ክፍል ፻
በጥቅምት ፲፪፣ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) በፔሪስበርግ ኒው ዮርክ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ለስድኒ ሪግደን የተሰጠ ራዕይ። ሁለቱ ወንድሞች፣ ለብዙ ቀናት ከቤተሰቦቻቸው ተለያይተው ስለነበር፣ ስለእነርሱ አስበው ነበር።
፩–፬፣ ጆሴፍ እና ስድኒ ለነፍሳት ደህንነት ወንጌሉን ይስበኩ፤ ፭–፰፣ የሚናገሩትም በዚያች ሰዓት ይሰጣቸዋል፤ ፱–፲፪፣ ስድኒ ቃል ተቀባይ ይሁን እና ጆሴፍ ገላጭ እና በምስክርም ሀያል ይሁን፤ ፲፫–፲፯፣ ጌታ ንጹህ ህዝብ ያነሳል፣ እና የሚታዘዙም ይድናሉ።
፩ በእውነት ባልንጀሮቼ ሀስድኒ እና ለጆሴፍ፣ ጌታ ለእናንተ እንዲህ ይላል፣ ቤተሰቦቻችሁ ደህና ናቸው፤ በእጆቼም ውስጥ ናቸው፣ እና መልካም እንደሚመስለኝም አደርግባቸዋለሁ በእኔ ሁሉም ሀይል አለና።
፪ ስለዚህ፣ ተከተሉኝ፣ እና የምሰጣችሁንም ምክር አድምጡ።
፫ እነሆ፣ እናም አስተውሉ፣ በዚህ ስፍራ፣ በዚህ ክፍለ ሀገር አካባቢ ብዙ ህዝብ አሉኝ፤ እና ውጤታማ በር በዚህ አካባቢ፣ በዚህ በምስራቅ ምድር ውስጥ ይከፈታል።
፬ ስለዚህ፣ እኔ ጌታ ወደዚህ ስፍራ ትመጡ ዘንድ ፈቀድኩኝ፤ ለነፍሳትም ሀደህንነት ይህም በእኔ ዘንድ አስፈላጊ ነበርና።
፭ ስለዚህ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ወደ እነዚህ ህዝብ ድምጾቻችሁን ከፍ አድርጉ፤ በልባችሁ የምጨምረውን ሀሳብ ሀተናገሩ፣ እና በሰዎችም ፊት አታፍሩም፤
፮ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት፣ አዎን፣ በዚያች ጊዜም፣ ምን እንደምትናገሩ ሀይሰጣችኋልና።
፯ ነገር ግን የምታውጁትን ማንኛውንም ነገር በስሜ፣ በሁሉም ነገሮች በተረጋጋ ልብ፣ ሀበትሁት መንፈስ ለታውጁ ዘንድ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።
፰ እና ይህን የተስፋ ቃል እሰጣችኋለሁ፣ ይህን ስታደርጉ ለምትሉት ማንኛቸውም ነገሮች ሁሉ ምስክር ይሰጣችሁ ዘንድ ሀመንፈስ ቅዱስ ይላካል።
፱ እና አንተ አገልጋዬ ስድኒ ለዚህ ህዝብ ሀቃል ተቀባይ እንድትሆን ፍቃዴ ነው፤ አዎን፣ በእውነትም በዚህ ሀላፊነት፣ እንዲሁም እንደ አገልጋዬ ጆሴፍ ቃል ተቀባይ እንድትሆኑ፣ እሾምሀለሁ።
፲ እና ለእርሱም ሀበምስክር ሀያል እንዲሆን ሀይል እሰጠዋለሁ።
፲፩ እና ቅዱሳን መጻህፍትን ሁሉ ለመዘርዘር ሀሀያል እንድትሆንም ዘንድ፣ ለእርሱም ቃል ተቀባይ እንድትሆን ዘንድ ሀይልን እሰጥሀለሁ፣ እና በምድር ላይ ስላለችው መንግስቴ ነገሮች በሚመለከት የሁሉም ነገሮች እርግጠኛነትን ታውቅ ዘንድ እርሱም ለአንተ ለገላጭ ይሆናል።
፲፪ ስለዚህ፣ በጉዞአችሁ ቀጥሉ እና ልባችሁ ይደሰቱ፤ እነሆ፣ እና አስተውሉ፣ እኔ እስከመጨረሻም ከእናንተ ጋር ነኝና።
፲፫ አሁንም ሀፅዮንን በተመለከት ቃልን እሰጣችኋለሁ። ምንም እንኳን ለጥቂት ዘመን ብትገሰፅም፣ ፅዮን ለትድናለች።
፲፬ ወንድሞቻችሁ፣ አገልጋዮቼ ሀኦርሰን ሀይድ እና ጆን ጉልድ፣ በእጆቼ ውስጥ ናቸው፤ እና ትእዛዛቴን እስከጠበቁ ድረስ ይድናሉ።
፲፭ ስለዚህ፣ ልባችሁ ይፅናኑ፤ በቅንነት ለሚራመዱት፣ እና ለቤተክርስቲያኗ ቅድስ እና ጥቅም ሀሁሉም ነገሮች አብረው ይሰራሉና።
፲፮ ለራሴም በፅድቅ የሚያገለግሉኝ ሀንጹህ ህዝብ አስነሳለሁና፤
፲፯ እና የጌታን ስም ሀየሚጠሩት፣ እና ትእዛዛቱን የሚጠብቁ ሁሉ ይድናሉ። እንዲህም ይሁን። አሜን።