ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፯


ክፍል ፯

ሚያዚያ ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) በሀርመኒ፣ ፔንስልቬንያ፣ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝና ኦሊቨር ካውድሪ በኡሪምና ቱሚም ተወዳጁ ደቀመዝሙር ዮሐንስ በስጋ መኖርና አለመኖርን በተመለከተ ለጠየቁት ጥያቄ የተሰጠ ራዕይ። ይህ ራዕይ በዮሐንስ በብራና ላይ ተጽፎ በራሱ ተደብቆ ከነበረው ጽሁፍ ላይ የተተረጎመው ነው።

፩–፫፣ የተወደደው ዮሐንስ እስከ ጌታ ምፅዓት ድረስ ይኖራል፤ ፬–፰፣ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ እና ዮሐንስ የወንጌልን ቁልፍ ይዘዋል።

እናም ጌታ እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥ የምወድህ ዮሐንስ ሆይ፣ ምንን ትሻለህ? የፈለግኸውን ብትጠይቅ እሱም ይሰጥኃል።

እናም እኔም እንዲህ አልኩት፥ ጌታ እንድኖርና ነፍሳትን ወደ አንተ እንዳመጣ በሞት ላይ ስልጣንን ስጠኝ አልኩት።

እናም ጌታም እንዲህ ይላልኝ፥ እውነት፣ እውነት፣ እልሀለሁ፣ ይህንን ስለፈለግህ እኔ በክብር እስክመጣ ድረስ ትኖራለህ እናም በሀገሮች፣ በነገዶች፣ በቋንቋዎች፣ እና በህዝብም ፊት ትተነብያለህ

በዚህም ምክንያት ጌታ ጴጥሮስን እንዲህ ይላልው፥ እኔ እስክመጣ እንዲኖር ብፈቅድ ያ ለአንተ ምንድን ነው? እርሱ ወደ እኔ ነፍሳትን ለማምጣት ፈልጓል፣ ነገር ግን አንተ በቶሎ ወደ እኔ በመንግስቴ መምጣትን ፈልገሀል።

ጴጥሮስምሆይ ለአንተ እንዲህ እልሀለሁ፣ ይህ መልካም ፈቃድ ነበር፤ ነገር ግን የምወደው እርሱ ተጨማሪ፣ ወይም ቀደም ብሎ ካደረገው የበለጠ ስራ በሰዎች መካከል ያደርግ ዘንድ ፈለገ።

አዎን፣ ታላቅ የሆነን ስራ ወስዷል፤ ስለዚህ እንደነበልባል እሳት እና እንደ አገልጋይ መልአክ አደርገዋለሁ፤ እርሱም በምድር ለሚኖሩ የደህንነት ወራሾችን ያገለግላል።

እናም ለእርሱና ለወንድምህ ለያዕቆብ እንድታገለግል አደርግሀለሁ፤ እናም ለእናንተ ለሶስታችሁም እኔ እስክመጣ ድረስ ይህን ስልጣን እና የአገልግሎቱን ቁልፍ እሰጣችኋለሁ።

እውነት እላችኋለሁ፣ ሁለታችሁም እንደመሻታችሁ ይሆንላችኋል፤ ሁለታችሁም በፈለጋችሁት ነገሮች ትደሰታላችሁና