ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፱


ክፍል ፱

ሚያዚያ ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) በሀርመኒ፣ ፔንስልቬንያ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት ለኦሊቨር ካውድሪ የተሰጠ ራዕይ። ኦሊቨር ትዕግስተኛ እንዲሆን ተገሰጸ እናም ለመተርጎም ከመሞከር ይልቅ ለጊዜው የተርጓሚውን ቃላት በመጻፍ እንዲደሰት ተመከረ።

፩–፮፣ ሌሎች ጥንታዊ መዛግብት ገና ይተርጎማሉ፤ ፯–፲፬፣ መፅሐፈ ሞርሞን በጥናት እና በመንፈሳዊ ማረጋገጫ ተተረጎመ።

እነሆ፣ ልጄ ሆይ እንዲህ እልሀለሁ፣ ከእኔ በፈለከው መሰረት ስላልተረጎምህ እናም ዳግም ለአገልጋዬ፣ ለጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ መጻፍን በመጀመርህ ምክንያት በእርሱ ላይ እምነት የጣልኩበትን መዝገብ እስክትጨርስ ድረስ እንድትቀጥል እፈልጋለሁ።

እና ከዚያም እነሆ፣ ሌሎች መዛግብቶች አሉኝ፣ ያንንም በመተርጎም እንድትረዳ ኃይል እሰጥኃለሁ።

ልጄ ትዕግስተኛ ሁን፣ ይህ በእኔ ዘንድ ጥበብ ነውና፣ እናም በአሁኑ ጊዜ መተርጎምህ አስፈላጊ አይደለም።

እነሆ፣ እንድታደርገው የተጠራህበት ስራ ለአገልጋዬ ለጆሴፍ እንድትጽፍ ነው።

እናም፣ እነሆ፣ ይህንም እድል ከአንተ የወሰድኩብህ መተርጎም በጀመርህ ጊዜ እንደ ጀመርኸው ባለመቀጠልህ ምክንያት ነው።

አታጉረምርም፣ ልጄ ሆይ፣ ከአንተ ጋር በዚህ ሁኔታ ይህን ማድርጌ ጥበብ ነው።

እነሆ፣ አልተረዳህም፤ እኔን ከመጠይቅህ በስተቀር ምንም ሳታስብበት፣ እንደምሰጥህ ገምተህ ነበር።

ነገር ግን እነሆ፣ እንዲህ እልሀለሁ፣ በአእምሮህ ውስጥ ልታጠናው ይገባል፤ ከዚያም ትክክለኛ መሆኑን ልትጠይቀኝ ይገባል፣ እናም ትክክለኛ ከሆነ ውስጥህም እንዲቃጠል አደርጋለሁ፤ ትክክል እንደሆነም ይሰማሀል

ነገር ግን ትክክል ካልሆነ እንደዚህ ያሉ ስሜቶች አይሰሙህም፣ ነገር ግን የተሳሳተ ነገርን የሚያስረሳ የሀሳብ ብዥታ ይሆንልሀል፤ ስለዚህ፣ ከእኔ ካልተሰጠ በስተቀር ቅዱስ የሆነውን መጻፍ አትችልም።

አሁን፣ ይህን አውቀህ ቢሆን ኖሮ መተርጎም በቻልህ ነበር፤ ሆኖም፣ አሁን መተርጎምህ አስፈላጊ አይደለም።

፲፩ እነሆ፣ በጀመርህበት ጊዜ አስፈላጊ ነበር፤ ነገር ግን ፈራህ፣ እናም ጊዜውም አለፈ፣ እናም አሁን አስፈላጊ አይደለም፤

፲፪ የጠፋውን ጊዜ ለመተካት ለአገልጋዬ ጆሴፍ በቂ ጥንካሬን አብጅቼ እንደሰጠሁት አታይምን? እናም ማናችሁንም ቢሆን አልኮነንኩም።

፲፫ እንድታደርግ ያዘዝኩህን አድርግ፣ እናም ትበለጽጋለህ። ታማኝ ሁን፣ እናም ለፈተና ራስህን አታጋልጥ።

፲፬ አንተን ለጠራሁበት ስራ ጸንተህ ቁም፣ እናም ከራስ ጠጉርህ አንዲት አትጠፋም፣ እናም በመጨረሻውም ቀን ከፍ ትላለህ። አሜን።