤

እናም የሰጠኋችሁን የመጨረሻ ትእዛዛቴን ከፈጸማችሁ የሲዖል ደጆችም አይቋቋማችሁም፣ ጸጋዬ ለእናንተ በቂ ነውና፣ እናም በመጨራሻው ቀን ከፍ ትላላችሁ።

እናም ለሰው ልጆች የጽድቅ አላማዬን አመጣ ዘንድ፣ እኔ ጌታችሁና አምላካችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ተናግሬዋለሁ። አሜን።