ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፶፬


ክፍል ፶፬

በሰኔ ፲፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ለኑወል ናይት የተሰጠ ራዕይ። በቶምሰን ኦሀዮ ውስጥ ይኖሩ የነበሩት የቤተክርስቲያኗ አባላት ስለ ንብረት መቀደስ ጉዳዮች አልተስማሙም ነበር። እራስን መውደድና ስግብግብነትም ይታዩ ነበር። ወደ ሼክርስ ሄዶበት ከነበረው ሚስዮን በኋላ (ክፍል ፵፱ መግቢያን ተመልከቱ)፣ ሊመን ኮፕሊም ትልቅ የእርሻ ስፍራውን ከኮልዝቪል ኒው ዮርክ ለሚመጡ ቅዱሳን በውርስ ለመባረክ የገባውን ቃል ሰብሮ ነበር። በዚህ ምክንያትም፣ (በቶምሰን ውስጥ የሚኖሩ አባላት መሪ) ኑወል ናይት እና ሌሎች ሽማግሌዎች ምን ማድረግ እንደሚችሉ ለመጠየቅ ነቢዩ ዘንድ መጥተው ነበር። ነቢዩም ጌታን ጠይቀ እናም በቶምሰን የሚኖሩትን አባላት ከሊመን ኮፕሊ እርሻ እንዲወጡ እና ወደ ምዙሪ እንዲጓዘ መመሪያ የሚሰጠውን ይህን ራዕይ ተቀበለ።

፩–፮፣ ምህረት ለማግኘት ቅዱሳን የወንጌሉን ቃል ኪዳን መጠበቅ አለባቸው፤ ፯–፲፣ በስቃይም ትዕግስተኛ መሆን አለባቸው።

እነሆ፣ ጌታ፣ እንዲሁም አልፋና ኦሜጋ፣ የመጀመሪያውና የመጨረሻው፣ እንዲሁም ለአለም ኃጢአት የተሰቀለው እንዲህ ይላል—

እነሆ፣ በእውነት፣ እውነት እልሀለሁ፣ አገልጋዬ ኑወል ናይት፣ በሾምኩህ ስልጣን ውስጥ ጸንተህ ቁም።

እና ወንድሞችህ ጠላቶቻቸውን ለማምለጥ ፈቃድ ካላቸው፣ ለኃጢአቶቻቸው ሁሉ ንስሀ ይግቡ፣ እና በፊቴም በእውነት ትሁት እና የተዋረዱ ይሁኑ።

እናም ለእኔ የገቡት ቃል ኪዳን ስለተሰበረ፣ ይህም ከንቱ ሆኗል እናም ተሽሮአልም።

እናም በእርሱ ጠንቅ ማሰናከያ ለሚመጣበት ለዚያ ሰው ወዮለት፣ ወደ ጥልቅም ባሕር መሰጠም ይሻለው ነበርና።

ቃል ኪዳንን የሚያከብሩት እና ትእዛዝን የሚከተሉት ግን የተባረኩ ናቸው፣ እነርሱም ምህረትን ያገኛሉና።

ስለዚህ፣ ጠላቶቻችሁ እንዳይመጡባችሁ አሁን ሂዱ፣ ከአገሩም ሽሹ፤ እናም ተጓዙ፣ እና መሪያችሁ እና ገንዘቦችን እንዲከፍልላችሁ የምትሹትን ምረጡ።

እንደዚሁም ወደ ምዕራብ ክፍለ ሀገሮች፣ ወደ ሚዙሪ ምድር፣ ወደ ላማናውያን ድንበርም ተጓዙ።

ጉዟችሁን ከጨረሳችሁ በኋላም፣ እነሆ እንዲህ እላችኋለሁ፣ ስፍራን እስካዘጋጅላችሁ ድረስ፣ እንደ ሰዎች የምትኖሩበትን ፈልጉ።

እና ደግሞም፣ እስክመጣ ድረስ በስቃይም ትዕግስተኛ ሁኑ፤ እናም፣ እነሆ፣ በቶሎም እመጣለሁ፣ እና ደመወዜ ከእኔ ጋር ነው፣ እናም እኔን ተግተው የሚሹኝም ለነፍሳቸው እረፍትን ያገኛሉ። እንዲሁም ይሁን። አሜን።