ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፵፰


ክፍል ፵፰

በመጋቢት ፲፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ቅዱሳኑ የሚሰፍሩበትን መሬት ማግኘት የሚችሉበትን ዘዴ ነቢዩ ጌታን ጠይቆ ነበር። ወደ ኦሀዮ እንዲሰበሰቡ ጌታ ያዘዛቸውን በማክበር፣ ከምስራቅ ዩናይትድ ስቴትስ በሚሰደዱት የቤተክርስቲያኗ አባላት ምክንያት ይህ አስፈላጊ ጉዳይ ነበር። ክፍል ፴፯፥፩–፫፵፭፥፷፬ን ተመልከቱ።

፩–፫፣ በኦሀዮ የሚገኙት ቅዱሳን ከወንድሞቻቸው ጋር መሬታቸውን ይካፈሉ፤ ፬–፮፣ ቅዱሳን ምድርን ይግዙ፣ ከተማም ይስሩ፣ እና የቀዳሚ አመራሮቻቸውንም ምክር ይከተሉ።

ለአላችሁበት ሁኔታ አስፈላጊ ስለሆነ፣ አሁን በምትኖሩበት መቆየታችሁ ተገቢ ነው።

መሬት እስካላችሁ ድረስ፣ በምስራቅ ካሉ ወንድሞቻችሁ ጋር ተካፈሉ

መሬት ከሌላችሁም፣ መልካም በሚመስላቸው ስፍራዎች፣ በአካባቢያቸው ከሚገኙት በአሁንም ጊዜ ይግዙ፣ ምክንያቱም በዚህም ጊዜ መኖሪያ እንዲኖራቸው በጣም አስፈላጊ ነውና።

በጊዜው መሬት፣ እንዲሁም ከተማ፣ ለውርስ ለመግዛት እንድትችሉ፣ የምትችሉትን ያህል ገንዘብ ማጠራቀም እና የምትችሉትን ነገሮች በፅድቅ ማግኘታችሁ በጣም አስፈላጊ ነው።

ስፍራው የሚገለጥበት ወቅት ገና ነው፤ ነገር ግን ወንድሞቻችሁ ከምስራቅ ከመጡ በኋላ አንዳንድ ሰዎች ሹመት ይሰጣቸው፣ እና ለእነርሱም ስፍራውን እንዲያውቁ ይሰጣል፣ ወይም ለእነርሱ ይህ ይገለጣል።

መሬቶችንም እንዲገዙ እና የከተማውን መሰረት እንዲጀምሩ ሀላፊነት ይሰጣቸዋል፤ እና ከዚያም እያንዳንዱ ሰው እንደ ቤተሰቡ፣ እንደ ጉዳዮቹ፣ እና ከዚህ በፊት በተቀበላችሁትና ወደፊትም በምትቀበሉት ትእዛዝ በኩል በአመራሩና በቤተክርስቲያኗ ኤጲስ ቆጶስ እንደተወከሉለት፣ ከቤተሰቦቻችሁ ጋር መሰብሰብ ትጀምራላችሁ። እንዲህም ይሁን። አሜን።