ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፻፳፮


ክፍል ፻፳፮

በሐምሌ ፱፣ ፲፰፻፵፩ (እ.አ.አ.) በብሪገም ያንግ ቤት ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። በዚህ ጊዜ ብሪገም ያንግ የአስራ ሑለቱ ሐዋርያት ቡድን ፕሬዘደንት ነበር።

፩–፫፣ ብሪገም ያንግ ለአገልግሎቱ ተሞግሷል እና ወደፊትም ወደውጪ ከመጓዝ ፋታን አገኘ።

፩ ውድ እና ተወዳጅ ወንድም ብሪገም ያንግ፣ እውነት ጌታ እንዲህ ይልሀል፥ አገልጋዬ ብሪገም፣ እንዳለፉት ጊዜያት ቤተሰብህን እንድትተው አይጠበቅብህም፣ መስዋዕትህ በእኔ ዘንድ ተቀባይነትን አግኝቷልና።

፪ ስለስሜም በጉዞዎችህ ከባድ ስራህን እና አገልግሎትህን አይቻለሁ።

፫ ስለዚህ ቃሌን ወደውጪ እንድትልክ፣ እና ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለአለም ቤተሰብህን በልዩ ሁኔታ እንድትንከባከባቸው አዝሀለሁ። አሜን።